ሰዎች ሕይወት ቅዱስ መሆኑን የሚያውቁት መች ይሆን?
- Category: ዜናዎች
- Published: Tuesday, 07 July 2009 09:46
- Written by Super User
- Hits: 2293
- 07 Jul
ቫቲካን ራድዮ - (2009-07-07) - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እሁድ ዕለት እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት እና በኋላ ባስተላለፉት መልእክት በዓለማችን በአመጽና በፍትሕ አልቦነት የሚፈሰው ደም ይቁም ሲሉ ተማጥነዋል።
የክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያለው ታማኝ ፍቅር ዋስትና ነው። በምድራችን በተለያዩ ክፍሎች የሚፈሰው ደም ለሚያሰማው የጩኸት ድምፅ እግዚአብሔር መልስ የሚሰጠው በልጁ ደም ነው።
የመጨረሻ የስቃይ ጩኸት ድምፅ የሰማነው ዛሬ ጠዋት በፊሊፒንስ አገር በኮታባቶ ካተድራል በራፍ በፈነዳውና የብዙ ሰው ሕይወት ባጠፋው የግብረ ሽበራ የጥፋት ድርጊት ሰበብ የተፈጠርው ነው በማለት ስለ አደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸው የሽበራ ድርጊት የችግር መፍትሔ አለመሆኑን በማረጋገጥ በአጽንኦት የአምጹን ተግባር ኮንነዋል።