የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 1

ጸሎተ ተሰዓቱ (ኖቬና) ዘቅዱስ ዮሴፍ - ቀን 1 

St Joseph Novena 2013 ec(በየዕለቱ የሚደገም)

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እኔ ደካማው ልጅህ ሰላም እልሃለሁ፡፡ አንተ የሚወዱህንና የሚያክብሩህን ትከላከላለህ፤ ታማልዳቸዋልህ፡፡ በአንተ ላይ ልዩ የሆነ መታመን እንዳለኝና ከአዳኜ ኢየሱስና ከቅድስት እናቱ በመቀጠል የደኅንነት ተስፋዬ አንተ ነህ፡፡ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር ወዳጆችን ለመርዳት ከቶ አታመነታም፡፡ ስለዚህም በትህትና ስምህን እጥራለሁ፡፡ ከምወዳቸው እና የቅድስት ቤተስብ አፍቃሪ ከሆኑት ጋር አማላጅነትህን በመተማመን ወደ አንተ እንቀርባለን፡፡ ለአዳኛችን ኢየሱስና ለወላዲተ አምላክ ባለህ ፍቅር በዚህች አለም እስካለንና በሞታችን ጊዜ እንዳትለየን እንለምንሃለን፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም እጮኛ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ንጹሕ፣ ትሑት፣ በቸርነት የተሞላ አዕምሮና ፍጹም ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛት ጸጋ አሰጠኝ፡፡ አንተ በኢየሱስና በድንግል ማርያም እጅ እንደሞትክ እኔም ተመሳሳይ ዕድል ያጋጥመኝ ዘንድ መሪ፣ አርአያ እና አባት ሁነኝ፡፡

አፍቃሪና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለመንፈሳዊና ለየእለቱ በጎነት በተለይ ደግሞ መልካም ሞት አገኝ ዘንድ በዚህች ሰዓት በልቤ ውስጥ ያለውን አሳብ አስፈላጊ የሆኑትን ጸጋዎች ከኢየሱስ መለኮታዊ ልብ ታሰጠኝ ዘንድ አማላጅነትህን እማጸንህለሁ፡፡

/እዚህ ላይ በልብ ያለውን አሳብ መጥቀስ/

ሥጋ የለብሰው ቃል ጠባቂ ስለእኔ የምታቀርበው ጸሎት በእግዚአበሔር ፊት እንደሚሰማ እተማመናለሁ፡ አሜን፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም እጮኛ፣ አፍቃሪና ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጥበቃህናን እርዳታህን የፈለገ፣ መጽናናትን ሳያገኘ የቀረ ማንም የለም፡፡ በቅዱስነትህ በመተማመን እነሆ ወደ ፊትህ እቀርባለሁ፡፡ የመድኃኒታችን ምድራዊ አባት ሆይ ልመናዬን በቸርነት ተቀበለኝ እንጂ ችላ አትበለኝ፡፡ አሜን፡፡

1ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ አንተ የኢየሱስ ክርስቶስ አሳዳጊ አባት በመሆን አንተን በሚስጥር ቅድስት ድንግል ማርያምን በቀጥታ በሚስጥረ ሥጋዌ እንድትሳተፉ እግዚአብሔር  መረጠ፡፡ እርሷም ኢየሱስ በውስጧ እንዲፀነስ ፈቀደች፤ መንፈስ ቅዱስ ከደሟ የኢየሱስን ትስብእት እንዲሠራ ፈቀደች፡፡ አንተ ግን ይህ ሚስጢር ይፈጸም ዘንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት - እመቤታቸን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን ከመውለዷ በፊት ሆነ በኃላ በማክበር በተለየ መንገድ የዚህ ሚስጢር ተሳታፊ ሆንክ፡፡ አንተ ድንግልናን ሳያፈርሱም  በጋብቻ መኖርን አስተማርክ፡፡ ይህም ጥንትም እግዚአብሔር  የታቀደ ነበር፡፡

ኢየሱስን በማሳደግና በመንከባከብ በርሱ ሕይወት በቀጥታ ተሳተፍክ፤ በዚህም ዓላማ እግዚአብሔር በፍቅርና በመሥዋዕትነት መንፈስ የተሞላ እውነተኛ አባት ልብ ሰጠህ፡፡ በገዛ እጅህ ሥራ ልፋት ለመለኮታዊ ሕጻን ምግብ፣ መጠለያና ልብስ በማቅረብ ከለላ ሰጠኸው፡፡ አንተ በእርግጥ የኢየሱስ ሕፃን ባልደረባውና ጠባቂው ነበርክ፡፡

ሄሮድስ ሊገደለው በፈለገ ጊዜ ሰማያዊ አባት ሕጻኑን ይዘህ በመሰደድ እንድታድነው እንዲነግርህ መልአኩን ወደ አንተ ላከ፡፡ አስፈላጊወን ሁሉ መሥዋዕትነት እንድትከፍል በአንተ እጅ ተወው፡፡ ሕጻን ኢየሱስ ያገኘው ብቸኛ መጠለያና ከለላ የአንተ አባታዊ ፍቅር ነበር፡፡ ጠላቶቹ ሁሉ እስኪወገዱ ድረስ ይህ አባታዊ ፍቅርህ በረሓውን አቆርጦ ወደ ግብጽ ወሰደው፡፡ ከዚያ በኃላ ልታሳድገውና ልትንከባከበው አስፈላጊውን ሁሉ ልታደርግለት በክንድህ ታቅፈኸው ወደ ናዝሬት ተመለስክ፡፡ አንድ ልጅ ከአባት ማግኘት የሚገባውን አንዳችም አላስቀረኽበትም፤ በእግዚአብሔር  ፈቃድ ምድራዊ አባቱ ነበርክና፡፡

አንተም እርሱን በልዪ ፍቅር አገለገልከው፤ ምክንያቱም ከማንኛውም ምድራዊ አባት በተለየ መልኩ እግዚአብሔር  በሰማያዊና በምልዕተ ባህርያዊ ፍቅር የተሞላ ልብ ስጥቶህ ስለነበረ ነው፡፡ አንተ ከህፃን ኢየሱስ ምንም ሳትጠብቅ ከታላቅ መሥዋዕትነት ጋር በፍፁም ደግነት አገለገልክ፤ የለፋኸው ለራስህ ሳይሆን ለሌሎች ጥቅም እንዲውል እንደታቀደ መሣሪያ ሲሆን የአንተ ተልዕኮ ሲሳካ፣ ልጅህ ኢየሱስ ሲጎላ አንተ ድብዝዝ ብለህ ከእይታ ጠፋኽ፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ አንተ በምድር ላይ የሰማያዊ አባትን ሥልጣን መወከል ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮአዊ በመሰለ መልኩም የኢየሱስ አባት በመሆን ለተወሰን ጊዜ የኢየሱስን መለኮታዊነት መደበቅ ስለነበርህ የሰማያዊ አባት ጥላ ነበርክ፡፡ ጥሪህ እንዴት ክቡርና አስደናቂ ነበር! ያፈቅርከውን፣ በክንድህ የያዝከውንና በታማኝነት ያገለገለክው ልዑል ኢየሱስ በሰማይ እግዚአብሔር የሆነ አምላክ አባት አለው፤ እራሱም አምላክ ነው፡፡ 

በእግዚአብሔር  መንግሥት ቅዱሳን የአንተ ማዕረግ ልዩ ነው፡፡ ምክንያቱም አንተ ሥጋ የለበሰው የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ክፍል ነበርክ፤ በናዝሬቱ ቤትህ ለሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት የሚሆነውን አዘጋጀህ፤ ስለኛ ብለህ የሚያስፈልገውን ሁሉ ፈጸምክ፡፡አንተ ለክርስቲያኖችና ለመላው የሰው ልጅ በጎ አድራጊ፣ በእግዚአብሔር  መንግሥት የላቅህ ቅዱስ ነህ፡፡ ከመላእክት የሚወዳደር የተለየ አክብሮት፣ ፍቅር፣ ውዳሴና ምስጋና ይገባሃል፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለመለኮታዊ ልጁ አባቱ እንድትሆን ስለመረጠህ እግዚአብሔር አምላካችንን እናመሰግንሃለን፡፡ ስለመመረጥህ ምልክት እንዲሆን አምላካችንና አዳኛችን ለሆነው ክርስቶስ ታማኝነት ፀጋ አሰጠን፡፡ አንተ ለእርሱ እንዳደረግከው መሥዋዕትነት በሚጠይቅ ፍቅርና ታማኝነት እንድናገለግለው አግዘን፡፡ ከእግዚአብሔር  ለኛ ያቀድልንን የቅድስና ጉዞ እንድንራመድ በአማላጅነትህ እርዳን፡፡ አሜን፡፡

የሕፃን ኢየሱስ አሳዳጊ አባት ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ - ለምንልን፡፡

የቅዱስ ዮሴፍ መዝሙር

.ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጠብቀን

ወደ ገነትም አድርሰን፡፡

የማርያም እጮኛ ሆይ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ

የአምላክ ልጅ

ለኛም አማላጅ::