እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ካቶሊካዊ ምልክቶችና ትርጉማቸው

ካቶሊካዊ ምልክቶችና ትርጉማቸው

ምልክቶች ከጥንት ጀምሮ በባህል፣ በማኅበራዊ ሕይወትና በሃይማኖት ውስጥ ልዩ ቦታ የነበራቸውና ያላቸው ናቸው። ምልክቶች በእምነት ውስጥ ልዩ ቦታ ሲኖራቸው፤ የሐሳብና ጸሎት ትኩረት ማረፊያ ናቸው።  በካቶሊካዊት ቤተክርሰቲያናችንም ውስጥ ከጥንታዊው የክርስትና ዘመን ጀምሮ እስከጊዜያችን ድረስ ሁላችንም በጋራም ይሁን እንደየባህላችንና ትውፊታችን የምንጠቀምባቸው የተለያዩ እምነታችንን ገላጭ ምልክቶች አሉን፤ ከነዚህም ውስጥ የጥቂቶቹን ትርጉሞች ባጭር መልኩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። 

ክርስቶስ በመስቀል ላይ

Symbols1መስቀል፦ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሚያሳይ ነው። ይህ የተለመደ ካቶሊካዊ ምልክት ሲሆን፣ ቅዳሴ በሚቀደስበት መንበረ ታቦት ላይ ወይም ከመንበረ ታቦቱ ፊት ለፊት ይሰቀላል። መስቀሉ ላይ በምሕጻረ ቃል በላቲን የተጻፈ ”INRI” (Iesus Nazareno Rex Iudae) የሚል ጽሑፍ ሲገኝ “ኢየሱስ ናዝራዊ የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ትርጉም ነው ያለው። እነዚህ ቃላቶች የይሁዳ አስተዳዳሪ የነበረው ጲላጦስ ከመስቀሉ በላይ እንዲጻፍ ያዘዘው ጽሑፍ ነው።  መስቀል የመስዋዕት ምልክት ነው።{jathumbnail off}

 

 

 

 

 

 

 

አልፋና ኦሜጋ

Symbols2እነዚህ የመጀመርያውና የመጨረሻው የግሪክ ፊደል ናቸው። በዮሐንስ ራዕይ 22፤13 ኢየሱስ ራሱን አልፋና ኦሜጋ የመጀመርያና የመጨረሻ መሆኑን ይናገራል። ክርስቶስ የፍጥረት መጀመርያና መጨረሻ ነው። አልፋና ኦሜጋ ምልክቶች በተለያዩ የቤተክርስቲያን ሊጡርጊያዊ አዝማናት ይጠቀሙባቸዋል።

 

 

 

 

 

 

 

መስቀል

Symbols3በጣም የተስፋፋው የክርስቲያን ምልክት መስቀል ነው። መስቀል ክርስቲያን ባለበት ሁሉ ይገኛል። በሮማውያን ጊዜ መስቀል እንደ ውርደትና ስቃይ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ወንጀለኞች በምስቀል ተሰቅለው ይገደሉ ነበር። ለክርስቲያን ግን መስቀል የክርስቶስ ሞት ብቻ ሳይሆን የትንሳኤም ምልክት ሆነ።

 

 

 

 

 

ልበ ኢየሱስ

Symbols4የኢየሱስ ልብ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የሚያሳይ ምልክት ነው። ልብ የፍቅር ምልክት ነው። ልቡ በመስቀል ተወግቶና በእሾኽ ተከቦ ይሳላል። ይህ ደግሞ የኢየሱስን ለሰው ልጅ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳያል። እሱ ስለ ሰው ልጅ ሊሰቃይና ሊሞት ተዘጋጅቶ ነበር። ፍቅሩ ደግሞ ዘለዓለማዊ ኢዩ።

 

 

 

 

 

አይ ኤች ኤስ እና ሲኤአይ-አርኤችኦው ( IHS & CHI-RHO)

Symbols6Symbols5እነዚህ ፊደሎች በቤተክርስቲያን አልባሳት፣ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ፣ በተጠረቡ ድንጋዮች ላይና የቤተክርስቲያን ዕቃዎች ላይ ተጽፈው ይገኛሉ።

በግሪክ ቋንቋ ክርስቶስ የሚለው የመጀመርያዎቹ ሁለት ፊደሎች “ኤክስ” ና “” ናቸው፤ “”ን መስሎ በላቲን ፊደል የምናየው በግሪክኛ "ሮ" የሚል አደማመጥ ነው ያለው። እነዚህ ሁለቱ የመጀመሪያ ፊደሎች ማለትም “ኤክስ” ና “” ክርስቶስ በሚለው ምትክ ስም ሆነው ይጻፋሉ።   በግሪክ ፊደል “ኤክስ” ከ “ሲ ኤች አይ” ጋር “” ከ “አር” ጋር እኩል ነው።

ሲ ኤች አይ-አር ኤች ኦው (CHI-RHO) በመባልም ሲታወቅ፣ አንዱ በአንዱ ላይ ተደርቦ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግም ብክብ ከበባል።

 

 

 

 

 

ዓሳ

Symbols7ከጥንታውያን የክርስቲያን ምልክቶች አንዱ ዓሳ ነበር። ይህ ክርስቲያኖች - በተለይ በስደት ጊዜ ማንነታቸውን ለመግለጽ ይጠቀሙበት ነበር። ሮም በሚገኙት ካታኮምብ (ክርስቲያኖች በክርስቶስ በማመናቸው ከስደት ለመሸሽ ይደበቁበት የነበረ ቦታ) ውስጥ ይገኛል።

የመጀመርያዎቹ ፊደሎች የክርስቶስ ስሞች ሲነበቡ በግሪክ ቋንቋ ዓሳ የሚል ትርጉም ይሰጣሉ። በግሪክ ቋንቋ ዓሳ ICHTHUS ማለት ሲሆን፤ የኢየሱስ ስም በግሪክ ቋንቋ Iesous CHristos THeou Uios Soter ነው። ትርጉሙ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚኣብሔር ልጅ - አዳኝ” ማለት ነው።

ክርስቶስ ሐዋርያትን “የሰው አጥማጆች” ሲላቸው። የመጀመርያዎቹ ክርስቲያን አባቶች ታማኝ ዓሳዎች ተብለው ይጠሩ ነበር።

 

ርግብ

symbols10symbols12ርግብ የመንፈስ ቅዱስ ምልክት ነው። ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ርግብ ወደርሱ ወረደ። (ማቴዎስ 3፤16 እና ማርቆስ 1፤10)

ርግብ እንደ የሰላም ምልክት የወይራ ቅጠል ይዛ ትሳላለች። የእግዚኣብሔር ጸጋንም ያመለክታል።

የኖኅን ታሪክ እናስታውሳለን። እግዚኣብሔርን ምድርን በጥፋት ውሃ በቀጣ ጊዜ፤ ኖኅ ውሃው ደርቆ እንደሆነ ለማረጋገጥ ርግብን ላከ። ርግብም ስትመለስ ከደብረ ዘይት ተራራ የወይራ ቅጠል ይዛ መጣች። ይህም እግዚኣብሔር ለሕዝቡ ምልክት እንዳደረግ ነው።

 

 

ጠቦት (በግ)

Symbols8Symbols9ከክርስቲያን ምልክቶች አንዱ ጠቦት ነው። በዮሐንስ ወንጌል 1፤35-36 እና በዮሐንስ ራእይ 5፤4-6 እንዲሁም በቅዳሴ ጊዜ ክርስቶስ በአምሳል በግ ይጠቀሳል። በጉ ነጭ መሆኑ ንጹሕና ሐጢኣት የሌለበት መሆኑን ያመለክታል። በብሉይ ኪዳን በጎች ለመስዋዕትነት ይቀርቡ ነበር። ክርስቶስ የሰው ልጅን ከኃጢያት ለማዳን መስዋዕት ሆኖ ሞተ።

በጉ አንዳንድ ጊዜ ሰንደቅ ዓላማ (ባንዲራ) ይዞ ይሳላል። ይህም ክርስቶስ ሞት አሸንፎ መነሳቱን ያመለክታል። የድል ምልክት ማለት ነው።

 

 

 

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት