እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

3 - ክብራችንና የሕፃናት ክብር

3 - ክብራችንና የሕፃናት ክብር

የእግዚአብሔር ቃል፤ - የመልአኩ ገብርኤል ብሥራት፤ ሉቃስ 1፡ 26-38

‹‹መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል››፡፡ ማርያም ‹‹እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ፤ አንተ እንዳልህ ይሁንልኝ›› አለችው፡፡

መንፈስ ቅዱስ በማርያም ላይ መጣ፡፡ እንደ መንፈስ ቅዱስ ፍሬ ቅድስት ማርያም፤

  • ቅዱስ ሕፃን ወለደች፡፡
  • የሕይወቷን ዕቅድ በጥልቀት ተረዳች፣ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለመፈጸም ሳትፈራ የእራሱ አገልጋይ በመሆን ሕይወቷን ሁሉ ለእርሱ ሰጠች፡፡
  • ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት በተራራማው በይሁዳ አገር ወዳለችው ከተማ በፍጥነት ተነስታ ሄደች፡፡

የእናም ቤተሰብ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏል፡፡ በምስጢረ ጥምቀት፣ ሜሮን፣ ቅዱስ ቁርባን፣ ተክሊልና በጸሎታቸው አማካይነት የቅድስት ሥላሴ ቤተ መቅደስ ናቸው፡፡ የእኛም ልጆች ቅዱሳንና የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር የፍቅር ፍሬዎች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሕፃን እግዚአብሔር ለእኛ የላከ መልዕክት፣ ደብዳቤና ሥጋ የለበሰ ቃል ነው፡፡ ኢየሱስ ፍፁም የእግዚአብሔር የተላከ መልዕክት ነው፡፡ ይህንን መልዕክት ልንረዳው፣ ልንሰማው እና ልንቀበለው ዝግጁዎች ነን?

እያንዳንዱ ሰው ወደ ዓለም የሚመጣው ጥሩ ተልኮ ለመፈፀም ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ወደ ዓለም ሲመጣ እግዚአብሔር አንድ ስም (ንጽ. የሐ ራዕይ 2፡ 17)፣ አንድ ጥሪ ይሰጠዋል፡፡ ወደ አባታችን ስንመለስ በዚህ ዓለም ላይ የገነባነው ስም (እዚህ የገነባው ጥሩም ሆነ መጥፎ ተልዕኮ) እግዚአብሔር የሰጠንን ስም (እግዚአብሔር ለእኛ አስቦልን የነበረው ተልዕኮ) ይነጻጸራል፡፡ ሙሉ ደህንነት ልናገኝ የምንችለው ስማችን (ተልዕኮአችንን ከፈፀምን) እግዚአብሔር ከሰጠን ስም ጋር ተመሳሳይ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ሕይወት የዚህ ስም ፍለጋና እግዚአብሔር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ የምንረዳበት ነው፡፡ እመቤታችን የእርሷ ተልዕኮ ስለተረዳች ‹‹አንተ እንዳልህ ይሁንልኝ›› ብላ መልሳለች፡፡

ሕፃንን ልንቀበለው፣ ልናከብረው፣ ለናገለግለውና በክርስቲያናዊ ጥሪ መሰረት እንዲያድግ ልናገዘው ዝግጁዎች ነን ወይ?

‹‹ ›› (ማር 9፡ 36-37)፡፡

አንድ የክርስቲያን ቤተሰብ ለልጆቹ የሚያስፈልገውን መሰረታዊ መብት፤ እምነት፣ ትምህርት፣ ምግብ፣ ጤናቸውን መጠበቅና ክብር መስጠት ችላ ብሎ፣ እንዴት ልጆቹን በመጥፎ አያያዝ፣ አጎሳቁሎ፣ በቸልተኝነት፣ ለራስ ጥቅም ብቻ ሥራ በማሰራት ያሳድጋል?

‹‹ ›› (ማር 9፡ 42)

እያንዳንዱ ሕፃን የቅድስት ሥላሴ ቤተ መቅደስ መሆኑን እናምናለንና እያንዳንዱን ሕፃን የቅድስት ሥላሴ ቤተ መቅደስ መሆኑን እናምናለንና እያንዳንዱን ሕፃን በአክብሮት መያዝ አለብን፡፡ ይህ ባሕላችን ስለሆነ ለዚህ ምስክርነት መስጠት አለብን፡፡

እንጸልይ፡-

የክርስቶስ አባት የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዝቅተኛ ቦታ አንስተህ የአዳኝ እናት በማድረግ ኃይልህን ገልጠሃል፡፡ የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት ክርስቶስን እየጠበቀ ላለው ዓለማችን እርሱን እንዲያመጣና ሙሉ ያልሆነውን ዓለማችን በለጇ እንዲሞላ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት