Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ 50ኛው የዓለም የጥሪ ጸሎት ቀን መልእክት

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ 50ኛው የዓለም የጥሪ ጸሎት ቀን መልእክት

"ጥሪ በእምነት የታነጸ የተስፋ ምልክት"

religion 02 temp-1336898535-4faf73e7-620x348የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ:-

"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፣ እኔም አውቃቸዋለሁ፣ ይከተሉኝማል እኔም የዘለዓለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ ለዘለዓለምም አይጠፉም፤ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም፡፡ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፣ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም፡፡ እኔ እና አብ አንድ ነን፡፡" (ዮሓ 10፡27-30)

እነዚህ ቃላት የኢየሱስን ጠቅላላ መልእክት ያዘሉ የወንጌሉ ጭብጥ ናቸው፡፡ እርሱ የሚጠራን ከአብ ጋር ባለው ወዳጅነት ውስጥ ሱታፌ እንዲኖረን ነው፤ ይህም ዘለዓለማዊ ሕይወት ነው፡፡

ኢየሱስ ከወዳጆቹ ጋር ሊመሠርት የሚፈልገው ግንኙነት በእርሱ እና በአባቱ ግንኙነት አምሳል ነው፤ ይህም ግንኙነት በሙሉ እምነት ራስን አሳልፎ የሚሰጥ እና የጠለቀ አንድነት ያለበት ነው፡፡ ይህንን ጥልቅ ምሥጢር እና የወዳጅነት ምሳሌ አድርጎ ይጠቀማል፤ እረኛው ይጠራቸዋል፣እነርሱም ድምፁን ያውቁታል፣ ለጥሪውም ምላሽ በመስጠት ይከተሉታል፡፡ የድምፁ ምሥጢር የሚያሳስበን ነው፤ በእናታችን ማኅጸን ሳለን የእርሷን እና የአባታችንን ድምፅ ለማወቅ ድምፁን እናስተውላለን፤ ድምፁ ይዞት የሚመጣው ፍቅር ወይም ንቀት፣ እንክብካቤ ወይም ቸልተኛነት ሊሆን ይችላል፡፡ የኢየሱስ ድምፅ ግን ይለያል! ለይተን ያወቅነው እንደሆነ ከሞት ጨለማ በላይ በሆነ የሕይወት መንገድ ላይ ይመራናል፡፡

ነገር ግን አንዲት ቦታ ላይ ኢየሱስ በጎቹን ጠቅሶ እንዲህ ይላቸዋል፡-

"የሰጠኝ አባቴ...."(ዮሓ 10፡29)፡፡ ይህ በጣም አስፈላጊ ነጥብ ነው፤ ፍጹም ጥልቅ የሆነ ለመረዳትም የሚከብድ ነው፡፡ ወደ ኢየሱስ ከተሳብኩኝ፣ ድምፁ ልቤን ካሸፈተው፣ በእኔ ውስጥ የማፍቀር፣ የእውነት፣ የሕይወት እና የቅድስና ጥማት ያሳደረውን አብን ማመስገን አለብኝ፡፡ ኢየሱስ የዚህ ጥማት ፍፃሜ ነው! ይህ የጥሪን ምሥጢር በተለይም ደግሞ የምንኩስናን ሕይወት በተለየ መልኩ እንድንረዳው ያግዘናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ኢየሱስ ሲጠራን፣ እንድንከተለው ሲጋብዘን እርሱ መሆኑን አናስተውልም፡፡ የወጣቱ ሳሙኤል ታሪክ በሕይወታችን ይደገማል፡፡ ዛሬ ብዙ ሆናችሁ እዚህ ተሰብስባችኋል፤ ስለዚህ እኔ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እፈልጋለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በውስጣዊ ጥማታችሁ ውስጥ፣ ያለ እረፍት ሲቀሰቅሳችሁ እና በቅርበት እርሱን እንድትከተሉት ሲጋብዛችሁ የጌታን ድምፅ ሰምታችሁት ይሆን? የኢየሱስ ሐዋርያ ለመሆን ፍላጎቱ አላችሁ? ወጣት ሕይወቱን ማሳለፍ ያለበት በጥበብ በተሞላ ነገር ላይ ነው፡፡ በአትራፊ ነገር ላይ ሕይወታችሁን መመሥረት አትፈልጉም? ኢየሱስ ከአንተ ምን እንደሚፈልግ ጠይቀው እናም ቆራጥ ሁን! በቆራጥነት ጠይቀው!!!

ከማንኛውም ጥሪ በኋላም ይሁን በፊት ሁልጊዜ ጠንካራ እና ጥልቅ የሆነ የሰዎች ጸሎት አለ፤ የቤተሰቦቻችን፣ የጓደኞቻችን፣ የማኅበራችን ጸሎት ሁልጊዜ ይከተለናል፤ ለዚህም ብሎ ኢየሱስ እንዲህ ይለናል፡-

"እንግዲህ የመከሩን ጌታ (እግዚአብሔር አብን) ወደ መከሩ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑት" (ማቴ 9፡38) ፡፡ ጥሪ ሁሉ የሚወለደው በጸሎት ውስጥ እና በጸሎት አማካኝነት ነው፤ ፍሬ የሚያፈራው እና የሚጸናውም በጸሎት ብቻ ነው፡፡ በተለይ በዛሬው ዕለት በዚህ ዓመት ክህነት ለተቀበሉ ሁሉ ጸሎት እናደርጋለን፡፡

በተለይ የማርያምን አማላጅነት እንለምናለን፡፡ የእርሷን አማላጅነት እንለምን፤ እርሷ በሕይወቷ ሁሉ ለመለኮታዊ ፈቃድ "እሺ" ብላለች፡፡ እርሷ በማኅጸኗ አሳድራዋለች እናም ከሁላችን ቀድማ የኢየሱስን ድምፅ ታውቀዋለች፡፡ እናታችን ማርያም ሆይ የኢየሱስን ድምፅ በተሻለ መልኩ እንድናውቀው እና እርሱን ተከትለን በሕይወት ጎዳና እንድንራመድ እርጂን!

ስለ ሰላምታችሁ አመሰግናችኋለሁ! እንዲሁ ደግሞ ጮክ ብለን ኢየሱስን እናውጅ፤ ሁላችንም በአንድ ላይ ወደ ድንግል ማርያም እንጸልይ!

ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ፣ መንፈስቅዱስ

ይባርካችሁ እና ይጠብቃችሁ፡፡

ቫቲካን መንበረ ጴጥሮስ - ሮማ

ር.ሊ.ጳ. ፍንቼስኮስ

ትርጉም በወጣት ሳምሶን ደቦጭ - ቅ. ዮሴፍ ቁምስና ዘሲታውያን አ.አ.

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።