እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel
Display # 
< < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < < <
Title Author Hits
የመንፈስ ፍላጐቶች Written by Super User 4872
የልብ ድኽነት Written by Super User 7409
ለንጽሕና የሚደረግ ተጋድሎ Written by Super User 3582
የልብ ንጽሕና Written by Super User 3319
ዘጠነኛይቱ ትእዛዝ - የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፣ የባልንጀራህን ሚስት፣ ሌሎችንም፣ ገረዱንም፣ በሬውንም፣ አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ Written by Super User 3738
የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት Written by Super User 2787
በእውነት ላይ የሚቃጡ በደሎች Written by Super User 2897
ስምንተኛይቱ ትእዛዝ - በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር Written by Super User 5074
የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት Written by Super User 2889
የሌሎችን ሃብቶች ማክበር Written by Super User 2766
ሰባተኛይቱ ትእዛዝ - አትስረቅ Written by Super User 3944
በጋብቻ ክብር ላይ የሚፈጸሙ በደሎች Written by Super User 4586
ልጅ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለመሆኑ Written by Super User 5110
የባልና ሚስት ፍቅርና መተማመን Written by Super User 15604
ራስን መስጠትና 3 ዓይነት ንጽሐ ድንግልና Written by Super User 7530
6 - አታመንዝር Written by Super User 5164
ሰላምን መጠበቅና ጦርነትን ማስወገድ Written by Super User 5139
ለሙታን ስለሚገባ ክብር Written by Super User 4845
ራስን ስለማጥፋትና በማይድን በሽታ ስለሚሰቃዩ ሰዎች ግድያ Written by Super User 14611
ሆንብሎ የሚፈጸም ግድያና ጽንስ ማስወረድ Written by Super User 5704
5 አትግደል Written by Super User 5538
ባለሥልጣናትና የዜጎች ግዴታ Written by Super User 4222
የቤተሰብ አባላት ኃላፊነቶች (ልጆችና ወላጆች) Written by Super User 5032
ቤተሰብና ሕብረተሰብ Written by Super User 3140
4. አባትና እናትህን አክብር Written by Super User 4554
ሦስተኛይቱ ትዕዛዝ Written by Super User 4401
ሁለተኛይቱ ትእዛዝ Written by Super User 3245

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት