Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ጸረ ክርስትያን አመጽ በፓኪስታን

ቫቲካን ሬድዮ - ባለፈው ዓርብ በፓኪስታን ፑንጃብ መንደር ሙስሊሞች የዓርብ ጸሎት አድርሰው በመመለስ ላይ እያሉ በማበር ባንድ ክርስትያን ምእመን እና ባንዲት ሙስሊም መካከል የተፈጠረው ወዳጅነት እና ፍቅር በመቃወም በክልሉ አቅራቢያ የሚገኘውን ቤተ ክርስትያን በእሳት ማጋየታቸው ሲገለጥ፣ በዚህች አገር አክራሪያን ሙስሊሞች በተከታታይ የሚፈጽሙት ጸረ ክርስትያን አመጽ ገና እንዳልተገታ ለማወቅ ተችሏል።

በመቀጠልም አክራሪያኑ...

የአንዳንድ ክርስትያን ምእመናን መኖሪያ ቤቶች እና እንዲሁም የክልሉ የፕሮቴስታንት እና የካቶሊክ ምእመናን የጸሎት ቤቶችን በእሳት ማጋየታቸውን የፓኪስታን የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትሕና የሰላም ድርገት ሊቀ መንበር አባ ኤማኑኤል ዩሳፍ ማኒ በመግለጥ፣ በፓኪስታን የሚገኙ የሁሉም ሃይማኖቶች ምእመናን በጋራ በሰላም አብሮ የመኖር ጉዳይ እንዲረጋገጥ እና ጸረ ክርስትያንም ሆነ የማንኛውም ዓይነት ሃይማኖት ምእመን ተቃውሞ እንዳይከሰት በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሂዱ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸውን ኤሺያን ኒውስ የዜና አገልግሎት ያሰራጨው ዜና ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. ባለፈው ወር መግቢያ በጎጅራ ከተማ አሥራ አንድ ክርስትያኖች በአክራሪያን ሙስሊሞች ከተገደሉ ወዲህ፣ የክልሉ ነዋሪ የሆነው ክርስትያን ማኅበርሰብ ቤቱን እና ንብረቱን እየተወ ለመፈናቀል አደጋ መጋለጡ እና በዚህ 2009 ዓ.ም. ውስጥ 9 ጊዜ ጸረ ክርስትያን እና አቢያተ ክርስትያን አመጽ መፈጸሙንና  ችግሩ ገና አሁንም እየቀጠለ መሆኑን  አቨኒሬ የተሰኘው የኢጣሊያውያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ ገልጿል።

 


 


አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።