7. ጤነኛ በራስ መተማመን
- Category: መጽሐፍ ቅዱስ
- Published: Sunday, 30 May 2021 12:15
- Written by Super User
- Hits: 2292
- 30 May
7. ጤነኛ በራስ መተማመን
“ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። እኔም። ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ። ወደምሰድድህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና። ብላቴና ነኝ አትበል።" ኤርምያሰ 1፡5-10፡፡
ኤርምያስ መናገር አልችልም ብሎ ደካማነቱን ከማወቁ የተነሣ በቅንነት ሲናገር የእግዚአብሔር መልስ ግን በኤርምያስ መተማመንን የያዘ ነበር፡፡ እኛ ስለእራሳችን የምናውቀውና እግዚአብሔር ስለኛ የሚያውቀው ምን ያህል የተራራቀ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
በተጨማሪም በእኛ ዘንድ ደካማነት ሆኖ የሚታየው ለእግዚአብሔር ግን ቁጥር ውስጥ የማይገባና የማያሳስብ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ጤነኛ በራስ መተማመን በእግዚአብሔር ፈት ከመቆም የሚመነጭ ነው፡፡ በራስ መተማመኔ የደከመ መስሎ ሲሰማኝ፣ ቀና ብዬ ለመሄድ ድፍረቱ ሲጎድለኝ ያደረግሁት ነገር ምን ነበር? ምን ዓይነት ዝንባሌ በውስጤ ሲቀሰቀስ ተሰማኝ?
ጤነኛ በራስ የመተማመን ስሜትስ ላይ እንዴት ልመለስ ቻልኩ?
በአባ ዳዊት ውብሸት
በድምፅ ለማዳመጥ ከታች ማጫወቻውን ይጫኑ (ንባብ በዘማሪት ሕይወት መልአኩ)