የብፁዕ አቡነ ኪዳነማርያም ጸሎተ ፍትሐት

 

የብፁዕ አቡነ ኪዳነማርያም ፀሎተ ፍትሐት ሐሙስ ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በ11፡30 በአዲስ አበባ ልደታ ማርያም (ካቴድራል) ቤተክርስቲያን ወዳጅ ቤተዘመዶቻቸው በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

 

የፍትሐት ሥነስርዓቱን የመሩት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሲሆኑ በሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ ብፁዕ ሊቀጳጳሳት ጆርጅ ፓኒኩለም በኢትዮጵያ የቅድስት መንበር ተወካይ፣ ክቡር አቶ ስዩም መስፍን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ሌሎች የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተወካዮች፣ ቤተዘመዶቻቸው፣ በርካታ ካህናት፣ ደናግልና ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

 

ብፁዕ ሊቀጳጳሳት ብርሃነየሱስ የብፁዕነታቸውን የህይወት ዘመን አገልግሎት የገለፁ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ተስፋሥላሴ የዓዲግራት ሀገረ ስብከት ጳጳስ ከብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ የተላከውን የሃዘን መግለጫ በንባብ አሰምተዋል፡፡

የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀብር ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2001 ዓ.ም. በአዲግራት እንደሚፈጸም ተገልጿል፡፡

 

 

 

 

 ብፁዕ አቡነ ኪዳነ ማርያም ባደረባቸው ህመም ከሁለት ዓመታት ላላነሰ ጊዜ በአዲስ አበባና በሮማ ከተማ ህክምና ሲደረግላቸው የቆየ መሆኑ ይታወሳል፡፡ 

 

 

 

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት

 ማህበራዊና ህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ