ሚያዚያ 14ቀን /2004 ዓ.ም - "ሰላም ለእናንተ ይሁን"

ሚያዚያ 14ቀን /2004 ዓ.ም - "ሰላም ለእናንተ ይሁን"

1ቆሮ 15፡1-19 1ዮሐ 1 ፡1-10 ዮሐ 20፡19-31

የእግዚአሔር ቃል ሲናገር ሐዋርያት የአይሁድ ባለስልጣናትን በመፍራት በራቸውን ዘግተው ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ወደተሰበሰቡበት ቤት ገባ፡፡በመካከላቸው ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው፡፡በዚህ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ታላቁን የሰላም ስጦታ ሰጣቸው ይህ ሰላም ከሰው ልጆች ማስተዋል የሆነ እና ቅዱስ ጳውሎስ በመለኮታዊ ጸጋ ተነሳስቶ የሰበከው ነው፡፡ክርስቶስ ወደ ዓለምመጥቶ ያበሰረውን የምስራች ቀጥለው እንዲሰብኩ የስብከተ ወንጌልን ስልጣን እና አገልግሎት ለሐዋርያቶቹ ሰጣቸው፡፡በዚህም ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መልዕክተኞች መሆናቸው ነው፡፡

ሁለተኛው ሐሳብ ስለ ተልዕኮ ጉዳይ ነው፡፡ይህም ኢየሱስ መለኮታዊ ክብሩን ሁሉ ትቶ አገልጋይ መሆኑን እንደወደደ ሁሉ የዚህ ወንጌል አገልጋዮች የእርሱን አብነት በመከተል የዚህ ዓለም ምኞት ፣ደስታ፤ ምቾትና የተመቻቸውን ሕይወት በመተው ራሳቸውን ለዘህ የወንጌል አገልግሎት መስዋዕት አድርገው ማቅረብ ማለት ነው፡፡

በሦስተኛ ትኩረት የተሰጠው ሐሳብ "መሄድ" የሚለው ነው፡፡ ወዴት እንደሚልካቸው አልገለፀም፡፡ስለዚህ እርሱ ወደፈቀደው ቦታ እንጂ ራሳቸው ወደፈለጉበት አይሄዱም፡፡እነዚህ አገልጋዮች ወደተለያዩ ሥፍራዎች ፣ወደተለያዩ ባህሎች፣ቋንቋዎች ፣የአኗኗር ዘዬዎች በመሄድ መልካሙን ዜና ያበስራሉ፡፡በመቀጠልም የኃጥያት ይቅርታን በመስጠት ከአምላካቸው ጋር አንድ እንዲሆኑ አድርጓቸው፡፡በመሆኑም ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል ልባቸውን ሲያመቻቹ ኃጥያታቸው በትሁት ንሰሐ አማካኝነት ይቅር ይባላል፡፡ቤተክርስቲያንም ምዕመናን ከኃጥያት እንዲላቀቁ የመምከር፣የማስተማር እና ከኃጥያት የመመለስ ስራ ትሰራለች፡፡(2ጢሞ 4፡2)

ጥፋትን ቸል አትበል፣በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ያለውንም አስጠንቅቅ፡፡ሰዎች ራሳቸውን ሲያታልሉ ዝም ብለህ አትያቸው፡፡የሰው ልጅ ሁሉ አስርቱን ትዕዛዛት በልቡ ይጠብቅ ዘንድ አስተምራቸው፤ሲበድሉት እያየህ ዝም አትበል፡፡እንዲህ ያለውን ቅዱስ ትዕዛዝ በልቡ ይጠብቅ የሚበድሉ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርስም፡፡(ገላ5፡21ን ተመልከቱ)ተገቢው መድኅን ሁሉ ከተሞከረ በኋላ ሰዎች በኃጥያታቸው ከጸኑ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በሰማይ ፍርድ ይጠብቃቸዋል፡፡

ምንባቡስለምንይናገራል?

ቤተክርስቲያን የማስተማር ስራ ላይ ምን ያህል ትካፈላለህ ?