ስፖርት የመቻቻልና የሰላም ትምህርት ቤት ነው! ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

ስፖርት የመቻቻልና የሰላም ትምህርት ቤት ነው! ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

WC2014ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ዛሬ ለሚጀመረው ለ2006 ዓ.ም. የዓለም ዋንጫ ትላንትና ረቡዕ ለአዘጋጆች፣ ለተጫዋቾችና ለደጋፊዎች የሚሆን የሰላም መልእክት አስተላለፉ።

ር.ሊ.ጳ. ለብራዚሏ ርእሰ ብሔር ዲልማ ረውሴፍ ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ በማንኛውም ደረጃ ዘረኝነትን መዋጋት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በተጨማሪም ስፖርት አንዱ ከሌላው ጋር እሴቱን ማለትም ጠቃሚ ነገሩን የሚለዋወጥበት መሣርያ መሆኑን ገልጸዋል። {jathumbnail off}

“ግላዊ ጥቅምን፣ ራስ ወዳድነትን፣ ማንኛውንም ዓይነት ዘረኝነት፣ ያለመቻቻልና ሌሎችን የመግዛት ዝንባሌን ማስወገድ ድል ለማድረግ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። በሕይወት በጣም ስግብግቦች ሆነን በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን የምንረሳ ዓይነት ስንሆን መላው ማኅበረሰብ ይሰቃያል።” በማለት ስፖርት ለማኅበረሰብ ሊያበረክት የሚችለውን የሁሉን አቀፍ ባህርይ አጉልተው ተናግረዋል።

ከዋነኛው የስፖርት ክንዋኔ ባሻገርም ይህ የዓለም ዋንጫ በዓለም ሕዝቦች መካከል የመቀራረብና የመተባበር ዝግጅት ይሆን ዘንድ ር.ሊ.ጳ. ተስፋቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ስፖርት በመዝናኛነት ብቻ ሳይገደብ ላቅ ብሎ የሰው ለሰው ጠቃሚ ነገሮች መለዋወጫ መድረክ በመሆን ሰላማዊና ወንድማማቻዊነት የነገሠበት ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን አሳስበዋል።

“ስለ ታማኝነት፣ ጽናት፣ ወዳጅነት፣ መጋራትና መተባበር እናስብ። በርግጥ እነዚህና እነዚህን መሰል እሴቶች በእግር ኳስ የሚበረታቱ ሲሆኑ ከዚያ ባሻገር በሁሉም የሕይወት መስክና በተጨባጭ በሚደረገው ሰላምን የመገንባት ሂደት ጠቃሚነታቸው መታየት አለበት። ስፖርት የሰላም ትምህርት ቤት ነው” በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዛሬው የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ላይ የተለያዩ የሥነ ጥበብ ሰዎችን ያካተቱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች መኖራቸው ሲታወቅ፤ የብራዚላዊቷን ፕሬዝደንት አካቶ ማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ ንግግር እንደማይኖር ተነግሯል። ሆኖም ግን እርግቦች የመልቀቅ ሥርዓት ላይ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስና የሌሎች ሃይማኖት አባቶች መልእክት እንደሚነበብ ታውቋል።

ምንጭ፡- http://www.copa2014.gov.br/en/noticia/pope-francis-football-must-be-a-school-building-a-culture-compromise

- http://www.abs-cbnnews.com/sports/06/12/14/jlo-iron-man-suit-star-world-cup-extravaganza

- http://www.news.va/en/news/pope-francis-sends-message-to-world-cup-opening

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።