Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ቅዱስ ዮሴፍ

ከቅዱስ ዮሴፍ ምን እንማራለን?

‘ዘመናችን’ ምን ዓይነት አባቶች ያስፈልጉታል?

‘ዘመናችን’ ምን ዓይነት አባቶች ያስፈልጉታል?

ቀደም ባለው ወር ር.ሊ.ጳጳሳት ፍራንሲስ ያለንበትን ዓመት (ከኅዳር 27 ቀን 2013 - ኅዳር 26 ቀን 2014) “የቅዱስ ዮሴፍ ዓመት” ብለው ሲያዉጁ፡ “አባታዊ ልብ” በሚል ርዕስ ካስተላለፉት ሐዋርያዊ መልዕክት ውስጥ የቅዱስ ዮሴፍን አባታዊ ልብ የሚገልጹትን ሰባት ባህርያት ማየታችን ይታወሳል፡፡ አሁንም ዓመቱን በሙሉ የቅዱስ ዮሴፍን አባታዊ ስብዕናና…

Read more: ‘ዘመናችን’ ምን ዓይነት አባቶች ያስፈልጉታል?

Write comment (0 Comments)

ከቅዱስ ዮሴፍ ምን እንማራለን? 2013 ዓ.ም.

ከቅዱስ ዮሴፍ ምን እንማራለን?

መግቢያ

ከቅዱስ ዮሴፍ ምን እንማራለን? በሚል ርዕስ ለዚህ የቅዱስ ዮሴፍ ቁምስና ዓመታዊ የቅዱስ ዮሴፍ ክብረ-በዓል ቅድመ-ዝግጅት የዘጠኝ ቀናት ጸሎትና አስተንትኖ መርሃ-ግብር ዝግጅት ላይ የተረዳሁትን፣ የገባኝን፣ ያስተነተንኩትንና በከፊል የኖርኩበትን እንዳጋራ ዕድሉ በክቡር ቆሞስ አባ ሙላት ስለተሰጠኝ ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ በተሰጠኝ ጊዜ፣ የማጋራችሁን እናንተም አስተንትናችሁ ትንሽ ጥቅም ታገኙበታላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡…

Read more: ከቅዱስ ዮሴፍ ምን እንማራለን? 2013 ዓ.ም.

Write comment (0 Comments)

የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 7 እና 8

7ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ የሠራተኞች ባልደረባ

ጸሎተ ተሰዓት (ኖቬና) ዘቅዱስ ዮሴፍ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በናዝሬት ከተማ ኑሮህን  ስትገፋ በአናጢነት ሙያ ነበር፡፡ አንተና ልጅህ በጉልበት ሥራ በቅንነት እንድትሠማሩ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የጉልበት ሥራ ለሚሠሩ ሁሉ  አርአያ ነህ፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም የመጣው በአብላጫው በድህነት ለሚኖሩት ነው፡፡ በነቢዩ ኢሳይያስ…

Read more: የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 7 እና 8

Write comment (0 Comments)

የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 9

9ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ የመልካም ሞት ባልደረባ

ጸሎተ ተሰዓት (ኖቬና) ዘቅዱስ ዮሴፍ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ከዚህ ዓለም በተለየህ ጊዜ የምትወዳቸው እና የሚወዱህ ኢየሱስና ማርያም ከጎንህ መገኘታቸው ተገቢና ትክክል ነው፡፡ ሙሉ ሕይወትህን ለኢየሱስና ማርያም መሥዋዕት አድርገህ አቀረብክ፡፡ በመጨረሻም አፍቃሪ ክንዳቸውን ተንተርሰህ የቅዱሳንን ሞት አገኘህ፡፡ ሞትን ፍቅር በተሞላበት መንፈስ እንደ…

Read more: የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 9

Write comment (0 Comments)

የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 6

 

6ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ የቤተሰብ ባልደረባ

ጸሎተ ተሰዓት (ኖቬና) ዘቅዱስ ዮሴፍ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እንደ ደግ የቅድስት ቤተሰብ ራስ አከብርሃለሁ፡፡ ከኢየሱስና ከማርያም ጋር በፍቅር ኖርህ፤ ተንቀሣቀስክ፣ ሠራህም፡፡ ቅዱስ ሉቃስ “ከእነርሱ ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፤ ይታዘዛቸውም ነበር ፡፡” /2፡51/ በማለት በአጭሩ የናዝሬቱን ሕይወትህን ይገልጻል፡፡ ይሁንና ይህ አጭር መግለጫ…

Read more: የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 6

Write comment (0 Comments)

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት