Map St Joseph Cistercians

Top Panel

በኢራቅ አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ ትላልቅ ግንቦች እየተገነቡ ነው

ለገና በዓል ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱትን ምዕመናን ከጥቃት ለመከላከል የኢራቅ መንግሥት በባግዳድና በሞሱል በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ እስከ አሥር ጫማ (3 ሜትር አካባቢ) የሚደርሱ ከፍታ ያላቸውን የአርማታ አጥሮችን እየገነባ ነው፡፡ ይህንን እርምጃ ሊወስድ የቻለው ከፊታችን ያለው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለመጣው በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደታሰበ ለሚያመለክቱ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ የካቶሊክ የዜና ወኪል /CNA/ ከኢራቅ ባግዳድ ዘግቧል፡፡

በተለምዶ እንደነዚህ ያሉ ክብረ በዓላት በአዳራሽና በመናፈሻ ቦታዎች የሚካሄዱ ዝግጅቶችን የሚያካትቱ ሲሆን ዘንድሮ ግን

ከደህንነት ስጋት የተነሳ የቤተክርስቲያን መሪዎች በጠየቁት መሠረት እነዚህ ዝግጅቶች በባግዳድና በሞሱል ቁጥራቸው እንዲቀንሱ ተደርጓል፡፡

“የሕዝቡ ሐዘን በየቦታው ነው፤ ጥርጣሬም እንዲሁ በየቦታው ሰፍኗል፡፡ በሁሉም ሰው አንደበት የሚነሳ ጥያቄ ‘ቀጣዩ ምን ይሆን?’ የሚል ነው” ይህንን የተናገሩት የኤርቢል ሊቀ ጳጳስ ባሻር ዋርዳ  Charity Aid to the Church in Need ለተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ነው፡፡ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ ይታያል፤ ቢሆንም ቅሉ ሕዝቡ የፈለገው ነገር ይምጣ በሚል ጽናት የገናን ቅዳሴ ለማስቀደስ ወስኗል፡፡

ወደ አበያተ ክርስቲየናት የሚወስዱ መንገዶች መሣሪያ በያዙ ፖሊሶች ጥበቃ ስር ሲሆኑ በየመግቢያውም በጥበቃ መሳሪያ የታገዘ ፍተሻ ይደረጋል፡፡ ሊቀ ጳጳስ ዋርዳ ሁኔታውን ማለትም ግንቡንና የደህንነት ጥበቃውን ሲገልጹ ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን ሳይሆን ወደ ወታደራዊ ካምኘ እንደሚገቡ ነው የሚሰማቸው፡፡ ሆኖም ግን የኢራቅ መንግሥት ደህንነትን ለማሻሻል የወሰደውን እርምጃ አወድሰዋል፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ቆሞሳትን የደህንነት ግንቡን ወደውት እንደሆነ ጠይቀው ነበር፡፡ በብዙ ቆሞሳቶች ዘንድ ይሁንታን ያገኘ ሲሆን አንዳንዶች ግን ድርጊቱ ቀድሞውኑ ፍራት ውስጥ የነበረውን የክርስቲያን ማህበረሰብ ተጽዕኖ ያደርግበታል የሚል ሃሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ከሁለት ወራት በፊት በባግዳድ በእመቤታችን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ውስጥ በተፈፀመው ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ 58 ሰዎች ሲገደሉ 70 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ በዚህ አመጽ ምክንያት ቢያንስ 2000 የሚሆኑ ክርስቲያኖች ከሞሱልና ከባግዳድ ሸሽተዋል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ግብረሰናይ ድርጅት የአደጋ ጊዜ እርዳታ ለተፈናቀሉ ክርስቲያኖች እያደለ ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ በዚሁ ጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑትና ለቤተሰቦቻቸው እርዳታን አዘጋጅቷል፡፡ ሊቀ ጳጳስ ዋርዳ እርዳታውን በደስታ ተቀብለው “እነርሱ ማለትም ተጐጅዎቹ በጣም ደስ ብሏቸዋል ከእነርሱ በተሻሉት   እድለኞች ዘንድ በመዘከራቸው ብርታትን አግኝተዋል” በማለት በተቀባዮቹ ዘንድ ያለውን ስሜት ገልጸዋል፡፡


ምንጭ:-  Catholic Online

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።