ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛውና የእረፍት ጊዜያቸው
- Category: ዜናዎች
- Published: Tuesday, 07 August 2012 09:23
- Written by Super User
- Hits: 1738
- 07 Aug
www.catholicnewsagency.com - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው በዚህ ወቅት የእረፍት ጊዜያቸውን በሚያሳልፉበት ከሮም ውጭ በሚገኘው ካስተል ጋንዶልፎ ሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ ላይ የሚጽፉትን መጽሐፍ ሦስተኛ መድበል ጽፈው መጨረሳቸውን የቫቲካን የማስታወቂያ ቢሮ ገለጸ።
ይህ መድበል በክርስቶስ የሕፃንነት ሕይወት ላይ የሚያተኩር መሆኑ ሲገለጽ የዚህ መጽሐፍ ሁነኛ እትም በጀርመንኛ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወደተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም ላይ ይገኛል፤ ይህ በዐበይት ቋንቋዎች የመተርጎሙ ሂደት ሲጠናቀቅም ለሕትመት እንደሚበቃ ታውቋል።
አዲሱ መድበል "የናዝሬቱ ኢየሱስ" በሚል ርእስ በ1999 ዓ.ም. የታተመውና በ2003 ዓ.ም. "የናዝሬቱ ኢየሱስ - ከኢየሩሳሌም መግባት እስከ ትንሣኤ" በሚል ርእስ የወጣው የሁለቱ ሥራዎቻቸው ቀጣይ ሦስተኛ መጽሐፍ ነው። ሁለቱ መጻሕፍታቸው በሰባት ቋንቋዎች በወረቀትና በኤሌክትሮኒክ መልኩ ለሕዝብ የቀረቡ ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ መሸጣቸው ታውቋል።
በዚሁ በእረፍት ጊዜያቸው ይህን መጽሐፍ ከማጠናቀቅ ባሻገርም ር.ሊ.ጳ. ከመስከረም 4 እስከ 6 ድርስ በሊባኖስ ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝትም ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውና ምናልባትም ከዚህ የመጽሐፍ ሥራቸው በኋላ አራተኛ የሚሆነውን ለመላዪቱ ቤተ ክርስቲያን የሚሆን አንድ የእምነት አንቀጽን የሚመለከት መልእክት Encyclical letter ሊያዘጋጁ እንደሚችሉ ይገመታል።