ግንቦት 19 ቀን 2004 - እጆቹን አንስቶ ባረካቸው የዕርገት በዓል ይሁንልን

ግንቦት 19 ቀን 2004 - እጆቹን አንስቶ ባረካቸው የዕርገት በዓል ይሁንልን

ሮሜ 1ዐ፡1-13 1ጴጥ 3፡13-22 ሉቃስ 24፡ 45-53

ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ አምስት ኪ.ሜ ርቆ ከደብረዘይት ወዲያ የሚገኝ መንደር የማርያም፣ የማርታና የአልአዛር እንዲሁም የለምጻሙ የስምኦን መኖሪያ የነበረና ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ የሚገኝ መንደር ነው ቢታንያ የስሙም ትርጓሜ የበለስ ቤት ማለት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ሐዋርያቱን ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ አግኝቷቸው በመካከላቸው በመሆን ከእነሱ ጋር በሕይወት እያለ በነብያት በሙሴ ሕግና በመዝሙራት ስለእርሱ ይነገር የበረውን እናም እርሱ የነገራቸውን ሁሉ አእምሯቸውን ከፍቶላቸው እንዲያስተውሉ አድርጓቸው ነበር፡፡ ቃሉን የሚያከብር አምላክ ቃሉን ጠብቆ የራሱን ቃል አከበረው ስለራሱ የተነገሩትን ሁሉ ደግሞ ደጋግሞ አደረገው ሰዎች ነንና ያየነውን የሰማነውን ለማመን እንቸገራለን ግን ለምን? ማመን ለምን ይሳነናል? በእርግጥ የእግዚአብሔር ድንቀ ስራዎች ከሰዎች እምነት በላይ ድንቅ ነው፡፡ ስለዚህ ይመስላል ሰዎች አድራጊው አምላክ የሚያደርጋቸው ድንቅ ነገሮች በሰው ልጅ አእምሮ ሊገመት የሚችል ባለመሆኑ ማመን ያዳግተናል ምንም እንኳን የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አምሳያ የተፈጠረ ቢሆንም አእምሮ ግን የሰው ልጅ ይለያል፡፡ ስለዚህ ቀድሞ ሐዋርያቶች በዓይናቸው እንዳዩት ሁሉ ዛሬም እኛ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እያየን ስለሆነ አምነን ስንቀበል በተግባር ስንፈጽመው ጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቶቹን እጆቹን አንስቶ ባርኳቸው ወደ ሰማይ እንዳረገ ሁሉ እኛንም በመጨረሻው ወቅት ይባርከናል፡፡

• ምንባቡ ስለምን ይናገራል?

• በእምነታችን ምን ያህል ጠንካሮች ነን?

• በእምነታችን ጠንካሮች ለመሆን ምን ማድረግ ይገባናል?