ቤተሰብና ሕብረተሰብ

ቤተሰብና ሕብረተሰብ

ቤተሰብ የማህበራዊ ህይወት መሠረታዊው ኅዋስ ነው፡፡ ቤተሰብ ባልና ሚስት በፍቅርና በህይወት ስጦታ ራሳቸውን እንዲሰጡ የተጠሩበት ተፈጥሮአዊ ሕብረተሰብ ነው፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የሚጀመሩት፤ ኃላፊነትን የመሸከም ሥልጣን፣ ጽኑ አቋምና የግንኙነት ሕይወት በሕብረተሰብ ውስጥ የነፃነት፣ የዋስትና የወንድማማችነትን መሠረት ይጥላል፡፡ ቤተሰብ፤ ሰው ከሕፃንነት ጀምሮ የሥነ መግባርን ጥቅም የሚማርበት፣ እግዚብሔርን የሚያከብርበትን ነፃነትን በመልካም ተግባር ላይ የሚያውልበት ማሕበር ነው፡፡ ቤተሰባዊ ሕይወት ወደ ማሕበራዊ ሕይወት መሸጋገሪያ ነው፡፡

ቤተሰብ አባላት በችግር ላይ የሚገኙ ወጣቶችን፣ አረጋውያንን፣ ሕሙማንን፣ አካለ ስንኩሎችንና ድሆችን የመርዳት ኃላፊነት ለመቀበል የሚማሩበትን አርአያነት ያለውን ሕይወት መኖር አለበት፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ምክንያት ይህን እርዳታ ማበርከት የማይቻላቸው ቤተሰቦች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም እነዚህን ችግሮኞች በድጐማ መልክ መርዳት ሌሎች ሰዎችን፣ ቤተሰቦችንና ኅብረተሰቦችን ይመለከታል፡፡ “ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ድሀ አደጐችን መበለቶችን በመከራቸው መጠየቅ፣ በዓለምም ላለመቆሸሽ ራስን መጠበቅ ነው” ያዕ. 1፡12

ቤተሰብ ተገቢ በሆነ ማሕበራዊ እርምጃዎች ድጋፍና ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ቤተሰቦች ኃላፊነታቸውን መወጣት የሚያቅታቸው ጊዜ ሌሎች ማሕበራዊ አካላት የቤተሰብን ተቋም የመርዳትና የመደገፍ ግዴታ አለባቸው፡፡ ታላላቅ ማሕበረሰባት የድጐማን መመሪያ ሽፋን በማድረግ አለአግባብ በቤተሰቦች መብት ከመጠቀም ወይም በእነርሱ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ አለባቸው፡፡

ቤተሰብ የሕብረተሰብ ሕይወትና ደህንነትን የማጐልበት ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ ሕብረተሰብ ጋብቻንና ቤተሰበን የመደገፍና የማጠናከር ዓይነተኛ ኃላፊነት አለበት፡፡ ማንግስት “የጋብቻንና የቤተሰብን እውነተኛ ባሕርይ ለይቶ የማወቅና የመጠበቅ፣ የማሳደግ፣ የሕዝበን ግብረገብነት የመንከባከብ፣ የቤተሰብን ብልጽግና ከፍ የማድረግ” ታላቅ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡

ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ቤተሰብን የማክበር፣ የመርዳት በተለይም ከዚህ በታች የተመለከቱንት ጉዳዮች የማሟላትና የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡

አራተኛው ትእዛዝ በሕብረተሰብ ውስጥ ያሉ ሌሎች ግንኙነቶችን ያብራራል፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስንመለከት የወላጆቻችንን ልጆች እናያለን፡፡ የአጐቶቻችንንና የአክስቶቻችንን ልጆች ስንመለከት የአያቶቻችንን የልጅ ልጆች እናያለን፤ ዜጐች ወንድሞቻችንን ሰንመለከት የአገራችንን ልጆች እናያለን፣ የተጠመቁትን ባየን ጊዜ ደግሞ የእናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ልጆችን እናስተውላለን፡፡ ማንኛውንም ሰው ስናይ ደግሞ “አባታችን ሆይ!” ተብሎ መጠራት የሚሻውን የእርሱን ወንድ ወይም ሴት ልጅ እንመለከታለን፡፡ በዚህም መሠረት ከባልንጀሮቻችን ጋር ያሉን ግንኙነቶች በባሕርይአቸው ግላዊ ናቸው፡፡ ባለንጀራ በሕዝብ ጥርቅም መካከል የሚገኝ “ነጠላ” አይደለም፡፡ እሱ ተለይቶ በሚታወቅባቸው መገኛዎቹ አማካይነት ልዩ ጥንቃቄ ከበሬታ የሚገባው “አንቱ” የተሰኘ ነው፡፡

የሰብአዊ ማኅበራት መሠረት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱን በተገቢው መንገድ ማስተዳደር፣ መብቶችን በማረጋገጥና ውልን የመሳሰሉ ግዴታዎችን በመስፈጸም ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በአሠሪዎችና ሠራተኞች፣ በአስተዳዳሪዎችና በዜጐች መካከል ያሉ ትክከለኛ ግንኙነቶች ፍትሕንና ወንድማማችነትን አስመልክቶ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር ጋር የሚሄድ የተፈጥሮ መልካም ፈቃድን ይጠይቃሉ፡፡