Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የተሟላ የሰብአዊነት አድማስ

catholicuniversity2ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ልበ ኢየሱስ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ (ዩኒቨርስቲ) 88ኛው ቀን ምክንያት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት መልእክት፣ የክርስትናው እምነት የባህል እርሾ፣ ለመግባባትና ለውህደት ብርሃን፣ የእድገት በጠቅላላ ለሁሉም ለሐቀኛው ሰብአዊ ጥቅም መረጋገጥ ለሚያግዘው አውንታዊው እምቅ ኃይል ግፊት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የአንዲት አገር ተስፋ በወጣት ትውልድ ልብ ዘንድ መሆኑ አብራርተው፣ ኃሴት እና ተስፋ የተሰየመው የሁለተኛው ቫቲካን የውሳኔ ሰነድ ዋቢ በማድረግ፣ "የሰብአዊ መጻኢ መቀመጫው ለነገው ሕይወት ተረካቢው ትውልድ የሕይወትና የተስፋ ምክንያት የማስተላለፍ ብቃት ባላቸው ዜጎች እጅ ነው። በዚህ ራእይ ካቶሊካውያን መናብርተ ጥበብ ለክርስቲያናዊ መለያቸው ታማኞች በመሆን፣ የላቀው እውቀት የሚኮተኮትበት፣ ሥነ ምርምር ወደ ሥነ ጥበብ የሚያድግበት ባለ ቤት በእሴቶችና በእወቅት ደረጃ ሳይገነጣጠል የተሟላ የሰብአዊነት አድማስ የሚለው ሐሳብ ግንዛቤ የሚደረግበት ሥፍራ መሆን አለበት። አንድ መንበረ ጥበብ ካቶሊካዊ የሚያሰኘው የተሟላ ሰብአዊ ሕንጸት የሚሰጥበት ሥፍራ በመሆኑ ነው።

በእምነት አማካኝነት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከሚደረገው የተጨባጭ ግንኙነት ገጠመኝ፣ የግል ሕይወት የሚለውጥ እና ሌሎችን ለማገልገልና ለኅብረተሰብ ህዳሴ መሠረታዊ ምክንያት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት አብራርተው፣ ስለዚህ መቼም ቢሆን የክርስትናው እምነት የባህል እርሾ ለመግባባትና ለውህደት ብርሃን፣ የእድገት በጠቅላላ የሁሉም ለሐቀኛው ሰብአዊ ጥቅም መረጋገጥ ለሚለው አውንታዊው እምቅ ኃይል ግፊት ነው። ተጽእኖ ሳይሆን ለሥነ ሰብእና ጥናትና ለሥነ ትምህርት አሰጣጥ መሠረትም ነው። ይህ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ ኃላፊነት በተለያዩ ሰበካዎች የመናብርተ ጥበብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መርሃ ግብር እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የሚያሳስብ ነው። ቤተ ክርስቲያን የሰው ልጅ በሙያ ዘርፍ በተሰማራበት፣ በሥራ መስክና በሚማርበት ሥፍራ ሁሉ በመገኘት ቃለ ወንጌል ለግላዊ እና ለማኅበራዊ ኅልውና መሠረት መሆኑ ለመመስከር እና ለማብሠር ተጠርታለች። ወንጌል ብርሃንና ለመጻኢው ሰብአዊ ጥያቄ መፍትሄ የሆነው መከተል ያለበት እውነተኛውን መንገድ ለመለየት የሚያበቃ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።