2 - እኛ በእግዚአብሔር የተወደድን ነን
- Category: ከእመቤታችን ማርያም ጋር መጸለይ
- Published: Monday, 09 August 2010 08:20
- Written by Super User
- Hits: 2845
- 09 Aug
2 - እኛ በእግዚአብሔር የተወደድን ነን
የእግዚአብሔር ቃል፤ - የመልአኩ ገብርኤል ብስራት፣ ሉቃስ 1፡ 26-38
‹‹አንቺ ጸጋ የተሞላሽ፤ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ››፡፡
እነዚህ ቃላት ለእያንዳንዳችን ይደገሙልናል፡፡ ማርያም ለእኛ ምሳሌ ናት፡፡ በማርያም እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው የፍቅር ዕቅድ ተፈጽሞአል፡፡ እመቤታችንን በመመልከት እግዚአብሔር እያደረገና ሊያደርግ ያሰበውን ነገር በይበልጥ እንገነዘባለን፡፡ ወደ ኤፌሶን ሰዎች የተላከውን መልእክት እናዳምጥ፤ ‹‹ ›› (ኤፌ 1፡ 3-6)፡፡
እነዚህን ሁለት ጥቅሶችን ማወዳደር እንቸላለን፡፡
|
ሉቃስ 1፡ 26-47 |
ኤፌ 1፡ 3-6 |
1 |
‹‹አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ፤ ከአንቺ የሚወለደውም ልጅ የተባረከ ነው፤ የጌታዬ እናት ልትጎበኘኝ መምጣትዋ ለእኔ እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው››፡፡ |
‹‹በሰማይ መንፈሳዊ በረከትን በመስጠት በክርስቶስ የባረከን›› |
2 |
‹‹ነፍሴ ጌታን ታከብራለች መንፈሴ በአምላኬ በመድኃኒቴ ትደሰታለች››፡፡ |
‹‹የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት የሆነው አምላክ ይመስገን›› |
3 |
‹‹አንቺ ጸጋን የተሞላሽ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻል›› |
‹‹ቅዱሳንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን በፊቱ እንድንገኝ ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ መረጠን›› |
4 |
ማርያምም በክርስቶስ ደም በፀጋ ተሞልታለች |
‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ልጆቹ እንድንሆን አስድሞ ወሰነን፡፡ ይህንንም ያደረገው በተወደደው ልጁ አማካይነት በነፃ የሰጠን ክቡር ጸጋ እንዲመሰገን ነው›› |
ቅድስት ድንግል ማርያምን በማክበር የእግዚአብሔር ፍቅር በአንድ ሰው ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚችል ልንረዳ እንችላለን፡፡ ማርያም፣ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ የለው መጥፎ ነገር ማሸነፍ እንደሚችል፣ ማስረጃ ናት፡፡ ይህም የሚሆነው እኛም እንደ ማርያም ሕይወታችንን ከሰዋንለት ነው፡፡
የቤተሰባችን አባላት በሙሉ፤ አባት፣ እናት፣ ልጆች፣ ወጣቶች፣ ሽማግሌዎችና የታመሙ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት የተወደዱ ናቸው፡፡ ማንም ሊናቅ፣ ሊጣል፣ ሊረሳ፣ ሊረገጥ፣ ሊዋረድና ሊገለል አይችልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለንን እንስማ፤
‹‹ ›› (ሲራክ 3፡ 3-5፣ 12-14)
እንጸልይ፡-
እግዚአብሔር አባት ሆይ፣ ቃል ሥጋ በመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ እኛም እውነተኛ አምላክና ሰው፤ አዳኝ የሆነውን ክርስቶስን እንድንመስል እርዳን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃን፡፡ አሜን፡፡