Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ሥነ ሕይወት በክርስትያናዊ አመለካከት

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ለመጪው ዓመት ማለትም 2010 እ.ኤ..አ ጥር አንድ ቀን የሚያስተላልፉት ዓለም አቀፍ መልእክተ ሰላም ፡"ሰላምን ለማፍራት ከፈለግክ አከባቢህን ጠብቅ" የሚል መሆኑ በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት አስታወቀ።


መልእክተ ሰላሙ የዚች የምንኖርባት ምድር መጻኢ ዕድል በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃለፊነት በመውሰድ እንድትጠበቅ የሚጠይቅና ሰላም ከሰው ክብር እና ከአከባቢ ጋር የተሳሰረ መሆኑን የሚያመለክት መልእክተ ሰላም መሆኑም ተመልክቷል። 

በቅርቡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ የጻፉት “ካሪታስ ኢን ቨሪታቴ” - ፍቅርን በእውነት- የሚለውን ሐርያዊ መልእክት ስንመለከት መልእክቱ ለአከባቢ ጥበቃ ትኩረት የሰጠ መሆኑ የሚታወስ ነው ። 

አከባቢ በአግባቡ ካልተያዘ በዓለም ሕዝቦች ላይ ሁከት መቀስቀስ ስለሚችል ከፍተኛ ትኩረት የሚያሻው መሆኑን የጠቀሰው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልእክተ ሰላም በሕዝቦች መካከል ፍትሕ እና ትብብር እንደሚያስፈልግ አበክሮ ያሳስባል።

የዚህ ዘመን ኅብረተሰብ ለፍጆታ እና ሀብት ለማካበት የሚከተለው የሕይወት ዘይቤ እና አኗኗር ተሐድሶ እና ለውጥ እንደሚያሻው የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ሐዋርያዊ መልእክት እንደሚያመልክትም የሚዘነጋ አይደለም።

ሐዋርያዊ መልእክቱ የዓለም ኅብረተሰብ የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረግ ዓለም ፍትሕ ከሌለ ሰላም ስለማይገኝ ሰላም ላይ ማተኮሩ የፍትህ እጦት መሠረታዊ መፍትሔ እንዲገኝለት የሚጠይቅ እንደሆነም የሚታወቅ ነው። 

ሐዋርያዊ መልእክቱ የሰው ልጅ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ በኩል እጅጉን ባደገበት ጊዜ ተፈጥሯዊ ሀብቶች ለሁሉም እንዲዳረስ ማድረግ እንደሚገባው በአጽንኦት በመጠየቅና ቤተክርስትያን የፍጥረት ሁሉ ኃላፊነት እንዳላትም አመልክቶ፡ የሰው ልጅ ራሱን በራሱ እያወደመ ባለበት ባሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያን ችላ ማለቱ እንደማይቻልት ይገልጻል።

ፍጥረት ሁሉ ለመጠበቅ የስነ ምግባር ባለቤት የሆነ ማኅበረ ሰብ እንደሚያስፈልግም በማሳሰብ የሰው እና የፍጥረት ሥነ ሕይወቶች ተፈጥሮአዊ ሂደቶች መከተል ሲገባቸው በሰው ሠራሽ ድርጊቶች ሲታወኩና የሰው ተፈጥሮአዊ እድገት ሲተጓጐል እንደሚታይም ሐዋርያዊ መልእክቱ እንደሚያስገነዝብ ይታወቃል። 

ሐዋርያዊ መልእክቱ የተፈጥሮ አያያዝ ሥርዓት መስተካከል እንደሚያሻው ይጠቁም እና የአከባቢ ተፈጥሮ እንዲጠበቅ በመጠየቅ ፡ የሚቀየሱ ሕጎች ግን ሰብአዊ ክብር ለመታደግ የማይረዱ ስለሚሆኑ ሁለቱም ነገራት እርስ በርሳቸው ተጻራሪ እንደሚሆኑ ይገልጣል።

 

 

በክርስትያናዊ አመለካከት ተፈጥሮ እንደ አጋጣሚ የተገኘ እና ያለ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑ ሐዋርያዊ መልእክቱ እንደሚያሰምርበትም ያታወቃል። 

 

 

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።