Map St Joseph Cistercians

Top Panel

በሮማ አዲስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን

በቀዳሚው ዘመን በነበረችው ቤተክርስትያን ታሪክ ቀደምት የእምነት ሰማዕት ተብለው ከሚጠቀሱት ቀደምት ሰማዕታት ቅድስት ካተሪና ዘ አለክሳድሪያ መሆኗ የቤተክርስትያን ታሪክ የሚገልተው ሲሆን። በዚህ የእምነት ሰማዕት ስም የሚጠራው አዲስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን እ.ኤ.አ. እሁድ ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በሮማ ከተማ መባረኩ ተገለጠ።

በሩሲያ የፓትሪያርክ የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስትያን የሊጡርጊያ ሥርዓት መሪዎች የሊጡርጊያ ሊቃውንት ካህናትና ዲያቆናት እዚሁ ሮማ ቤተ ክርስትያኗ ለመባረክ በተካሄደው የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በመምራት መሳተፋቸው ለማወቅ ተችለዋል።የቅዱስ ዮሓንስ አፈወርቅ አኰቴተ ቍርባን መሠረት ባረገው መስዋዕተ ቅዳሴ፣ የተሳተፉት የክርስትያን አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር እና የዚሁ ምክር ቤት ዋና ፀሓፊ ብፁዕ አቡነ ብሪና ፋረል የብፁዓን ካርዲናላት አፈ ጉባኤ ምክትል ብፁዕ ካርዲናል ሮዠር ኤትቻጋራይ ሌሎች ብፁዓን ጳጳሳትና የካቶሊክ ቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ተጠሪዎችና አባላት መሳተፋቸው ለማወቅ ተችለዋል።
በኢጣሊያ የፈደራላዊት ሩሲያ ልኡከ መንግሥት የሮማ ከንቲባ እና የኢጣሊይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የክርስትያኖች አንድነትና የሁሉም ሃይማኖት ውይይት የሚያነቃቃው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንቸንሶ ፓሊያ መገኘታቸው ተገልጠዋል።

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።