የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አስተምህሮ (እ.አ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2009)
- Category: ዜናዎች
- Published: Wednesday, 10 June 2009 21:11
- Written by Super User
- Hits: 3797
- 10 Jun
ቅዱስነታቸው ዛሬ በተለያዩ ቋንቋዎች ያስተማሩትና የገለጡት በንጉሥ ካርልማኝ ዘመን ስለኖረው እና ከፍተኛ ተደማጭነት ስለነበረው፣ ከቤተ ክርስትያን አበውና ጸሓፍት አንዱ ስለሆነው ዮሐንስ ስኮቱስ ኤሪጂና ነው። በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡት እንደሚከተለው ነው።
“ኤሪጂና ስለ ምሥራቁ ሃይማኖተ አበውና ትምህርተ አበው ወይም ነገረመለኮት የነበረው ፍቅርና ስሜት በተለይ ስለ ዲዮናስዩስ ኣጥንቶ ፤ ጽሑፎቹን ሁሉ በዝርዝርና በጥንቃቄ ወደ ላቲን ቋንቋ እንዲ ተረጉም ገፋፋው። እንድ ኤሪጂና እምነት ኣማኝ የሆነው ሁሉ በመለኮትነት ባህርዩን የምንሳተፈውን ኣምላክ ተመስጦአዊ ስግደት ወይም አምልኮ ማቅረብ እስክሚቻለው ድረስ ሐቅን መፈለግ ወይም መሻት የግድ ይለዋል፤ የሚል ነበር ነገር ግን የዚህ ዓይነቱ ስግደት እና አምልኮ ተመክሮ በቃላት ሊገለጥ ስለማይቻል የኤሪጂና ተዮሎጊ ቀጣይነት የሚያገኘው በአታፋሲስ ማለት ኣስቀድሞ ኣምላክ ያልሆነውን ነገር በማወቅና በማረጋገጥ ነው”።