Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የሌሊት ወፍ ክርስቲያኖች ከመሆን ይሰውረን!

Homily pope2ቅዱስ አባታችን .ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ጥዋት በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ "የጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ ከሚሰጠው ደስታ የሚፈሩና በዚህም ሕይወታቸው ወደ መቃብር የሚጓዙ በሚመስል ሓዘን የተሸፈኑ አንዳንድ ክርስትያኖች አሉ፤ ሆኖም ጌታ ከሙታን ተለይቶ በመነሣት ዘወትር በመካከላችን ስለሚገኝ መደስት አለብን" ሲሉ የጌታ ትንሣኤ ብርሃን ከሚሰጠን ደስታ በመፍራት እንደ የሌሊት ወፍ በጨለማ ብቻ መጓዝን መምረጥ እንደሌለብን አሳስበዋል።

በዕለቱ የተነበበው ወንጌል ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ በፍራቻ በቤት ውስጥ ተዘግተው የነበሩ ሐዋርያትን "ሰላም ለእናንተ ይሁን" በማለት በመካከላቸው እንደቆመና ሐዋርያት ግን በፍራቻ ተውጠው ስለነበር ሊያውቁት እንዳልቻሉ እንዲያውም ምትሓት መስለዋቸው እንደነበር፣ ኢየሱስ እርሱ ራሱ መሆኑን ለማስረዳትና ምትሓት እንደእርሱ የተለወጠ ሰውነት እንደሌለው በመግለጥ እጆቹንና እግሮቹን በማሳየት እንዲሁም የሚበላ ነገር ያላቸው እንደሆነ በመጠየቅና ምግቡን በመብላት ሕያው እንደሆነ ሊያስረዳቸው ቢሞክርም ሐዋርያት ግን የደስታ ፍራቻ ስለነበራቸው በደስት ሊያምኑ እንዳልቻሉ የሚተርከው ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችንም በዚሁ ወንጌል ተመርኩዘው፡-
"ይህ የክርስትያኖች ሁሉ ሕመም ነው፣ የደስታ ፍራቻ አለን፣ አዎ እውነት ነው እግዚአብሔር አለ ክርስቶስም ከሙታን ተነሳ ብሎ በቀላሉ ለማሰብ እንፈልጋለን ነገር ግን ከዚያ ወደፊት ለመራመድ አንፈልግም፣ የኢየሱስ ቅርበት ፍራቻ አለን፣ ምክንያቱም ይህ ደስታ ይሰጠናል ከደስታውም እንፈራለን ለዚህም ነው ብዙ ክርስትያኖች የመቃብር ኀዘን ያህል ተላብሰው የሚንቀሳቀሱት፣ ከደስታ ይልቅ ሓዘንን ይመርጣሉ፣ በደስታ ብርሃን ከመመላለስ ይልቅ በሌሊት ብቻ ወደ ውጭ ለመውጣት እንደሚችሉ እንደ የሌሊት ወፍ በጨለመ ጐዳናዎች ለመመላለስ ይመርጣሉ፣ እነኚህ ወፎች በብርሃን ምንም ሊያዩ አይችሉም፣ በተረታዊና ምሳሌአዊ አነጋገር የሌሊት ወፎች የሆኑ ክርስትያኖች አሉን ለማለት እንችላለን፣ እነኚህ ክርስትያኖች ከጌታ ጋር በመመላለስ ከሚገኝ ብርሃን ጨለማን ይመርጣሉ ለማለት ይቻላል፣ ኢየሱስ ግን በትንሣኤ ደስታ ይሰጠናል የክርስትያን መሆን ደስታም እርሱን በቅርብ የመከተልና በብፅዕና ጐዳና በመጓዝና ከእርሱ ጋር በመኖር ይገኛል፣
"እኛም ብዙ ጊዜ ይህ ደስታ ወደኛ በሚመጣበት ጊዜ ደስ ያላለን ጊዜ አለ ምናልባት ወይንም በፍርቻ ተውጠን ወይንም አንድ ምትሃት እንደምናይ ወይንም ኢየሱስ በሌላ መንገድ እንደሚሠራ በማሰብ ዕድሉን ያልተጠቀምነበት ጊዜ አለ፣ ነገር ግን እኛ ክርስትያኖች እንዲህም ማድረግ አለብን እንላለን፣ ጌታ ኢየሱስስ የት አለ ብሎ የጠየቀን ከተገኘም ኢየሱስማ እማ በሰማይ ነው ያለው እንላለን፣ በኢየሱስ ታምናለህን? ኢየሱስን ጌታ ባንተ አምናለሁ በሕወት እንድምትኖር አምናለሁ ከሙታን እንደተነሣህና ዘወትር ከኔ ጋር እንደሆንክ ለዘለዓለምም እንደማትተውኝ አምናለሁ ብለህ ትነግረዋለህን? የአንድ ክርስትያን ሕይወት እንዲህ መሆን አለበት ሕይወታችን ከኢየሱስ ጋር በመወያየት መሆን አለበት ምክንያቱም ኢየሱስ ዘወትር ከእኛ ጋር ነው ከችግሮቻችን እንዲሁም ከመልካም ሥራዎቻችን ጋር ነው፣ አብዛኛውን ግዜ ደስተኞች የምንሆንበት ምክንያት ታውቃላችሁን ፍራቻ ስላለን ነው፣ ክርስትያኖች በመስቀል የተሸነፉ ሆኖ ስለሚሰማን ነው፣
"የመጣሁበት አገር የሚነገር አንድ ምሳሌ አለ፤ በሚፈላ ወተት የተቃጠለ እንደሆነ በመንገድ የምታልፍ ላም ባየ ቍጥር ያለቅሳል ይባላል፣ ክርስትያኖችም በመስቀሉ ድራማ ስለተቃጠሉ እዚህ እንቆማለን እርሱ በሰማይ ነው ያለው፤ ይህ ጥሩ ነው አንዴ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ እዚህ አይቅረብብን ምክንያቱም ሌላ ጊዜ የመስቀሉን ሁኔታ ለማየት አያስችለምና ይላሉ፣ ጌታ ኢየሱስ የደስታ ፍራቻ ካሸነፋቸው ከሐዋርያቱ ጋር እንዳደረገው ሁሉ አ እምሮ አችን ሊከፍትልን እንለምነው ምክንያቱም ያኔ ከብዙ ትምህርት በኋላ አ እም ሮ አቸው ተከፈተ ቅዱሳት ጽሑፎችን ለመረዳት ጀመሩ ይላል፣ አእምሮአችንን ከፍቶ እርሱ በእውነት ሕያው መሆኑ ሰውነት እንዳለው ዘወትር ከእኛ ጋር በመሆን እንደሚሸነንና ድል እንደነሳ ለመረዳት ያስችለን፣ የደስታ ፍራቻ እንዳይኖረን ጌታን እንለምነው ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ትዊተር በሚባለው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን "መጠነኛ የሆነ የአኗኗር ዘዴ በይበልጥ ይረዳናል ምክንያቱም ያለንን ሁሉ ምንም ከሌላቸው ጋር ለማካፈል ይረደናልና" ሲሉ አጭር መል እክት ጽፈዋል፣
ከቫቲካን ሬድዮ ድረ ገጽ የተወሰደ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።