ግንቦት 12 ቀን /2004 ዓ.ም - "ከነዚህ ይልቅ ትወደኛለህ?"

ግንቦት 12 ቀን /2004 ዓ.ም -  "ከነዚህ ይልቅ ትወደኛለህ?"

ሮሜ 6፡1-14 1ጴጥ 4 ፡1-11 ዮሐ 21፡12-25

የምህረት አምላክ የእግዚአብሔር የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስ በፀጋው የሚመራን የመንፈስ ቅዱስ ሰላም እና ጥበቃ ይብዛልን፡፡ከዚህ ከጳዉሎስ መልዕክት የምንረዳዉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐጢያት ነፃ በማዉጣት ክፉን በማሸንፍ፣ ሕይወት የሰጠ እርሱ ነዉ፡፡በመንፈስ ቅዱስ ህይወት እንድናገኝ ሙሉ እምነት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፤ምንባቦች እንድናስብ ይጋብዘናል፡፡ ከክርስቶስ ጋር ያለን ህብረት ያመለክተናል፡፡ ጥምቀት የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ተካፋይ እንደሆንንና በትንሳኤዉም ተካፋይ መሆናችንን ያመለክታል፡፡ ሐዋርያዉ ጴጥሮስ እንደ ስጋ ፍቃዳችን ሳይሆን በእግዚአብሔር ፍቃድ ዉስጥ እንድንመላለስ ይጋብዘናል፡፡ህብረታችን ፣ኑሯችን፣ ሁለንተናችንን ህይወትን በሰጠን በክርስቶስ ኢየሱስ እንዲመራ እና መገዛታችን ለክፋት እንዳይሆን ያስገነዝበናል፡፡በዮሐ. 21-15 ጀምሮ የእግዚአብሔርን ቃል ስናነብ ጴጥሮስ በክርሰቶስ ኢየሱስ የወንጌል አምባሳደር ሆኖ ሲገኝም እንመለከታለን፡፡በክርስትና ህይወት ዉስጥ ክርስቶስ ህይወታችንን እንድንፈትሽ ይጋብዘናል፡፡ እንድንታመን የእሱ አገልጋይ እንድንሆንም እንጋበዛለን፡፡ ጴጥሮስ የቱንም ያህል ደካማ ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ግን ሀላፊነት ተሰጠዉ መንጋን የመጠበቅ፡፡ስለዚህ ከዚህ ቃል የምንረዳዉ ክፋትን በእረሱ በመታመን በማሸነፍ ፍቃዳችንን ለእርሱ በማስገዛት በእምነት ፀንተን ለሌሎች ምስክሮቹ እንድንሆን እንጋበዛለን፡፡እንዲሁም የእግ/ርን መመልከት በእርሱም ፍቃድ መመላለስ ለቅድስና የተጠራንበትን ህይወት እንድንኖር ብርታት ይሆነናል፡፡በመጨረሻ ቃሉን ለህይወታችን መመሪያ በማድረግ በፀሎት ክፋትን በማሸነፍ የተሻለዉን እና የሚበልጠዉን የእግ/ርን በረከት ለመቀበል እንድንችል መበርታት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ቃል የምንረዳዉ ክፋትን በእረሱ በመታመን በማሸነፍ ፍቃዳችንን ለእርሱ በማስገዛት በእምነት ፀንተን ለሌሎች ምስክሮቹ እንድንሆን እንጋበዛለን፡፡እንዲሁም የእግዚአብሔርን መመልከት በእርሱም ፍቃድ መመላለስ ለቅድስና የተጠራንበትን ህይወት እንድንኖር ብርታት ይሆነናል፡፡በመጨረም ቃሉን ለህይወታችን መመሪያ በማድረግ በፀሎት ክፋትን በማሸነፍ የተሻለዉን እና የሚበልጠዉን የእግ/ርን በረከት ለመቀበል እንድንችል መበርታት ያስፈልጋል፡፡

ምንባቡ ስለምን ያናገራል?

ሙሉ እምነት አለን? ሙሉ እምነት እንዲኖረን ምን ማድረግ አለብን ?