Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ሌዮ 14ኛ፥ አዲሱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተሰየሙ

ሌዮ 14ኛ፥ አዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተሰየሙ

Habemus Papam

የካርዲናሎች ጉባኤ ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስትን 267ኛው የሮም ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ እና የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት አድርጎ መርጧቸዋል። በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባ ለተሰበሰቡት ታዳሚዎች ይህን ያበሰሩት የካርዲናሎች ጠቅላላ ጉባኤ ሊቀ አገልጋይ ብጹዕ ካርዲናል ዶሚኒክ ማምበርቲ ናቸው።
አዲሱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዮ 14ኛ በቅድሚያ፥ “ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!” በማለት በአደባባዩ ለተገኘው በርካታ ቁጥር ላለው ሕዝብ ሰላምታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፥ የካርዲናሎች ጠቅላላ ጉባኤ ሊቀ አገልጋይ ብጹዕ ካርዲናል ዶሚኒክ ማምበርቲ ቀደም ብሎ ባሰሙት ንግግር፥ “ደስታን እነግራችኋለሁ”፣ “ጳጳስ አለን!” በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት መመረጣቸውን አብስረው፥ “እጅግ የተከበሩ የሮም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካርዲናል ሮበርት ፍራንሲስ ፕሪቮስት፥ ሌዮ 14ኛ የሚል አዲስ ስም ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ሊቀ አገልጋይ ካርዲናል ዶሚኒክ ማምበርቲ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ማዕከላዊ ሰገነት በኩል ቆመው ባሰሙት አጭር ንግግር፥ “ሃቤሙስ ፓፓም” ውይም “ጳጳስ አለን” በማለት ለሮም ከተማ ነዋሪዎች እና ለመላው ዓለም ሕዝብ ካርዲናል ሮበርት ፍራንሲስ ካርዲናል ፕርቮስት፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዮ አሥራ አራተኛ ተብለው መመረጣቸውን አብስረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን https://www.vaticannews.va/am/pope/news/2025-05/cardinal-elected-pope-papal-name.html

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።