Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያን

 በኢራቅ በተለይ ደግሞ በባግዳድ የሚኖሩት የአገሪቱ ማኅበረ-ክርስትያን ላይ ምክንያቱ ገና እውን ያልሆነ ለድጋፍና እርዳታ ለማቅረብ እየተባለ በአንዳንድ ግለ ሰዎች የክርስትያን ሕዝብ የብዛት የንብረት ቆጠራ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑ በመጥቀስ የአገሪቱ ከለዳውያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢና ሕልውናን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገሃድ አድረገዋል።

ይህ ጉዳይ ምን ያስከትል ይሆን ለሚለው ጥያቄ የፓክስ ክርስቲ ማለትም የሰላመ-ክርስቶስ ማኅበር ተጠሪ ኣባ ሬናቶ ሳኮ ከቫቲካን ረድዮ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፣ “ክርስትያኖችን ለይቶ መመዝገቡ ምናልባት ለመቆጣጠር ሊያመች ተብሎ ሊሆን ይችላል፣ ይህ ማለት ግን ሌላ አደገኛ ምሥጢር ያለውም ሊሆን ይችላል። ለምንስ ክርስትያኖች ብቻ ለይቶ ብዛታቸው ለማወቅ ተፈለገ? በኢራቅ ውሁዳን የህብረተሰቡ ክፍል ላይ የተከሰተውና ገና በመከሰት ላይ ያሉ ችግሮች እግምት ውስጥ በማስገባት እየተከናወነ ያለው የብዛትና የባለ ንብረትነት ቆጠራ አሳሳቢ ነው” ብለዋል።
 
 
“የኢራቅ ክርስትያኖች ለራስ ደህንነት ሲባል አገራቸው እየለቀቁ ወደ ተለያዩ አገሮች በመሰደድ ላይ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ በዚህ ክልል መረጋጋት እንደሌለ የሚያረጋግጥ ምርጫ ነው። ስለዚህ እየተከናወነ ያለው የክርስትያኖች ብዛትና የንብረት ቆጠራው ጉዳይ ምን ዓላማ እንዳለው በክልሉ ካለው አለ መረጋገት አንጻር ሲታይ የሚያሳስብ ነው። ር.ሊ.ጳ. በቅርቡ በመካከለኛው ምሥራቅ ሓዋርያዊ ጉብኝት ሲያካሄዱ የሚለያዩ ግንቦች ሳይሆን የሚያገናኙ ድልድዮችን እንገባ እንዳሉ አባ ሳኮ አስታውሰው በኢራቅ የተለያዩ ጎሳዎችና ሃይማኖቶችን የሚያቀራርብ ድልድይ ለክልሉ መረጋጋት መሠረት ነው” ብለዋል።
 
 

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።