ሚያዚያ 21ቀን /2004 ዓ.ም - ከማመን ልባቹህ የዘገየ.....

ሚያዚያ 21ቀን /2004 ዓ.ም - ከማመን ልባቹህ የዘገየ.....

2ቆሮ 5፡11-21 ጴጥ 3 ፡14-18 ሉቃ 24፡13-35

መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር በሕይወት ያሉ ሁሉ ስለ እነርሱ የሞተው እና ከሞትም ለተነሳው እንዲኖሩ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ ለራሳቸው ሲሉ እንዳይኖሩ ክርስቶስ ለሁሉም ሞተ ይላል፡፡(2ቆር 5፡15)ቅዱስ ጳውሎስ ራሱን ጨምሮ ክርስቶስ ሰለ ሰው ልጅ ፍቅር በመስቀል ላይ እንደሞተ ያውቅ ነበር፡፡በመንፈስ ሙታን የሆኑ ሰዎች ሕያው ሊሆኑ የሚችሉ በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ በማመን ብቻ ነው፡፡ምንም እንኳን ይህ መልዕክት የሞኝ ተረት ቢመስልም ለሰው ልጆች ብቸኛው ተስፋ ነው፡፡ቅዱስ ጳውሎስ በድፍረት መስበኩን የቀጠለው ሥለዚህ ተስፋ ሲል ነው፡፡ እርሱ ሰዎችን የተመለከተው በሥጋ ዐይኑ አማካኝነት በጎሳቸው፣በቋንቋቸው፣በኢኮኖሚ ደረጃቸው አልነበረም ነገር ግን ጳውሎስ ሰዎችን የተመለከተው በክርስቶስ ወንጌል አማካኝነት አዲስ ፍጥረት ከመሆናቸው ወይም ለወንጌል ካላቸው የደነደነ ልብ አሮጌ ፍጥረት ከመሆናቸው አንፃር ብቻ ነው፡፡ አንድ ግለሰብ በእግዚአብሔር (በአብ ፣በወልድ፣በመንፈስ ቅዱስ )በማመኑ በውስጡ የተለወጠ አዲስ ፍጥረት ይሆናል፣አስተሳሰቡና አሰራሩ ሁሉ ይለወጣል፡፡ለዚህ ወንጌል ወደ ኤማሁስ ሲጓዙ የነበሩ ደቀመዛሙርት ምስኪን ደሃ መስሎ ከቀረባቸው ከክርስቶስ ጋር እንደተገናኙ እናያለን፡፡እነርሱም ክርስቶስን ካገኙት እና በመዓድ አብሮአቸው ከተቀመጠ በኋላ ያገኙትን ደስታ ለመመስከር ተቻኩለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡የሰሙት የምስራች ቃል በእነርሱ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር አልፈለጉም ይልቁንም ከወንድሞቻቸው ጋር ለመካፈል ወጡ፡፡ ክርስቶስም ማንንም አያስገድድም፤በፍቅርና በቅን ልብ ለሚፈልጉት ግን ራሳቸውን እስከሰጡት ድረስ ራሱን በሙላት ይገልፃል፡፡እነዚህ ሁለቱ ደቀመዛሙርት የተለያዩ ሦስት የዘመናችንን ሰዎች ይወክላሉ፤እነርሱም

1ኛ ያለ ኢየሱስ የሚጓዙ ሰዎችን

2ኛ ከኢየሱስም ጋር ቢጓዙም ማን መሆኑን የማያውቁ በደመነፍስ የሚመሩ ሰዎች

3ኛ ከክርስቶስ ጋር በኅብረት እና በትብብር በመጓዝ ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎችን፡፡

ምንባቡስለምንይናገራል?

ከምንባቡከተሰጠንሦሥትምሳሌዎችራሳችንንየቱጋእንመድበዋለን?