Map St Joseph Cistercians

Top Panel

በቃሉ የተነካ ልብና አእምሮ

ጸሎተ ሐሙስየላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ወደ በዓለ ትንሣኤ ዘእግዚእነ የሚያሸጋግረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰሙነ ሕማማት ባለፈው ሳመንት የተከበረ ሲሆን፣ በጸሎተ ሐሙስ የነበረው ሥርዓትና የቅዱስ አባታችን ስብከትእንደሚከተለው ቀርቧል።

ጸሎተ ሐሙስ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የቅብአ ቅዱስ ሥርዓት መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚፈጸምበት ዕለት ሲሆን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱስ ቁርባን እና ምሥጢረ ክህነት ምሥረታን በማረጋገጥ ለደቀ መዛሙርቱ "እርስ በእርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ" (ዮሐ. 13፣ 34) በማለት አዲስ ትእዛዝ የሰጠበትና ቋሚ ሥርዓተ ሊጡርጊያ የሚፈጸምበተ ዕለት ሲሆን፤ በዚህ የቅዱስ ቁርባን ምሥረታ ማረጋገጫ የሆነው የጌታ የመጨረሻ እራት ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ጌታችን ለአርድእቱ የፈጸመው ሥርዓተ ሕጽበተ እግር ምልክት በተለይ በተራ ምሳሌ የሚፈጸምበት ዕለት ነው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው በዚሁ እለት ሥርዓት ላይ "የእውነተኛው ተሃድሶ ኃይል" የሚል ሃሳብን ማእከል በማድረግ በቅዱስ ጴጥሮስ አቢይ ደብር ባሰሙት ስብከት ካህን ግላዊው ክንዋኔንበመካድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመዋሃድ የተጠራ መሆኑ በማሳሰብ፣በተለይ ደግሞ ምእመናን በዘንድሮው የእምነተ ዓመት ጸጋ አማካኝነት በማኅበርሰባችን የሚይታየው ሃይማኖታዊ መሃይመነትን እንዲዋጉ አበረታተዋል።

ካህን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሱታፌ (ኅብረት) ያለው እና ከእግዚኣብሔር የሚጀምር ተግባርን የሚያከናውን መሆን አለበት። በምሥጢረ ክህነት አማካኝነት ለእግዚኣብሔር የተለየው ካህን፣ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የጠለቀ ግኑኝነት ያለው፣ ክርስቶስን በጥልቀት ለመምሰል የተጠራ መሆኑን በመገንዘብ፣ ክርስቶስን ተመስሎ በሚኖረው በዚህ ሕይወት አማካኝነትም የግል ምኞት እና ጉጉትን ሁሉ በመካድ (በፈቃዱ በመተው) አዛዥ ሳይሆን አገልጋይ ሆኖ መኖር አለበት። ይህ ጥሪ ከክርስቶስ ጋር ጥልቅ መተሳሰር የሚጠይቅ እንደውም እርሱን መምሰል ከእርሱ ጋር መወሃድ የሚል ከገዛ እርስ በልጦ ብዙውን ጊዜ ከሚሰበከው ገዛ እርስን ማረጋገጥ ከሚባለውን አነጋገር እና ተግባር ርቆ የእኔ የሚለውን ሁሉ የሚክድ፤ ሕይወትን ለገዛ እራስ ምርጫ መጠቀሚያ ሳይሆን ለክርስቶስ የሚያቀርብ ነው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሠራው ምሥጢረ ክህነት በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስትያን በሚጋረጧት ፈተናዎች ምክንያት ለአደጋ ሲጋለጥ ይታያል፣ ለዚህ እንደ አብነትም በቅርቡ በአንዳንድ ጥቂት የኤወሮጳ አገሮች ካህናት የክህነት ምሥጢር ለሴቶች እንዲፈቀድ ያቀረቡት የጥያቄ ጥሪ "ተአዝዞን የሚቃወም" የቤተ ክስትያን ሥልጣናዊ ትምህርትን የሚያገል መሆኑን ቅዱስነታቸው በመግለጥ፣ አለ መታዘዝ መንገድ ሊሆን ይችላልን? በመታዘዝ እንጂ ባለ መታዘዝ እውነተኛ የቤተ ክርስትያን ተሃድሶ አይረጋገጥም። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በእኛ ፍላጎት እና አስተሳሰብ አማካኝነት መለወጥ ሳይሆን፣ ለቤተ ክርስቲያን በመታዘዝ ብቻ ነው ቤተ ክርስትያንን በእውነት ለማደስ የሚቻለው ብለዋል።

ቤተ ክርስትያን ለወቅታዊው ሁኔታ የበቃች ሆና እንድትገኝ የማያግዟት ጉዳዮች አሉ፣ እውነት ነው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃል እና ፈቃድ ለማፈን ሥጋት የሆነውን ሰብአዊ ባህል አድሷል፣ በማረምም አስተካክሎታል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በማድረግ ለእውነተኛው የእግዚአብሔር ፈቃድ መታዘዝን ዳግም አነቃቅቷል። እውነተኛ ተአዝዞ የሚል እጅግ ያተኮረበት እና በልቡም ያለው ጥልቅ ፍላጎት የሰው ልጅ የራሱ ብቸኛ ዳኝነቱን የሚቃወም ነው ብለዋል። ኢየሱስ ተልእኮውን በፍጹም ተአዝዞ እና እስከ መሰቀል ድረስ የገዛ ራሱን ዝቅ በሚታደርግ ትህትና አማካኝነት የተሰጠው የተልእኮ ጥሪን በመፈጸም፣ ለተልእኮው ታማኝ ሆኖ ታማኝነቱን አረጋግጧል። ኢየሱስ የአብ አንድ ልጅ ሕይወቱን "የኔ ሳይሆን ያንተ ፈቃድ" በማለት በኖረው ፍጹም ተአዛዞ ለአብ መታዘዝ የሚሰጠውን ጸጋ በመኖር ገልጦታል። የኢየሱስ ትህትናው ከመለኮታዊነቱ ጋር እውነተኛውን መንገድ ያመለክተናል።

ይህንን መሠረት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ይላሉ፣ ካህናት የግላቸው ርእዮተ ዓለም እና አስተሳሰብን ሳይሆን 'የቤተ ክርስትያንን እምነት እንዲያበሥሩ የተጠሩ ናቸው። ብዙዎች ይኸንን አነጋገር ጸረ ለውጥ፣ ወግ አጥባቂነት የሚል ትችት ሲሰነዝሩበት ይታያል። ሆኖም ድኅረ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በቤተ ክርስትያን የተወለዱት የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴዎች የቤተ ክርስትያን ኅያውነትና ባለችበት ዘመን ተጨባጭ እና ንቁ ተሳታፊ መሆኗን የሚያደርጋጥ እውነተኛው አዳሽ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሆኑ ተመስክሯል። በተአዝዞ ላይ የጸናው እምነት ያለው ፍርያማነት የፍቅር እና የተስፋ ንቁ ኃይል መሠረት መሆኑ እየተመሰከረ ነው።

ቅዱሳት ተኃድሶ እንዴት እንደሚረጋገጥ እና እንደሚሠራ ለዚህ ሕይወት እንዴት ልንታዘዘውም እንደሚገባን በቃል እና በሕይወት እግዚአብሔር በቁጥር ብዛትና በጊዚያዊ እርካታ ሳይሆን በትናንሽ እና ትሁታን በሆኑት ተግባሮች አማካኝት መሆኑን ለማስረዳት ከሁሉም ያነሰች የሰናፍጭ ዘር ነገር ግን ከሁሉም አትክልቶች በልጣ የምትገኘውን በማስታወስ በትህትና እና እራስ ዝቅ በማድረግ የሚረጋገጠው የላቀውን ድል ያረጋግጥሉናል ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ቀጥለውም እምነታችንን፣ ሃይማኖታችንን ለመኖር እና እግዚአብሔርን ለማፍቀር ማለትም በትክክል እና በተገባ እርሱን ማዳመጥ የበቁ ለመሆን እርሱ እንደሚለውም ልባችን እና አእምሮአችን በቃሉ የተነካ መሆን እንዳለበት ገልጠው፣ በዓለማችን የሚታየው የሃይማኖታዊ መሃይምነት በመጥቀስ፣ ሃይማኖታዊው መሃይምነት ልባም ተመስሎ በመስፋፋት ላይ ነው። የእምነት ዓመት እምነታችንን በአዲስ ቀናተኛ መንፈስ እና በአዲስ ኃሴት አማካኝነት እንድንኖረው እና እንድንመሰክረው የሚያነቃቃን ቅዱስ አጋጣሚ ነው። ስለ ነፍስ መናገር የሚጠላ እንዳውም ማስታወስንም ፈጽሞ እንዳይቻል የሚያደርግ ነፍስን የሚክድ ባህል በመስፋፋት ላይ ቢሆንም ቅሉ፣ ይኽንን በሥጋ እና አካል ብቃት ላይ ያተኮረውን ባህል፣ የሰው ልጅ ሙሉ ደኅንነት ላይ በማተኮር ብቃት ተለውጦ እንዲኖረው ማድረግ ይገባናል፣ ስለዚህ ካህናት የአገልግሎት ጥሪያቸውን ተራ ሥራ አድርገው ከመኖር ፈተና ተቆጥበው ተልእኮ መሆኑን እንዲመሰክሩ አደራ በማለት፣ ካህን ሕይወቱ የገዛ እራሱ ሳይሆን የጌታ በመሆን ለሌሎች እርሱ በሚሰጠው የወንጌል ታማኝነትን የሚያበክር ከእውነተኛው ቀናተኛ መንፈስ የመነጨ ምስክርነት የሚያቀርብ የአገልግሎት ሕይወት መሆኑ መገንዘብ ይኖርበታል በማለት ያሰሙትን ስብከት አጠቃለዋል።

ምንጭ:- ቫቲካን ራድዮ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።