Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የካህናት ቁጥር እድገት አሳየ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ደናግላን ቁጥር ሲቀንስ በአንፃሩ ግን የካህናት ቁጥር እድገት አሳይቷል

እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. በዓለም ላይ 1 ቢሊየን 181 ሚሊየን የነበረውየካቶሊካውያን ቁጥር በ2010 ዓ.ም. 15 ሚሊየን በመጨመር ወደ 1 ቢሊየን 196 ሚሊየን ከፍ በማለት የ1.3 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዓለም ላይ የተጠመቁ ካቶሊኮች አኀዝ በቋሚነት 17.5 ከመቶ አካባቢ ይገኛል፡፡

የካቶሊኮች ቁጥር ከአጠቃላይ የሕዝብ ብዛት አንጻር ሲታይ ከአህጉር አህጉር ይለያያል፡፡ በደቡብ አሜሪካ 28.54 ከመቶ የነበረው ወደ 28.34 ከመቶ ዝቅ ሲል እንደዚሁም በአውሮፖ ከ25.05 ከመቶ ወደ 23.83 ከመቶ ወርዷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ግን ከ15.15 ከመቶ ወደ 15.55 ከመቶ በምሥራቅ እስያም እንደዚሁ ከ10.47 ከመቶ ወደ 10.87 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

የጳጳሳት ቁጥር ከ5,065 ወደ 5,104 አድጓል፡፡ ይህም ከመቶ የ0.77 እድገት ማለት ነው፡ይህም በአፍሪካ 16 አዳዲስ ጳጳሳት፣ በአሜሪካ 15 እንዲሁም በእስያ 12 ሲሆን በአውሮፓ ግን በትንሹም ቢሆን ቀንሷል፡፡ ይኸውም ከ1, 607 ወደ 1, 606 እንደዚሁም በኦሽንያ ከ132 ወደ 129 ዝቅ ብሏል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ የካህናት ቁጥር ወጥ የሆነ እድገት በማሳየት ላይ ይገኛል። በ2010 ዓ.ም. የካህናት ቁጥር 412, 236 ነበር። ከነዚህም ውስጥ 227, 009 የሰበካ ካህናት (diocesan priests) ሲሆኑ 135, 227 የማኅበራት ካህናት (Religious priests) ነበሩ፡፡ ይህ የካህናት ብዛት በ2009 ዓ.ም. 410, 593 የነበረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 275, 542 ሰበካውያን እና 135, 051 ደግሞ የማኅበራት ካህናት ነበሩ፡፡

የካህናት ቁጥር በእስያ በ1695፣ በአፍሪካ በ765፣ በኦሽንያ በ52 እና በአሜሪካ በ42 እድገት ሲያሳይ በአውሮፓ ግን በ905 ቀንሷል፡፡

በ2009 ዓ.ም. 38,155 የነበረው የቋሚ ዲያቆናት (permanent deacons)  ቁጥር በ2010 ዓ.ም ወደ 39,564 ማለትም በ3.7 ከመቶ ጨምሯል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 64.3 ከመቶ የሚሆኑት በሰሜን አሜሪካ 33.2 ከመቶ ደግሞ የሚገኙት በአውሮፓ ነው፡፡

በተቀራኒው ክህነት የማይቀበሉ ገዳማውያን መነኮሳት ቁጥር በ2009 ዓ.ም. ከነበረው 54, 229 በ2010 ዓ.ም ወደ 54, 665 አዎንታዊ በሆነ መልኩ አሻቅቧል፡፡ በደቡብ አሜሪካ በ3.5 ከመቶ እንደዚሁም በሰሜን አሜሪካ በ0.9 ከመቶ መቀነስ ሲያሳይ በአውሮፓ ደግሞ በነበረበት ነው ያለው፡፡ በአፍሪካና በኢሲያ ግን ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ይኸውም በአፍሪካ በ4.1 ከመቶ በእስያ ደግሞ በ3.1 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

የሴት ገዳማውያት (መነኮሳይያት) ቁጥር በጣም ግን እየቀነሰ ነው፡፡ ይኸውም ባጠቃላይ በ2009 ዓ.ም. 729, 371 የነበረው በ2010 ዓ.ም. ወደ 721, 935 ዝቅ ብሏል፡፡ በአውሮፓ በ2.9፣ በኦሽንያ በ2.6፣ በአሜሪካ በ1.6 ከመቶ የቀነሰ ሲሆን፤ በአፍሪካና በእስያ ግን በ2 ከመቶ አካባቢ እድገት አሳይቷል፡፡

ላለፉት አምስት አመታት በሰበካዎችና በገዳማት ሴሚናሪዎች (ዘርአ ክህነት) የሚማሩ የፍልስፋናና የነገረ-መለኮት ተማሪዎች ቁጥር ቀጣይ እድገት አሳይቷል፡፡ ይኸውም በ2005 ዓ.ም. 114, 439 የነበረው በ2010 ዓ.ም. በ4 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ በአንጻሩ በአውሮፓ በ10.4 እና በአሜሪካ ደግሞ በ1.1 ከመቶ የዐቢይ ዘርዓ ክህነት ተማሪዎች ቁጥር ዝቅ ብሏል፡፡ ይኸውም በአውሮፓ  ከመቶ በአሜሪካ ቀንሷል፡፡ ነገር ግን በአፍሪካ የ14.2 እና በእስያ የ13 እንደዚሁም በኦሽንያ የ12.3 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ምንጭ፡- ዜኒት የዜና ወኪል

(www.zenit.org)

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።