በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....
ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።
ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።
በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!
ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11
By Super User
“የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት ደስታ እንደገና ሊሰማን ይገባል!” ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ ጥር 5/2016 ዓ. ም. በቅዱስ...
By Super User
የሲታውያን ወንድሞች ገዳም የሆነው “ሲቶ የመጽሐፍትና ንዋየ ቅዱሳት መደብር” ዛሬ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም. ተመረቀ። በአዲስ አበባ...
By Super User
እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ወንድም ፍቃደ ሥላሴ (ፍቃዱ) ተስፋዬ እና ወንድም ሉቃስ (ብርሃኑ) ቡናሮ በአዲስ አበባ ቅ. ዮሴፍ ገዳም...
ቤተሰብ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ያለውን እውነታና ለዚህም የክርስቲያናዊ ጋብቻ ምስጢር፣ ልጆችን የመውለድና የማሳደግ ኃላፊነት…
መንፈሳዊ ሀብቶች በድምፅና በምስል የሚሰበሰቡበት ክፍል ሲሆን በአማርኛ የተጻፉ መንፈሳዊ መጻሕፍትን፣ ጸሎቶችን…ማየትም ሆነ በድምፅ ለመስማት ይችላሉ።
ነጻነት ማለት የፈለግነውን ማድረግ የመቻል መብት ማለት ሳይሆን፤ ማድረግ የሚገባንን ማድረግ የመቻል መብት ነው።
የምንሆነው የምንወደውን ነገር ነው፤ ተራ ነገር ካፈቀርን ተራ እንሆናለን፤ ከፍ ያለ ነገር ካፈቀርን ግን ከፍ እንላለን።
ቤተ ክርስቲያን ዝምተኛ ከሆነች ነገሮች የበለጠ እየተበላሹ ነው ማለት ነው።
መላእክት በሰው መቅናት የሚችሉ ቢሆን ኖሮ በአንድ ነገር ይቀኑ ነበር፡- በቅዱስ ቁርባን!!!
ሰላምን የምትሻ ከሆነ ሌሎች ሰዎችን ሳይሆን ራስህን ለውጥ፤ እግርህን ከሚጎዱ ነገሮች ለመከላከል ምድርን በሙሉ በቆዳ ከመሸፈን ለራስህ ብቻ ጫማ ማጥለቁ ይቀላል።
በመንበረ ታቦት (ቅዱስ ቁርባን) ፊት ስትሆን ኢየሱስ ከ2 ሺህ ዓመታት ጀምሮ የአንተን መምጣት እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውስ።
ኢየሱስ ሆይ! እሆን ዘንድ የምትፈልገውን ዓይነት ሰው መሆን እንድችል ሕይወቴን እንዳላወሳስብ እርዳኝ።
አምላኬ ሆይ! ልክ ሌላ የተፈጠረ ሰው የሌለ እስኪመስል ድረስ እያንዳንዳችንን ትንከባከባለህ፤ እያንዳንዳችንንም እንደምትንከባከበን ሁሉ ደግሞ ሁላችንን ትጠብቃለህ!
ክፍል ሦስት (ትምህርት ሃያ ሰባት) - የነቢያት መጽሐፍት ጥናት ትንቢተ…
Read Moreበአዲስ ኪዳን ውስጥ ተፈጻሚነት ያገኙ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች የክርስቶስ ልደት…
Read Moreገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን
ፖ.ሳ.ቁ. 21902
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
Phone: +251 (116) 461-435
Fax +251 (116) 458-988
1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም
2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም
3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን
በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።
"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።
“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።
ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት