እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የባልና ሚስት ፍቅርና መተማመን

የባልና ሚስት ፍቅር

ሩካቤ ለወንድና ለሴት ቃል ኪዳናዊ ፍቅር የታቀደ ነው፡፡ በጋብቻ ጊዜ በባልና ሚስት የሚፈጸም ጥልቅ የሆነ አካላዊ ግንኙነት የመንፈሳዊ ሱታፌ ምልክትና ዋስትና ይሆናል፡፡ በተጠመቁ ሰዎች መካከል የሚፈጸሙ ጋብቻዊ ትስስሮች በምስጢረ ተክሊል ይቀደሳሉ፡፡

“ወንድና ሴት ለባልና ሚስት በተገባና የእነርሱ ብቻ በሆነ እርስ በእርስ መሰጣጠት የሚፈጽሙት ሩካቤ ሥነ-ሕይወታዊ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሰውን ልጅ ጥልቅ ማንነትም የሚመለከት ነው፡፡ ይህ ጋብቻዊ ፍቅር በትክክል ሰብአዊ በሆነ መንገድ ከፍጻሜ የሚደርሰው ወንድና ሴት እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ እርስ በእርስ ፍጹም አንድ ለመሆን ቃል የገቡበት ፍቅር ሁነኛ አካል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡”

ሁለቱ ቤት በተዘጋባቸው ጊዜ ጦብያ ከአልጋው ተነሥቶ “እቴ፣ ተነሽ፤ እግዚአብሔር ይቅር ይለን ዘንድ እንለምን” አላት፡፡ ጦቢያም “አቤት ያባቶቻችን ፈጣሪ አንተ ምስጉን ነህ፤ … አባታችን አዳምን አንተ ፈጠርከው፤ ትረዳውም፣ ታሳርፈውም ዘንድ ሐዋን ሰጠኸው፡፡ ከነዚህም ሰው ሁሉ ተወለደ፡፡ አዳምን ትረዳው ዘንድ ሔዋንን እንፍጠርለት እንጂ አዳም ብቻውን ይኖር ዘንድ አንተ በጐ ነገር አይደለም አልክ፡፡ አሁንም ይህችን እቴን የማገባት በሚገባ ነው እንጂ ስለ ዝሙት አይደለምና አቤቱ እንረዳዳ ዘንድ ለእሷና ለእኔ ይቅርታህን ስደድልን” አለ፡፡ እርሷም “ከእርሱ ጋር በውነት ይደረግልን” አለች፡፡ በዚያች ሌሊት ሁለቱም አብረው አደሩ፡፡ ጦቢት 8፡4-9

“በጋብቻ ውስጥ የሚፈጸሙትና ጥልቁና ንፁሑ የባልና የሚስት ግኑኝነት የሚከወንባቸው ድርጊቶች ድንቅና የከበሩ ናቸው፤ የእኒህ ድርጊቶች ትክከለኛው ሰብአዊ አፈጻጸም የሚወከሉትን ራስን መስጠትን ከማጉላት በተጨማሪ ተጋቢዎቹን በሐሴትና በምስጋና ያበለጽጓቸዋል፤” ሩካቤ የሐሴትና የእርካታ ምንጭ ነው፡፡

ፈጣሪ ራሱ ባልና ሚስት ዘርን የማብዛት ተግባርን ሲፈጽሙ ሳለ የሥጋና የመንፈስ ደስታና እርካታ ሚያያገኙበትን ደንብ መሠረተ፡፡ ስለዚህ ባለና ሚስት ደስታንና እርካታን በመፈለጋቸውም ምንም ዓይነት ክፋትን አይፈጽሙም፡፡ ፈጣሪ ለእነርሱ ያሰበላቸውን ብቻ ይቀበላሉ፡፡ ሆኖም ባልና ሚስት ከተወሰኑላቸው ሁኔታዎች መውጣት እንደማይገባቸው ማወቅ አለባቸው፡፡

የባልና ሚስቱ አንድነት የጋብቻን ሁለት ዓላማዎች፣ ማለትም የባልና የሚስቱን በጐነትና ሕይወትን የማስተላለፍ ተግባር ከፍጻሜ ያደርሳል፡፡ እኒህ ሁለት የጋብቻ እሴቶች ወይም ትርጉሞች የባልና የሚስቱ መንፈሳዊ ሕይወት የጋብቻ መልካምነትን የቤተሰቡ የወደፊት ሕይወት ካልተለወጠ በቀር ሊነጣጠሉ አይችሉም፡፡

ስለዚህ የባለትዳሮች ሩካቤአዊ ፍቅር ድርብ በሆኑት በታማኝነትና ልጅን በማፍራት ኃላፊነት ሥር የተያዙ ናቸው፡፡

የባለ ትዳሮች መተማመን

ባልና ሚስት “ጥልቅ የሆነ የሕይወትና ፍቅር አነድነት ያለው በፈጣሪ የተቋቋመና በሕግጋቱ ብቁነት ያገኘ ጓደኝነትን” ይመሠርታሉ፡፡ “ይህ የሕይወት ጓደኝነት በባልና ሚስት የማይሻር ጋብቻዊ ቃል ኪዳን ላይ የተመሠረተ ነው” ባልና ሚስት በተሟላ ፍላጐት ሙሉ በሙሉ እርስ በርስ ይሰጣጣሉ፡፡ እነርሱ ከአንግዲህ ወዲህ ሁለት አይደሉም፤ አንድ ሥጋ ብቻ ናቸው እንጂ፡፡ ባልና ሚስት ባይገደዱ በሙሉ ፈቃደኝነት ውል የተቡለትን ቃል ኪዳን ልዩና የማይፈርስ አድርገው እንዲጠብቁት ግዴታን ያስከትልባቸዋል፡፡ “እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየውም፡፡” ማር. 1ዐ፡9

ታማኝነት ቃል የገቡለትን ነገር ዘወትር አጽንቶ መጠበቅን ይገልጻል፡፡ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፡፡ ምስጢረ ተክሊል ወንድና ሴት በክርስቶስ ላይ ባላቸው አመኔታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት ያስችላቸዋል፡፡ ወንድና ሴት በጋብቻዊ ፍቅር ንጽሕና አማካይነት በዓለም ፊት ለዚሁ ምስጢር ይመሰክራሉ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እያንዳንዱ ወጣት ሙሽራ ሚስቱን “በእቅፌ አስገብቼሻለሁ፣ እወድሻለሁ፣ ከሕይወቴ አብልጨ አፈቅርሻለሁ፤ያለንበት ሕይወት ምንም ማለት አይደለም፤ የጋለ ምኞት ለወደፊቱ በሚመጣው ዘመነ ተዘጋጅቶአል ባለ ሰፍራ እንደማንለያይ ለማረጋገጥ በዚሁ ምድር ሕይወቴን ካንቺ ጋር ማሳለፍ ነው፤ በእኔ ዘንድ የአንቺ ፍቅር ከሁሉ ነገር በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከአንቺ ሐሳብ ጋር እንዳለ መስማማት የሚመረኝ ወይም የማያመኝ ነገር ከቶ የለም ማለት አለበት”

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት