Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ር.ሊ.ጳ. በሚስዮናዊው መገደል የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

VATICAN CITY, SEPT. 22, 2009 (Zenit.org).- ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ባለፈው ቅዳሜ ብራዚል ውስጥ በተገደሉት ጣልያናዊ ሚስዮናዊ አባ ሩጄሮ ሩቮሌቶ ሞት ምክንያት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ። ለማናዎስ ሊቀ ጳጳሳት ሉይስ ሶዋሬስ በላኩት የቴሌግራም ኀዘን መግለጫቸው ውስጥ ይህን "ሰላማዊ የወንጌል አገልጋይ ላይ ደስ የማይልና የጭካኔ ድርጊት" በጥብቅ በማውገዝ በጸሎት መንፈሳዊ አብሮነታቸውን ገልጸዋል።

አባ ሩቮሌቶ የተገደሉት በሰሜን ብራዚል

ማናዎስ በሚባል አካባቢ በሚያገለግሉበት ቁምስና በቅድስት ኤቬሊና ሲሆን ፖሊስ በመጀመሪያ ግድያውን ዘራፊዎች የፈጸሙት መሆኑን ቢጠቅስም ዛሬ የጣልያን ጳጳሳት ጉባኤ ዜና ወኪል ግን "ለረጅም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ወንጀሎችን፣ የአደንዛዥ ዕፅና የሰውን ብዝበዛ ስለምትቃወም በማናዎስ አካባቢ ቀጣይ የሆነ ቤተ ክርስቲያንን የማስፈራራት ሁኔታዎች" መኖራቸውንና የኚህ ካህን መገደል እውነትም የዚህ ድርጊት ክፍል የመሆኑ ርግጠኝነት መጨመሩን ዘግቧል።

እ.ኤ.አ. ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ አባ ሩቮሌቶ "አደንዛዥ ዕፅና ሴትኛ አዳሪነት እንደ ኅብረተሰብ አደጋ" የገለጹባቸው ሰነዶችና ቃለ መጠይቆች እንዳሉም ታውቋል።

አባ ሩቮሌቶ በ1957 ዓ.ም. ጣልያን ቬኑስ አጠገብ ተወልደው በ1982 ዓ.ም. ሢመተ ክህነት የተቀበሉ ሲሆን ልኡከ ወንጌል ሆነው ወደ ብራዚል የተጓዙት ከስድስት ዓመታት በፊት ነበር።

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።