Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የእግዚአብሔርን የፍቅር ትእዛዝ መከተል

 

ራድዮ ቫቲካን - ቫቲካን በሚገኘው የሲኖዶስ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ከጥቅምት 20 ቀን እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2011ዓ.ም አለም ዓቀፍ የለመከላከያ ኃይል አባላት ሐዋርያዊ አገልግሎት ኀላፊ ብፁዓን ጳጳሳት እና ለመከላከያ ኃይል አባላት የነፍስ አባቶች ጉባኤ መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይህ ለመከላከያ ኃይል አባላት የሚሰጠው ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚመለከት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 24 ቀን 1986 ዓ.ም ይፋ ያደረጉት የመከላከያ ኃይል አባላት መንፈሳዊ እንክብካቤ ሐዋርያዊ መመሪያ ድንጋጌ 25ኛው ዓመት በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት የተከናወነ በመሆኑም የጉባኤው ሂደት ለየት እንዲል እንዳደረገው ቅዳሜ ጧት ለተጋባዦች ቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ባሰሙት ስብከት ማስታወሳቸው ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለተጋባዦች ያስተላለፉት ምዕዳን

የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ኃላፊ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ የላቲን አሜሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርጊት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት መነበቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለተጋባዦች ባስተላለፉት መልእክት፣ መንፈሳዊ አድማስ የሰው ዘር ሁሉ የሚመለከት መሆኑ በማብራራት የወታደር ሕይወት ጭምር ትኩረት የሚያሻው ሰብአዊ ባህርይ መሆኑ እንዳይዘነጋ አደራ ብለዋል።

የመከላከያ ኃይል አባላት ጥልቅ እምነት እንዲኖራቸው እና በሚኖሩበት እና በተሰማሩበት አገልግሎት እውነተኛ የክርስቶስ ምስክር ሆነው እንዲገኙ የማድረጉ ቅዱስ አላማ ክርስትያን የመከላከያ ኃይል አባላት የሚያንጽ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ዘርፍ መሆኑ በማስታወስ፣ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን ለመከላከያ ኃይል አባላት መንፈሳዊ እንክብካቤ እንድታደርግ መጠራትዋ ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፣ ለዚህ መሳካት የመከላከያ ሃይል አባላት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ብፁዓን ጳጳሳት እና የመከላከያ ሃይል አባላት መንፈሳዊ አባቶች እና ቆሞሶች ወንጌላዊ ምስክርነት ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ፣ የአንድ ክርስቲያን የመከላከያ ኃይል አባል መንፈሳዊ ሂደት፣ ለእግዚአብሔር እና ለባልንጀራው ያለውን ፍቅር የሚገለጥ ነው። ስለዚህ የሰላም መሣሪያ እንዲሆን የተጠራ ነው ብለዋል።

በተለያየ ሰብአዊ እና የተፈጥሮ አደጋ በተከሰተበት ክልል ተሠማርተው ግብረ ሠናይ የሚፈጽሙ የመከላከያ ኃይል አባላት ለገዛ እራሳቸው ሕይወት ሳይሳሱ እራስን አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለም የሚለው የእያንዳንዱ ክርስትያን ፍቅር ክርስቶሳዊ መመዘኛ በመኖር፣ ጦርነት በሚካሄድባቸው ክልሎች በሰላም አስከባሪ ተልእኮ ወንድማማቾች የእርስ በእርስ ሞት ምክንያት እንዳይሆኑ በማረጋገት ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰጡት የግብረ ሠናይ አገልግሎት የሚደነቅ ነው። ኃይሉም ከእግዚአብሔር ነው ካሉ በኋላ፣ ለመከላከያ ኃይል አባላት የሚሰጠው ወንጌል ማስፋፋት አገልግሎት ኃላፊነት ቀላል አይደለም። ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 2002 ዓ.ም. ባስተላለፉት ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት እውነተኛ ሰላም የፍትህ ውጤት ነው ያሉትን ሐሳብ በማስታወስ፣ ሰብአዊ ፍትህ ኮሳሳ እና ኢፍጹም በመሆኑም በፍትህ ላይ ይቅር የመባባል መንፈስ መታከል አለበት። በማለት ያስትላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።