የአንጾኪያው ቅዱስ ኢግናጢዮስ

የአንጾኪያው ቅዱስ ኢግናጢዮስ

ቅዱስ ኢግናጢዮስኢግናጢዮስ ትውልዱ በሲርያ ሲሆን የሮማ ዜግነት እንደነበረው ይታመናል፡፡ በ69 ዓ.ም ገዳም ጳጳስ ሆኖ እስከተቀባበት ጊዜ ድስ ስለሕይወቱ ይህ ነው ተብሎ በግልፅ የሚታወቅ ነገር አልነበረውም፡፡ በዘመነ ጵጵስናውም ቢሆን የእርሱ ክርስትና ያስቆጣቸው ሰዎች በሮም ወታደሮች ጥበቃ ወደ ሮም እንደላኩት ከሚያስረዳው ታሪኩ ውጪ ሌላ ነገር አልነበረም አንዳንዶች ይህ ሰው የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር የነበረ በመሆኑ በሐዋርያት እና እነርሱን ተከትሎ ከመጣው ተውልድ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደነበረው ይጠቅሳሉ እርሱም ስለራሱ ሲናገር ‹‹ እኔ የእግዚአብሔር ኩሊ ወይም ተሸካሚ ነኝ›› ይል ነበር ስለርሱ በይበልጥ የታወቀው ሊገደል ወደ ሮም በመሄድ ላይ ሳለ "ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት" በጻፈው መልዕክቱ አማካይነት ነው፡፡ እነዚህ መልዕክቶች ለሮማው ጳጳስ ለፓሊካርፕ ካደረሱ በኋላ በእስያ ለሚገኙ አምስት አብያተ ክርስቲያናት፣ ኤፌሶን፣ ማኘስያ፣ ትራለስ፣ ፊላዴልፊያ እንዲሁም በሰሚናር ሁሉ ተሰራጭተዋል፡፡ ኢግነጢዮስ በነዚህ መልዕክቶች ውስጥ ክርስቲያኖች ለቤተክርስቲያን በመታዘዝ አንድነታቸውን እንዲጠብቁ በአጽኖት ገልፆላቸዋል እንዲሁም ቅዱስ ቁርባን የሰላም ምስጢር ሥለመሆኑ እና ከአሳሳች መምህራን ጋር ከመከራከር ራሳቸውን እንዲያርቁ መክሮአቸዋል፡፡ "በድብቅ እንደሚናከሱ እብድ ውሾች ናቸውና ሃሰተኞች መምህራን ራቁ" (ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን የላከው መልዕክት)

ኢየሱስ ክርስቶስ የነቢያት ሁሉ ፍፃሜ በመሆኑ ከእንግደህ ወዲህ በርሱ ትዕዛዛ እንጂ በአይሁዳውያን ባህል እንዳይመሩ በጥብቅ ከማሳሰቡም በላይ ቃል ለኛ ሲል ሰብዓዊ ባሕሪን ሳይቀር በመጋራት ከእኛ እንደ አንዱ መሆኑን ያስረዳቸው ነበር፡፡

"ከዳዊት ዘር የሆነው እርሱ ከማርያም ተወለደ፣ በእውነት የተወለደ ነው፣ እንደ ሰው የሚበላ እና የሚጠጣ፣ በጴንጢናዊው ጲላጦስ ለሞት ተላልፎ የተሰጠ፣ በእውነት የተሰቀለ እና ስለ እኛ የሞተ እናም በእውነት ሞትን ድል አድርጐ የተነሣ ነው" /ለትራሚያን ቤተክርስቲያን የላከው መልዕክት/ ቅዱስ ኢግነጢዮስ ለሮማውያን በድፍረት ለሰማዕትነት ለምትሆን ሞት ዝግጁ መሆኑን ገለጸላቸው፣ "በአረመኔዎች እጅ ልውደቅ እነርሱ ይገድሉኛል እኔ ግን እግዚአብሔርን አገኘዋለሁ፣ እኔ የእግዚአብሔር የስንዴ ቅንጣት ነኝ፣ በአረመኔዎች መንጋጋ በታኘክሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር ምርጥ ሕብስት ሆኜ እቀርባለሁ"

በደብዳቤዎቹ ውስጥ የጥንት ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ላይ ያለችውን ነገረ-መለኮታዊ አመለካከት አንጸባርቋል፣ ይህም በአካላዊ መንገድ ጭምር ለመሠቃየት በክርስቶስ ሕማም ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ ከርሱ ጋር ያለንን አንድነት ማጠናከር ብቻ ሳይሆን መከራንና ሞትን ሳይቀር በክርስቲያናዊ ደስታ የመቀበል አመለካከትን ማዳበር ነው፡፡ ከታሪኩ እንደምንረዳው የሮም ክርስቲያኖች ተሠባስበው ከተፈረደበት ሞት ሊያድኑት ወደ እርሱ ቢመጡም ወደ እግዚአብሔር ለመሄድ በተነሳበት መንገድ ላይ እንቅፋት ሆነው እንዳይቆሙ ነገራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ሞተ፡፡ "የኢግነጢዮስ የሰማይ ቤት ልደት" በማለት በጥቅምት 17 ቀን በአንጾኪያ ይከበራለ፡፡ በቤተክርስቲያን የሥነ ሥዕል ጥበብ የአንጾኪያው ቅዱስ ኢግነጢዮስ ሙሉ የጳጳስ ልብስ ለብሶ ይቀርባል፣ ይህ ዓይነት ምስል በቅድስት ሶፍያ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን እና በካርትሬስ በሚገኙ ቅርፃቅርፆች ላይ ይስተዋላል፡፡ አንዳንዱ ጊዜ ልቡን በግራ እጁ ደግፎ እንደያዘ ሆኖ ሲቀርብ በሌላ ጊዜ ደግሞ ለክርስቶስ ሰብዓዊነት ያለውን እምነት ለማሳየት ልቡ ከተፈጥሮ ቦታዎች ውጪ ሆና "ኢየሱስ" የሚለው ሥም ተፅፎባት ይቀርባል፡፡