Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የመጀመርያው ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ

Vista D portico da ovest fullVOA — በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ አዲስ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ነው። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቶማስ አኳይናስ አሁን ለጊዜው በካቶሊክ ካቴድራል ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ያለው። በካቶሊክ እምነት የሚመራው ዩኒቨርሲቲ  አላማ  ሀላፊነት የሚሰማቸው የወደፊት የሀገር መሪዎችን ለማፍራት የታቀደ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው አለም አቀፍ የትምህርት ተቋም እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት አቡነ ብርሀነ-የሱስ ገላጸዋል። 

ዩኒቨርሲቲው የሚሰራው የኢትዮጵያ መንግስት በሰጠው 60 ኤክር መሬት ሲሆን የመጀመርያውን ደረጀ ለመገንባት መሰረተ ልማት የተጣለው ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር ላይ ነው።

 አዲስ አበባ የሚመሰረተው ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚባልውንም ዩኒቨርሲቲ የመሰረተችው ካቶሊካዊት ቤተክስትያን እንደሆነች  አስመራ ላይ የነበረው ዩኒቨርሲትም  በካቶሊክ ቤተክርስትያን እንደተመሰረተ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ብርሀነ-የሱስ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን አሁን በአዲስ አበባ የምትመሰረተው የመጀመርያው የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ግን በካቶሊክ ቤተክርስትያን የሚመራ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።   http://amharic.voanews.com/audio/audio/342599.html

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።