እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የ2013 ዓ.ም ዘመን መለወጫ መልዕክት።

የብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የ2013 ዓ.ም ዘመን መለወጫ መልዕክት።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

“አንተ ግን ያው አንተ ነህ፣ የዕድሜህም ዘመን ወሰን የለውም፣ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም” (መዝ.102፡ 27)

ብፁዐን ጳጳሳት፣ ክቡራን ካህናት፣ ገዳማውያንና ገዳማውያት፣ ክቡራን ምዕመናን በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ፣ ክቡራትና ክቡራን፤

ከሁሉ አስቀድሜ ለመላው ምዕመናን እንኳን…

Read more: የብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የ2013 ዓ.ም ዘመን መለወጫ መልዕክት።

Write comment (0 Comments)

የር.ሊጳ. ፍራንቼስኮስ የ2009 ዓ.ም. ፋሲካ ሌሊት ቅዳሴ ስብከት

በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በከፍተኛ ድምቀት ማክበራቸው ይታወቃል። የዚህ በዓል አንድ ክፍል በሆነው በእለተ ፋሲካ ማለትም በሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም. ቅዳሜ ምሽት የትንሣኤ ዋዜማ መስዋዕተ ቅዳሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ መሪነት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ዐቢይ ደብር ካህናት፣ ደናግላን፣ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት እንዲሁም ተለያዩ ሀገራት ልዑካን፣…

Read more: የር.ሊጳ. ፍራንቼስኮስ የ2009 ዓ.ም. ፋሲካ ሌሊት ቅዳሴ ስብከት

Write comment (0 Comments)

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን እግር ኳስ ተጨዋች በደብሊን ካቶሊክ ቤ/ያን የዲቁና ማዕረግ ተቀበለ።

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን እግር ኳስ ተጨዋች በደብሊን ካቶሊክ ቤ/ያን የዲቁና ማዕረግ ተቀበለ።

38ኛ ዓመት እድሜው ላይ የሚገኘው ዲያቆን ፊሊፕ መልራይን ከወጣት ቡድኑ ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ እ.ኤ.አ. ከ1992-1996-1999 ዓ.ም. የማንቸስተር ዩናይትድ፤ ከ1999-2008 ዓ.ም. ደግሞ በኖርዊች ሲቲ፡ ካርዲፍ ሲቲ፡ ሌይተን ኦሪየንትና ኪንግስ ሊን ቡድኖች የመሀል ሜዳ አጥቂ የእግር ኳስ ተጨዋች የነበረ ሲሆን ባለፈው ቅዳሜ በደብሊን ሊ. ጳጳስ ቤልፋስት መድኃኔዓለም ቤ/ያን ማዕረገ ዲቁናን ተቀብሏል።

ፊሊፕ በነበረው የእግር ኳስ ተጨዋችነት ወቅት ለአገሩ አየርላንድ 27 ጊዜ ተሰልፏል። አብዛኛውን ጊዜ በነበረው ደረጃ የሚገኙ ሰዎች ጫማቸውን ሲሰቅሉ ወደ አሰልጣኝነት ወይም በመገናኛ ብዙኃን የኳስ ሐተታ ባለሙያ ሲሆኑ እርሱ ግን “ጥሪዬ ነው” ብሎ ወዳመነበት መንፈሳዊ ሕይወት አዘንብሎ የተለያዩ የበጎ አድራጎቶችን ሲያበረክት ቆይቶ እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. የዶሚኒካን ገዳምን ተቀላቅሏል።

በመቀጠልም ለክህነት ዝግጅት የሚያስፈልገውን የሁለት ዓመት የፍልስፍና ትምህርት በሮም በማጥናት አራት ዓመት የሚወስደውን የነገረ መለኮት ትምህርት የመጨረሻ ዓመት በአየርላንድ በማድረግ ላይ ይገኛል። የአየርላንድ ዶሚኒካን ወንድሞች ድረ ገጽ እንደሚገልጸው ከጥቂት ወራት በኋላ የክህነትን ሢመት ተቀብሎ ሕዝበ እግዚአብሔርን የሚያገለግል መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፡- http://www.bbc.com/news/uk-northern-ireland-37820819

-      http://www.dailymail.co.uk/sport/football/article-3890752/Former-Manchester-United-footballer-Philip-Mulryne-Catholic-priest-ordained-Belfast.html

Read more: የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን እግር ኳስ ተጨዋች በደብሊን ካቶሊክ ቤ/ያን የዲቁና ማዕረግ ተቀበለ።

Write comment (0 Comments)

‹‹ሽማግሌዎች የሌሉበት አገር የሚባልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል›› ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ማክሰኞ የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱት ተቃውሞችና አለመረጋጋቶች አስመልክቶ ባወጣው የአቋም መግለጫና ሃይማኖታዊ ጥሪ፣ መንግሥትንና ምዕመንናን ለሰላማዊ መድረክ እንዲተጉ ጥሪ አቀረበ፡፡
የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት ተጠሪዎች፣ የጉባዔው የቦርድ አባላትና የበላይ ጠባቂዎች በተሰየሙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ…

Read more: ‹‹ሽማግሌዎች የሌሉበት አገር የሚባልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል›› ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን

Write comment (0 Comments)

የቅብጥ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክና ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ መሠረታዊ የመቀራረብ ሰነድ ፈረሙ

ያለፈው ቅዳሜ የተገባደደው የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የግብጽ ጉዞ ትልቁ ተግባራዊ መገለጫ የሆነው ክንዋኔ የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤ/ያን ፓትሪያርክ ከሆኑት ከቴዎድሮስ ዳግማዊ ጋር ያደረጉት ግንኙነትና የተፈራረሙት የአንድነት ሰነድ ነው። በሁለቱ ኃላፊዎች ግንኙነት ወቅት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጥምረት በሰማእታት ደም ይበልጥ የተሳሰረ መሆኑንና ይህንንም አንድነት በተሻለ መልኩ በፍቅር ድርጊቶች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ…

Read more: የቅብጥ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክና ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ መሠረታዊ የመቀራረብ ሰነድ ፈረሙ

Write comment (0 Comments)

የአራቱ ውድ እህቶች አጭር የሕይወት ታሪክ

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅ. ሐና ልጆች ማኅበር እህቶች ላይ ከቀናት በፊት የሁላችንን ልብ የነካ ኀዘን ማጋጠሙ ይታወሳል። በአንዳንድ ምክንያቶች የሕይወት ታሪካቸውን በወቅቱ ሳናካፍል ምንም እንኳ ጥቂት ቀናት ያለፉ ቢሆንም አሁንም ፋይዳ ይኖረዋል ብለን ስላመንበት ከማኅበራችው ያገኘነውን አጭር የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

የእህቶቻችን አጭር የሕይወት ታሪክ

እህት ሐና ወይንሸት ገብሩከአባታቸው…

Read more: የአራቱ ውድ እህቶች አጭር የሕይወት ታሪክ

Write comment (0 Comments)

ብፁእ ካርዲናል ብርሃነየሱስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን ሊ.ጳ. የ፳፻፱ ዓ.ም. የዘመን መለወጫ መልእክት

ብፁእ ካርዲናል ብርሃነየሱስ በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳት ለመላው ምዕመናን የ፳፻፱ (የ2009) ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

እግዚአብሔር ሆይ ከዘመናት እስከ ዘመናት መጠጊያ ሆነኸናል (መዝ.90፡1)

ብፁዐን ጳጳሳት
ክቡራን ካህናትና ገዳማውያን/ዊያት
ክቡራትና ክቡራን መዕመናን
መላው ሕዝበ እግዚአብሔር
በጎ ፍቃድ ላላቸው ሰዎች በሙሉ

የተወደዳችሁ ምዕመናን…

Read more: ብፁእ ካርዲናል ብርሃነየሱስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን ሊ.ጳ. የ፳፻፱ ዓ.ም. የዘመን መለወጫ መልእክት

Write comment (0 Comments)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያሪክ ዘኢትዮጵያ ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጋር ሊገናኙ ነው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ያኑ ብ.ወ.አ. ማቲያስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ሰኞ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጋር ለመገናኘት ወደ ሮም እንደሚያቀኑ ተገለጸ። ፓትሪያርክ ማቲያስ በዚሁ ጉዟቸው ወቅት በካቶሊካዊት ቤ/ያን የክርስቲያኖች ኅብረት እንቅስቃሴን ከሚያጠናክረው ምክር ቤት ጋር ስብሰባ እንደሚያደርጉና በቫቲካን የሚገኘውን የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ መቃብር እንደሚጎበኙም ታውቋል።
በሮም በሚገኘው የኡርባኒያኑም ኮሌጅ ቤተ ጸሎት ፓትሪያርኩና በሮም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሥርዓተ አምልኮ እንደሚያካሂዱ መርኃ ግብር ወጥቷል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በካቶሊክ ቤ/ያን መካከል ያለው ግንኙነት በጥሩ መልኩ የተጠናከረው በቀድሞው ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ጊዜ ሲሆን እርሳቸው እ.ኤ.አ. በ1993 ዓ.ም. ከር.ሊ.ጳጳሳት ቅ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊና እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. ደግሞ ከር.ሊ.ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው ጋር መገናኘታቸው ይታውሳል።
ምንጭ፡- http://en.radiovaticana.va/news/2016/02/25/ethiopias_orthodox_patriarch_to_meet_with_pope_francis/1211046

Read more: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያሪክ ዘኢትዮጵያ ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጋር ሊገናኙ ነው

Write comment (0 Comments)

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጉብኝት በግብጽ

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጉብኝት በግብጽ

ማንኛውም የአመፅና የጥላቻ ድርጊት በእግዚአብሔር ወይም በሃይማኖት ስም ተገንነት የሚደረግ ከሆነ የእግዚአብሔርን ስም ማዋረድ ነው!

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከሚያዝያ 20-21 የቆየ የሁለት ቀናት የግብጽ ጉብኝታቸውን ጨርሰው ወደ ቫቲካን ተመልሰዋል። በብዙ መልኩ ትልቅ ትርጉም ያለውና ውጤታማው ጉብኝታቸው ስለ ሰላም፣ ስለ አንድነት፣ ስለ ተስፋ፣ እምነትና…

Read more: የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጉብኝት በግብጽ

Write comment (0 Comments)

ሢመተ ክህነት በማኅበረ ሲታውያን

ሢመተ ክህነት በማኅበረ ሲታውያን

ጥር ፯ ቀን ፪፻፱ ዓ.ም. ብፁእ አባታችን ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ለዲያቆን ወመነኮስ ታዴዎስ ተስፋዬ ሢመተ ክህነትን አከናውነዋል።

አባ ታዴዎስ በአ.አ. የካፑቺን ፍልስፍናና ነገረ መለኮታዊ ተቋም ለሰባት ዓመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በተጨማሪም እንደ ሲታዊ መነኮስ ሁለት የሰአሊነት አንድ የተመክሮ እንዲሁም አንድ የቅድመ ክህነት ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ ፲፱ ቀዳስያን ካህናት፤ ወላጅ፤ ቤተሰቦቻቸውና ሌሎች ምእመናን በተገኙበት በቅ. ዮሴፍ ዘሲታውያን ቁምስና ቤ/ያን ክህነትን ተቀብለዋል። 

በእለቱ የገዳመ ሲታውያን ዘቅዱስ ዮሴፍ ማርያም ጽዮን ት/ቤት ለሁለተኛ ደረጃ ማስፋፊያ ያሠራውን አዲስ ሕንጻ በብፁእ አባታችን ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስና በኢትዮጵያ የሲታውያን ማኅበር ኃላፊ አባ ባዘዘው ግዛው የተመረቀ ሲሆን ማኅበሩ በሰፊው ደግሞ ካቶሊካዊት ቤ/ያን በኢትዮጵያ ትውልድን በትምህርት በመቅረጽ ዙሪያ ያላትን ሰፊና አኩሪ ነባር ታሪክ በብቃት የሚያስቀጥል መሆኑም በእለቱ ለተገኙት የት/ቤቱ መምህራን፤ የተማሪዎች ወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች ተግልጿል።

 

Read more: ሢመተ ክህነት በማኅበረ ሲታውያን

Write comment (0 Comments)

“ከሚከፋፍለን ይልቅ አንድ የሚያደርገን የላቀ ነው!” ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮስ

“ከሚከፋፍለን ይልቅ አንድ የሚያደርገን የላቀ ነው!” ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮስ በቫቲካን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያሪክ ዘኢትዮጵያን በተገናኙበት ወቅት በአጽኖዖት የተናገሩት ነው።
ብፁዕ ፓትሪያርኩ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በቫቲካን የተገኙ ሲሆን፡ በቫቲካን ውስጥ በ“ኮሌጆ ኢቶፒኮ” የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተማሪ ካህናት በመኖሪያቸው አቀባበል እንዳደረጉላቸውና ተይዞ በነበረው መርኀ ግብር መሠረት በካቶሊካዊት ቤ/ያን የክርስቲያኖች…

Read more: “ከሚከፋፍለን ይልቅ አንድ የሚያደርገን የላቀ ነው!” ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮስ

Write comment (0 Comments)

የቁስቋም ማርያም በዓልና የገዳመ ሲታውያን ፪ኛ ደረጃ ካቶሊክ ት/ቤት መሠረት ድንጋይ ሥርዓት በደብረ ብርሃን

እሑድ ኅዳር 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ብፁእ አባታችን ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የደብረ ማርያም ቁስቋም ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት ከአካባቢው፣ ከአዲስ አበባ ከመጡ ምእመንና ከብዙ ካህናት ጋር በጋራ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርጉ።

ይህ ደብር የሚተዳደረው ከቦታው 27 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በሚገኘው በደብረ መድኃኔዓለም የሲታውያን ገዳም መነኮሳት ሲሆን፤ በዚሁ ገዳም በደብረ ብርሃን ከተማ ሊከፈት ለታቀደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ብፁእ አባታችን ካርዲናል የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል። 

Read more: የቁስቋም ማርያም በዓልና የገዳመ ሲታውያን ፪ኛ ደረጃ ካቶሊክ ት/ቤት መሠረት ድንጋይ ሥርዓት በደብረ ብርሃን

Write comment (0 Comments)

Subcategories

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት