ግንቦት 5 2ዐዐ4 - መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉት

ግንቦት 5 2ዐዐ4 - መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉት

ሮሜ 4፡13-24  ራዕይ 2ዐ፡ 1-6 እና 11-15    ዮሐ 21፡ 1-41

ምህረት አምላክ የእግዚአብሔር የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስ በፀጋው የሚመራን የመንፈስ ቅዱስ ሰላም እና ጥበቃ ይብዛልን፡፡እግዚአብሔር ለአብርሃም ታላቅ ነገርን ያደረገለት በእርሱ ላይ ባለዉ እምነት ነዉ፡፡ ያም የገባለትን ቃልኪዳን ለመፈጸም የመሲሑን መምጣት በተስፋ መጠበቅ ያስፈልገውም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል አምላክ እንደሆነ በይስሐቅ መወለድ ማየት እንችላለን፡፡ዘፍ 17፡ 17-18 አብርሐም ከነበረዉ ችግሩ ይልቅ እግዚአብሔርና የተሰጠዉን ተስፋ ይመለከታል፡፡ የአብርሐም እምነት በይገባኛል የተሞላ ሳይሆን በተስፋ ሰጪዉ አምላክ ክብርን በመስጠት ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ሺ ዓመት መጨረሻ የሌለዉ ንግስና ያመለክታል፡፡ የክርስቶስን ዘላለማዊ ንጉስነት እንድንመለከተዉ ይጋብዘናል፡፡ በወንጌሉ ሐዋርያት የሰጣቸዉን የተስፋ ቃል በመዘንጋት ተስፋ ቆርጠዉ ወደነበሩበት ታሪካቸዉ መመለሳቸዉን እና ዳግም ክርስቶስ በህይወታቸዉ ተገልጦ ‹‹ ጌታ እኮ ነዉ›› በማለት አይነ ልቦናቸዉ እንደተገለጠ በቃሉ እናገኛለን፡፡

1. ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምረን በእኛ የጊዜ ቀመር ሳይሆን እንደፈቃዱ በታሪካችን ዉስጥ ያልነበረንን፡ ተስፋ የቆረጥንበትን በመፈፀም ታላቅ ነገርን በህይወታችን የሚያደርግ አምላክ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

2. ክርስቶስ አምላካችን ፍጹም አምላክ እንደሆነ ንግስናዉም መጨረሻ የሌለዉ ልዑል የሆነ አልፋ ኦሜጋ እንደሆነ መገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡

3. አይነ ልቦናችንን ከፍተን በቃሉ በመኖር ተስፋችንን ማለምለም ያስፈልጋል፡፡

ስለዚህ በእምነት መጽናት ፤በተስፋዉ ቃል መኖር እራሳችንን ኑሯችንን ለእርሱ መስጠት ስንችል እግዚአብሔር በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ታሪካችን ይገባል፡፡ ታላቅ ነገርን ያደርግልናል፡፡ በረከትና ዋጋዉን ያበዛል፣ ዘመናችን ልክ እንደ አብርሃም ይባረካል፡፡የበረከት አምላክ የበረከቱ ተካፈይ ያድርገን አሜን፡፡

• ምንባቡ ስለምን ይናገራል ?

• እኛስ ዘመናችንን እንዴት እናየዋለን ?