Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የሲታውያን መነኮሳትን አበረታቱ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የሲታውያን መነኮሳትን አበረታቱ

padre mauro lepori papa francesco.jpegርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የሲታውያን መነኮሳት የሚሰጡትን የወንድማማች ኅብረት እና የምንኲስና ድህነት ምሥክርነት አበረታቱ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለጠቅላላ ጉባዔ በሮማ ከተሰበሰቡት የማኅበረ ሲታውያን መነኮሳት ጋር ሲገናኙ የሲታውያን መነኮሳን   በሚኖሩት የወንደማማችነት ማኅበራዊ ኑሮ እና በሚሰጧቸው የስብከት ወንጌል አገልግሎቶች ውስጥ ኢየሱስን መፈልግ እና መከተል ያለውን ሚና በአጽኖት ገልጸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም ከተማ መደበኛ ዓመታዊ ጉባዔያቸውን እያደረጉ ከሚገኙት ከሲታውያን መነኮሳን ጋር በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ጽኅፈት ቤት ውስጥ በቅዱስ ቀሌምንጢኖስ አዳራሽ በተገናኙበት ወቅት ባሰሙት ቃለ ምዕዳን የሲታውያን መነኮሳን በእምነት ጉዟቸው ኢየሱስን በመከተል“ከእርሱ ጋር ለመሆን፣ እርሱን ለመስማት፣ እርሱን ለማሰላሰል" በወንድማማች ኅብረት በጋራ እንዲጓዙ አበረታተዋቸዋል።  ይህ ጉዞ እያንዳንዱ መነኩሴ በራሱ ፍጥነት የሚያደርገው ጉዞ ሲሆን፣ በዚህም እያንዳንዱ መነኩሴ የራሱ የሆነ ልዩ እና የማይደገም የእምነት ጉዞ ታሪክ ያለው ሲሆን፣ ነገር ግን በማኅበር መካከል፣ ከማኅበር ጋር አስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሁል ጊዜ ከኢየሱስ ጋር አብረው እንደነበሩ እና አብረውት እንደሚሄዱ እንዲሁ መነኮሳን ይህንን አብነት እንዲከተሉ ጋብዘዋል። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ አክለውም ሐዋርያት ራሳቸውን አልመረጡም ነገር ግን በጌታ ተመርጠዋል፤ ይሁንና ከልዩነታቸው፣ ከድክመታቸው እና ከመታብያቸው የተነሳ እርስ በእርስ መግባባት ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም በማለት የማኅበር ሕይወት ያለውን መልክ አስታውሰዋል።

ር.ሊ.ጳ. በመቀጠልም እኛም እንደዚያ ነን በማለት የጌታ ሐዋርያት መካከል የነበረው ሰባዓዊ እውነታ ዛሬም በእኛ መካከል እንደሚገኝ እና አንዳንድ ጊዜ ጌታን በመከተል የጥሪ ጉዞ በጋራ ለመጓዝ አስቸጋሪ የሚሆኑባቸው ጊዜአት መኖራቸውን ጠቁመዋል። በተመሳሳይ ጊዜ ይህ የገዳም የወንድማማቾች ኅብረት ስጦታ ዘወትር የሚያስደንቀን ቁም ነገር ነው፤ ምንም እንኳን እኛ ፍፁማን ባንሆንም፣ ሁላችንም የተለያየ ማንነት ባለቤት ሆነን ሳለን በወንድማማችነት ሱታፌ ጌታን በመከተልየደቀ መዝሙርነት ሕይወት በጋራ የተጠራን ነን።

ሌሎችን የሚቀበል እና በቤተክርስቲያን ሕይወት በጋራ የሚጓዝ ኅብረት

WhatsApp-Bild-2022-11-19-um-112702ር.ሊ.ጳ. “ለኢየሱስ ክርስቶስ የምሰጠውን የጋራ ምሥክርነት” ሲገልጹ ይህ ሌሎችን ለመቀበል ክፍት የሆነ እና ወደ ዓለም የሚወጣ በማያቋርጥ የመለወጥ እና የመንፈሳዊ ብስለት የታጀበ የጋራ ምሥክርነት መሆኑን አመላክተዋል።   ይህም ለግለሰብ ክርስትያናዊ ሕይወት ብቻ የሚሰራ መርህ ሳይሆን በማኅበር ለሚኖሩ መነኮሳንም የሚሆን ጥሪ በመሆኑ ማኅበር ወደ ራሱ ብቻ የሚመለከት በገዛ ማንነቱ ላይ የተዘጋ ተቁም ሳይሆን፣ ይልቁንም “ ወደ ዓለም የሚወጣ ፣ እንግዳ ተቀባይ እና የወንጌል ልኡክ” መሆን ይገባዋል በማለት አስተምረዋል።  ይህም “የሥጦታዎች ባለቤት እና የመስራቾችን መንፈስ አነሳስቶ ልዩ ልዩ ማኅበራትን የተከለውን” የመንፈስ ቅዱስን ሕያው ተግባር የሚመሰክር ቁም ነገር ነው። ይህ በተግባር እንዲገለጥ በአንዲት ቤተ ክርስትያን ልብ በፍቅር እያሰብን በጋራ እንድንጓዝ ያስፈልገናል በማለት አሳስበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ አባታዊ ምክራቸውን በመቀጠል አንድነት ለለውጥ እና ለተሃደሶ  ክፍት በሆነ  ማንነት ውስጥ የሚያብብ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መሆኑን አስገንዝበው ሳይለወጡ ኅብረት የለም በማለት የመለወጥን አስፈላጊነት አሳስበዋል። ይህ የማያቋርጥ ለውጥ በግለሰብም ሆነ በማኅበር ሕይወት ውስጥ አስፈላጊ እና መሰረታዊ የሆነ የክርስቶስ መስቀል ፍሬ እና የመንፈስ ቅዱስ ሕያው ተግባር ውጤት እንደሆነ ገልጸዋል።

ብዝሃነትን  የሚንከባከብ  የተልዕኮ  ሕይወት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት  በተጨማሪም የሲታውያን መነኮሳን እና መነኮሳት እርስ በእርሱ ተመጋጋቢ በሆነ ጤናማ  ትስስር በእስያ፣ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ አባላት መካከል ካለውን የባህል ልዩነት ባሻገር ራሳቸውን ለወንጌል ተልዕኮ ሥራ ክፍት በማድረጋቸው ር.ሊ.ጳ. አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ዛሬ ብዝሃነትን የመንከባከብ ጥሪ ለጊዜው ምልክት ልንሰጠው የሚገባ ወሳኝ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የገለጹት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ፣ አያይዘውም መነኮሳን በተመስጦ ሕይወት ጥሪያቸው ውስጥ እንዲህ ያለውን ወርቀ ዘቦ የሆነ የጸጋ ጉብኝት በተለያየ ደረጃ እንደሚካፈሉ አስታውሰው፣ በውስጣዊ ማንነታችን፣ በጸሎት እና በመንፈሳዊ ተመስጦ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በሚደረግ የልብ ለልብ ውይይት መነኮሳን ብዝሃነትን በጥልቅ የሚለማመዱ በመሆናቸው በዚህ ረገድ ለዓለም የሚያበረክቱት ምሥክርነት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው ተናግረዋል። ይህም በጤናማ ተመጋጋቢ ኅብረት የሚገለጥ እጅግ ጥልቅ በሆነ እና ዘወትር አዳዲስ ነገሮችን በሚያፈልቅ ስምረት የሚታይ መሆኑን ር.ሊ.ጳ. አመላክተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቃለ ምዕዳናቸው ማሳረጊያ፣ የሲታውያን መነኮሳን ለጌታ የበለጠ ተደራሽ ይሆኑ ዘንድ፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ድህነትን የበለጠ እንዲያዘወትሩ ዐደራ ብለዋል። ከዚሁ ጋር አያይዘውም የሲታውያን መነኮሳን በሚሰጡት ዘርፈ ብዙ አገልግሎታቸው ውስጥ ዘወትር ሕያው ተስፋ ኖሯቸው እንዲጓዙ በመጋበዝ ቃለ ምዕዳናቸውን አሳርገዋል።

ሴሞ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።