Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የር.ሊ.ጳ የጥቅምትና የኅዳር ወሮች ፕሮግራም

ራድዮ ቫቲካን - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛው የዘንድሮውን የኤውሮጳውያን ዓመት በአፍሪቃ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ፣ በጣልያን አገር በሚያደርጉት ሐውጾተ ኖልዎ እና ሌሎች በመንበረ ጴጥሮስ በሚደረጉ ሥርዓተ አምልኮአዊ አገልግሎቶች እንደሚፈጽሙት ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክቷል። ይህንን ያመለክቱት የቅዱስነታቸው የሥርዓተ አምልኮ ተግባሮች መሪ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጒዶ ማሪኒ ናቸው።

 

ብፁዕነታቸው በሰጡት ማብራርያና በቅዱስነታቸው መርኃ ግብር መሠረት
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛው እፊታችን ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓም በላመጽያ ተርመ እና ሰራ ሳን ብሩኖ በሚባሉ የካላብርያ ክፍለሃገር ከተሞች ሐውጾተ ኖልዎ ያደርጋሉ፣ ላመጽያ ተርመ የሚባለ በካታንዛሮ ክልል የሚገኛ ሃገረ ስብከት ነው። በመርኃ ግብሩ መሠረት ቅዱስነታቸው እኁድ ጥቅምት 9 ቀን ጥዋት 9፡15 በላመጽያ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፍያ በመገኘት ወዲያውኑ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ ከዛ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ በማቅረብ ከምእመናኑ ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ያሳርጋሉ፣ ከክልሉ ጳጳሳት ጋር ምሳ ከተጋበዙ በኋላ በሄሊኮፕተር ወደ ሰራ ሳን ብሩኖ ይጓዛሉ። ማምሻውን በጥንታዊው የቸርቶዚና ገዳም ከሚኖሩ መነኮሳን ጋር ጸሎተ ሠርክ እንደሚያሳርጉም ተመልክተዋል። ጉብኝቱን ከፈጸሙ በኋላ ሰባት ሰዓት ተኩል ወደ መንበራቸው ሮማ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፣
ቅዱስነታቸው ይህንኑን ሐውጾተ ኖልዎ ከፈጸሙ ከአንድ ሳምንት በኋላ በአዲሱ የስብከተ ወንጌል ጳጳሳዊ ምክር ቤት በተዘጋጀው ለጥቅምት 15 እና 16 ቀኖች የሚካሄደውን ጉባኤ በመሥዋዕተ ቅዳሴ ይከፍታሉ። በጉባኤው የሃገረ ስብከቶች ተወካዮ መንፈሳውያን ማኅበራት ቊምስናዎች እና በምዕራቡ ክፍለ ዓለማችን ለስብከተ ወንጌል የተላኩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴዎችና ማኅበራት አባላትም እንደሚሳተፉ ተመልክተዋል።
ከዚሁ ጉባኤ አንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓም፡ የሳቨርያኒ መሥራች የሆኑ ብፁዕ ጒዶ ማርያ ኮንፎርትና ከኢጣልያ ቅዱሳን ካህናት አንዱ የሆነው የልዊጂ ጓነሎ እንዲሁም የቅዱስ ዮሴፍ ደናግ መሥራች የሆነው የቦኒፋቻ ሮድሪግወዝ ካስትሮ ሥርዓተ ቅድስና ያውጃሉ፣
ጥቅምት 26 ቀን ደግሞ በብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተጀመረው የአዚሲ የኅብረት ጸሎት ለመሳተፍ እንዲዘጋጁ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምእመናን ጋር አብረው ጸሎት ያሳርጋሉ፣
በመጀመርያው የኅዳር ወር ቀኖች የተለመደውን የቅዱሳንን የሙታን ዕለታትን በተለያዩ ሥርዓተ ጸሎቶች በቫቲካን ያስታውሳሉ፣
በመጨረሻም ከኅዳር 18 እስከ 20 ቀን በበኒን ሐዋርያዊ ጉዞ እንደሚያደርጉ አጋጣሚውም የበኒን ክርስትና 150 ዓመት መሆኑ ሲመለከት ቅዱስነታቸውም ለአፍሪቃ ጳጳሳት የሁለተኛው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት የሆነውን ሐዋርያዊ ምዕዳናቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፣

 


አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።