በዓለ ጥምቀት ዘእግዚእነ

የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እሑድ ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በቅዱስ ዮሓንስ እጅ የተጠመቀበትን ዕለት አክብራ ውላለች። በዚህ ዓቢይ በዓል ሁሌ በየዓመቱ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ለሕፃናት እና የክርስትና እምነት ለሚቀበሉ ምሥጢረ ጥምቀት የምትሰጥበት ዕለትም ጭምር መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ትላንትና 14 ሕፃናት ወንዶችና 7 ሕፃናት ሴቶች በደብረ ቅዱስ ጴጥሮስ  በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው መጠመቃቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስስ 16ኛው እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. ለበዓለ ጥምቀት ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ የምንኖርበት ዘመን የሞት ባህል የተንሰራፋበት የሆነው፤ የታጠረ የተደበቀ የተደናገረ ሕይወት የሚኖርበት ጸረ ባህል እና ከተለያዩ ችግሮች ለማምለጥ ሲባል ለተለያዩ አንደንዛዥ እጽዋት እጅ የሚሰጥበት፣

ከተጨባጩ ሕይወት ለማምለጥ አታላይ እና ጊዚያዊ ደስታ በሆነው ሕይወትን በሚያታልለው የሓሰት መንገድ በኢፍትሐዊነት ተግባር ሌላውን ዋጋ ቢስ በማድረግ በማንቋሸሽ በጠቅላላ የሰው ልጅ ሰብአዊነት እየተዘነጋ እንደ ግኡዝ የሚታሰብበት መሆኑን በማብራራት፣ ወላጆች ይህ ዓይነቱ ኢባህል በተዛመተበት ዓለም ቤተሰብን ይመሠርታሉ፣ ይህንን ባህል በመጋፈጥም በእምነት ልጆቻቸውን ለማነጽ ይተጋሉ። ባላቸው እምነት ምክንያትም ልጆቻቸው የጥምቀት ምሥጢር ተካፋይ እንዲሆኑ ይፈቅዳሉ ብለዋል።


እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. በበዓለ ጥምቀት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ ወላጆች እምነትቸውን በተመለከተ በሳል ግንዛቤ ካላቸው በርግጥ ልጆቻቸውን በእምነት ይመራሉ፣ ካልሆነ ግን እንደ ግኡዝ ነገርና እንደ ንብረት በማየት፤ ልጆቻቸውን የገዛ ወላጆቻቸው ምኞች እና ፈቃድ መገለጫ እንዲሆኑ በማስገደድ ለተለያዩ ችግሮች እንዲጋለጡ ያደርጋሉ። የሚወለደው ሕፃን ምሉእ ነጻ ሰው መሆኑ በመገንዘብ ወላጆች ልጆቻቸው በእምነት ታንጸው የራሳቸው ጥሪ እንዲኖሩ አርአያ በመሆን በማነጽ ሰብአዊ እና መፍነሳዊ እድገት በማሟላታ ለማንከባከብ መጠራቸውን እንዲረዱ በማሳሰብ፣ የክርስትናው ባህል የተወለደውን ሕፃን ወደ እግዚአብሔር ብርሃን በመጥራት እውነተኛው ነጻነት ባለበት እርሱም የእግዚአብሔር ልጆች ከመሆን የሚገኘው ጸጋ እንዲቀበሉ ለሚያደርጋቸው የመለኮታዊ ሕይወት ጸጋዎችን እንዲታደሉ ብሎም እውነተኛው የነጻነት ትርጉም እየተረዱ የሚከተሉት የሕይወት ምርጫ ለመለየት የሚያግዛቸው የኃላፊነት ብቃት እንዲያጎለብቱ ያደርጋል እንዳሉ የሚዘከር ነው።


ወላጆች ልጆቻቸውን ብርቱዎች እና ጤናማ አድርጎ ለማሳደግ በሚያደርጉት ጥረት ሕፃኑ የሚሻውን ቁሳዊ እንክብካቤ በማሟላት ዘለዓለማዊ ሕይወትን ለመታደል እግዚአብሔርን ማወቅ ማፍቀር እና በእማኔ ማገልገል ይኖርባቸዋል ሲሉ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. በበዓለ ጥምቀት ባሰሙት ስብከት እንዳሰመሩበት የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. ወላጆች በልጆቻቸው ሰብአዊ እና የመንፈሳዊነት ነጻነት ብስለት በመወሰኑ ረገደ የሚሰጡት አብነት እና ምስክርነት አቢይ ተጽእኖ እንዳለው ተገንዝበው፣ ምንም’ኳ በሥራው ዓለም እጅግ የተወጠሩ ቢሆንም በቤተሰብ ማዕድ እና ጥላ ሥር የክርስትናው እምነት ጽናት የሚያረጋግጠው የጸሎት መንፈስ እንዲኖር በማድረግ ኃላፊነት እንዳይጎድሉ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሷል።


ምንጭ፡- ቫቲካን ሬድዮ

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።