ቅድስት ማሪያ ጐሬቲ
- Category: አጫጭር ገድለ ቅዱሳን
- Published: Friday, 13 April 2012 10:30
- Written by Super User
- Hits: 9954
- 13 Apr
ቅድስት ማሪያ ጐሬቲ
የማርያ ጐሬቲን የሚመስል የወጣት ሴት ታሪክ ብዙ ጊዜ የሚገኝ ዓይነት አይደለም፤ ሊደፍራት ከሞከረው ሰው ጥቃት ራሷን በመጠበቅ ሰለ ንጽህና የታገለችው ትግል፣ በትግሉ ከፍተኛነት ለሞት ስትቃረብ እስትንፋሷ ከመቆሙ በፊት ለሰውየው ይቅርታ ማድረጓ ታሪኳን የተለየ እና ኃይል ያለው ያደርገዋል፡፡
እርሷ በተወለደችበት ወቅት ለመሬት ከበርቴው የሚከፈለው የጉልት ገቢ መጠኑ የሚቀመስ ባለመሆኑ ቤተሰቧ የመኖርያ ስፍራውን ለመልቀቅ ተገደዱ፡፡ የመኖርያ አካባቢውን በቀየሩ በሁለተኛው ዓመት፣ የቤተሰቡ ሦስተኛ ልጅ ማርያ አስር ዓመት ሲሞላት ወላጅ አባቷ አረፈ፡፡ እናቷ በመስክ ስራ ላይ ረጅም ሰዓት ተጠምዳ ስለምትውል ማርያ ታናናሾቿን በመጠበቅ እና በመንከባከብ ጊዜዋን ታሳለፍ ነበር፡፡
ምንም እንኳን መሠረታዊ ትምህርት ለመቅሰም ባትታደልም በራሷ ፍላጐት ወደ ከተማ እየሄደች ለመጀመሪያ ቁርባን ለምታደርገው ዝግጅት የሚጠቅሟትን አዳንዳንድ ትምህርቶች ትወስድ ነበር፡፡ ግንቦት 19ዐ2 እ.ኤ.አ ሕይወቷ እስካለፈበት ድረስ በጊዜው ብዙም ባልተለመደበት ወቅት ዘወትር በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባን ትቀበል ነበር፡፡ /እንደ ዛሬው ቅዱስ ቁርባን በየዕለቱ አይገኝም ነበርና/ ቤተሰቧን ያስጠጉላት ባለጠጋ ቤተሰቦች ወንድ ልጅ አሌሳንድሮ በመጀመሪያ እንደ መልካም ወንድም ቢቀርባትም እያደር ግን ንጽህናዋን የሚያጐድፍ ወሲባዊ ትንኮሳን ያደርግባትና ለማንም የተናገረች እንደሆነ እንደሚገድላት ያስጠነቅቃት ገባ፡፡
እ.ኤ.አ ግንቦት 5 ቀን አሌሳንድሮ ከመስክ ውሎ ወደ ቤት ሲመለስ ጐረቤቱ ማርያ በቤቷ ውስጥ ለብቻዋ እንደሆነች አወቀ፡፡ ይህንን የክፋት አጋጣሚ መጠቀም የፈለገው ወጣቱ በመድሃኒት /ባሕላዊ/ ካሰከራት በኋላ ሊደፍራት ቢታገልም ማርያ ስለ ንጽሕናዋ ጉዳይ ቸል የምትል የዋዛ አልነበረችም፡፡
ሴት ልጅ ስለታገለችው ክብሩ የተነካ የመሰለው ወጣቱ አሌሳንድሮ በአካባቢው ባገኘው ነገር የማርያን ግንባር ተረተረው፡፡ ማርያ ወለሉ ላይ ተዘረጋች፣ በደም ተለወሰች ምንም እንኳን ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም በቁስሉ ትልቅነት የተነሳ በቀጣዩ ቀን ወደ ጌታዋ ደስታ ለመካፈል ሄደች፡፡ እስትንፋሷ ከማረጉ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ቅድስ ቁርባን ስትቀበል "ስለ ክርስቶስ ፍቅር" ስትል እግዚአብሔርን እንዲሁ እንደሚያደርግላት ተስፋ በማድረግ ለአሌሳንድሮ ይቅርታ እንዳደረገችለት ተናገረች፡፡ ከዚህ በኋላ ምንም ሳትናገር አሸለበት፡፡ ወጣቱ አሌሳንድሮ ዕድሜው ለሞት ቅጣት ገና ነበርና 3ዐ ዓመታት ወህኒ ቤት ውስጥ አሳልፏል በወህኒ ቤት ሣለ ማርያ በህልሙ እየመጣች ታነጋግረው ነበር፡፡ በ1929 ብፅዕናዋን ለማወጅ ሲደረግ ወጣቱ ከእስር ነፃ በሆነበት ጊዜ ማርያ በህልም እንዳነጋገረችው እና ከእንግዲህ ወዲህ ለነፍሱ ብቻ እንዲያስብ እና እንዲህ ያለውን እኩይ ተግባር እንዳይደግም እንደለመነችው መሰክሯል፡፡ ማርያ በ1947 ብፅዕናዋ ከታወጀ በኋላ በ195ዐ በርካታ ተዓምራት በስሟ በመመዝገቡ ቅድስናዋ ታውጇል፡፡ መርያ ሕይወቷን ሳይቀር ሰውራ ነፍሷን ለዘለዓለም አግኝታለች፡፡