Map St Joseph Cistercians

Top Panel

“ንስሐ መግባትን አትፍሩ

ኢየሱስ ክርስቶስ የሥጋ እና የነፍስ ቋሚ እና ዘላለማዊ ወጌሻ ነው”

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ

pope confessesከአርባ ጾም መግቢያ በፊት በነበረው የረቡዕ ዕለት መደበኛው የአስተምሕሮ ጊዜያቸው ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በሮም የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡትን ምእመናን ወደ ንሰሐ ለመሄድ ደፋሮች እንዲሆኑ አበረታተዋቸዋል፡፡ ር.ሊ.ጳ. ፍርንችስኮስ በዚሁ ጊዜ “ሁሉም ሰው እንዲህ ይላል፡- መቼ ነበር ለመጨረሻ ጊዜ የተናዘዝኩት? እናም ይህ ጊዜ ረዝሞ ማስታወስ ሲያቅታችሁ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ አታብክኑ ! ሂዱ ፣ ካህኑ መልካም መሳርያ ይሆናችኋል ኢየሱስ በዚያ አለ% ከካህኑ በላይ በልቡ የሚቀበላችሁ እርሱ ነው፡፡ በብዙ ፍቅር ይቀበላችኋል! ስለዚህ ደፋሮች ሁኑ ወደ ንስሐ ሒዱ! ” በማለት ምእመናንን አነቃቅተዋል፡፡

በምሥጢረ ንስሐ ዙሪያ ያለውን የምእመናን ፍራቻ እና ጥርጣሬ በመገንዘብ ር.ሎ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የሚከተለውን ምክር አስተላልፈዋል “አንዳንድ ሰው ኃጢአቴን የምናዘዘው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ይላል፡፡ ልክ ነው እግዚአብሔርን ይቅር በለኝ ብላችሁ ኃጢአታችሁን መናገር ይቻላል% ነገር ግን ኃጢአቶቻችን ወንድሞቻችንን የሚገ:ዱ እና ቤተክርስቲያንን የሚያቆስሉ ናቸው፡፡  ስለዚህ ይቅርታችን ከወንድሞቻችን እና ከቤተክርስቲያን መጀመር ያለበት ለዚሁ ነው፡፡ ይህም የሚቀርበው በካህኑ አማካኝነት ነው፡፡ የምሥጢሩ አከባበር ፍጹም ምሥጢራዊ እና የግል ቢሆንም በቤተክርስቲያን ኲላዊነት ውስጥ ሥር የሰደደ ነው፡፡ ይህም እንለወጥ ዘንድ የምታጅበንን ቤተክርስቲያንን ያስታውሰናል ፡፡”

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ ቀጥለው ስለ ይቅርታ ወይም ስለ ኃጢአት ሥርየት አስረድተዋል “ ይቅርታ እኛ በቀላሉ ለራሳችን ልናበረክት የምንችለው ሥጦታ አይደለም ፡፡ ይልቁንም ይቅርታ እንጠይቃለን፣ የምንጠይቀውም ከሌሎች ሰዎች ነው % በዚህ ዓይነት በካህኑ ውስጥ ያለውን ኢየሱስን በምሥጢር ንስሐ ይቅርታ እንጠይቀዋለን፡፡ ይቅርታ የድካማችን ደሞወዝ ሳይሆን ሥጦታ ነው፡፡ በውስጣችን ጸጋ እና ምሕረት ሞልቶ ይህንን ሥጦታ የሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ ከተሰቀለው እና ከሞተው ኢየሱስ ክርስቶስ ልብ ውስጥ ያፈስስልናል፡፡” ካሉ በኋላ ር.ሊ.ጳ. ብዙ ሰዎች ኃጢአታቸውን ለመናዘዝ ያላቸውን ሐፍረት አስመልክተው የሚከተለውን ምክር አስተላልፈዋል ፡- “አንዳንድ ሰዎች ‘ አባ በጣም ያሳፍረኛል’ ሲሉ እሰማለሁ፡፡ ነገር ግን ሐፍረት በራሱ አስፈላጊ ነው፣ ሐፍረት ጤናማ እስከሆነ ድረስ መልካም ነው % በመልካም መንገድ ይበልጥ ትኅትና ያላብሰናል ፡፡” ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በተደጋጋሚ ልዩ ትኩረት በመስጠት “ንስሐ ለመግባት አትፍሩ! ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ከዚህ ገ:ን ለገ:ን ደግሞ “አንድ ሰው ንስሐ ለመግባት ሲሰለፍ ሐፍረት ሊሰማው ይችላል፡፡ ነገር ግን ንስሐ ገብቶ ከጨረሰ በኋላ ሲመለስ በነጻነት፣ በፍቅር፣ ደስ በሚል ስሜት፣ በይቅርታ፣ በቆንጆ ልብ ይመለሳል፡፡ የንሰሐ ምሥጢር የፈውስ ምሥጢር ነው፡፡ እኔ ንሰሐ ስገባ ለፈውስ ብዬ ነው % ጤናው የተቃወሰውን ልቤን እና ነፍሴን ለመፈወስ ብዬ ነው ፡፡ ” ኢየሱስ ክርስቶስ ሽባ የነበረውን ሰው የፈወሰበትን ታሪክ ጠቅሰው ከምሥጢረ ንስሐ ጋር ያለውን ጥልቅ ግንኙነት በማስገንዘብ በይቅርታ እና በፈውስ መካከል ያለውን አንድነትና ግንኙነት ጠቁመዋል፡፡

        ኢየሱስ ክርስቶስ የሥጋ እና የነፍስ ቋሚ እና ዘላለማዊ ወጌሻ ነው፡፡ በሉቃስ ወንጌል የምናገኘው መልካም አባት የጠፋውን ልጅ ለመቀበል የተዘረጉት እጆቹ የክርስቶስን አባታዊ እቅፍ ያስታውሱናል፡፡ ከዚህ በኋላ ር.ሊ.ጳ. ጠንክር ባለ መልኩ ይህንን አስተላልፈዋል “ወደ ንስሐ ስንሄድ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ያቅፈናል፡፡”

ትርጉም በመ/ር ሳምሶን ደቦጭ - ቅ. ዮሴፍ ቁምስና ዘሲታውያን አ.አ.

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።