Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የጸሎት ጥሪ

c13522529ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ለቤኔዲክት 16ኛ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ!

በመደበኛ የረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ መዝጊያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የቀድሞው ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክት 16ኛ “በጠና ስለታመመው ልዩ ጸሎት” እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት ዳይሬክተር በጤናቸው ላይ መባባስ መኖሩን ቢያረጋግጡም ሁኔታው ግን የተረጋጋ መሆኑን ተናግሯል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ሁላችሁም በጽሞና ጸሎት ቤተክርስቲያንን ለሚደግፉት ለር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክት ልዩ ጸሎት እንድታደርሱ እጠይቃለሁ። በጠና ታመዋልና በጸሎታችሁ አስቧቸው! ጌታ እስከ መጨረሻው ድረስ በዚህ የቤተክርስቲያን የፍቅር ምስክርነት እንዲደግፋቸው እና እንዲያጽናናቸው ጸልዩላቸው” በማለት በ95 ዓመቱ የቀድሞ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ የመጨረሻ ምድራዊ ንግደት ልዩ ጸሎት እንዲያደርጉ ምእመናንን ሁሉ ጋብዘዋል።

የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ማትዮ ብሩኒ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ፣ “ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ በጤናቸው ላይ የደረሰው ችግር ተባብሷል” ሲሉ አረጋግጠዋል። አክለውም "በአሁኑ ጊዜ ሁኔታው ​​በቁጥጥር ስር ነው" ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ በገዳማቸው ቅርብ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ የረቡዕ መደበኛ የትምህርተ ክርስቶስ መርሐ ግብር ካጠናቀቁ በኋላ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ወደሚገኙበት በቫቲካን ቅጥር ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የቤተ ክርስትያን እናት ቅድስት ማርያም ገዳም በመሄድ ጎብኝተዋቸዋል።

ለር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ የመጨረሻ ሰዓታት የሚደረግ ጸሎት

እንጸልይ!

ሁሉን ቻይ እና ዘላለማዊ አምላክ ሆይ

በአንተ ለሚያምኑት ሁሉ ዘላለማዊ ጤንነታቸው አንተ ነህ

ስለ አገልጋይህ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ የምናቀርብልህን ጸሎት ተቀበል

በሚያጽናናው ምሕረትህ ትጎበኛቸው ዘንድ ፈቃድህ ይሁን ብለን

በልጅህ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንለምንሃለን

አሜን!

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።