Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ማንም ሰው ብቻውን እንዳይሆን፤ ማንም ሰው እንዳይነጠል፤ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር

ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ለነዳያን በሚያዘጋጁት የምሳ ግብዣ ላይ ከ2000 ድኆች ጋር ምሳ በልተዋል። ተጋባዦቹ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ስደተኞችና ምንም የሌላቸው የሮማ ድኆች ናቸው። ቅዱነታቸው እቦታው በደረሱበት ጊዜ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የማኅበሩ መሥራች ፕሮፈሰር ኣንድረያ ሪካርዲ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓጝልያዞ ከአንድ ሮም ሴትና የሰነጋል ስደተኛ ወጣትና የተርኒ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓጝልያ እና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ሞረቲ ከድኆቹ አብረው ተቀብለዋቸዋል፣

ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው፣ “ብፁዕ አባታችን ይህንን ቦታ እንደቤታቸው ከሚቈጥሩት የዚህ ልዩ ኅብረተሰብ ጓደኛ በመሆን ከእኛ አብረው ሲበሉ፣ እርስዎን በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር ማእድ ከእኛ ጋር ማየት ትልቅ ደስታ ይሰማናል”፣ ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠው በቦታው በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ እንደሚመገቡ፣ ሰዎቹም በተለያዩ ችግሮች የተጠቁ መሆንቸውን አልደበቁም፣ እንደ ቤተሰብ ሆነው መግብ ብቻ ሳይሆን በፍቅርና በጓደኝነት እንደሚኖሩም ኣብራርተዋል። የድኆች ጓደኛና አለኝታ መሆን ክርስትያንን ያሳድጋል በማለት ትልቁ ጎርጎርዮስ ድኆችን በማገልግል ኃይልና ብርታት እንደሚገኝ ያስተማረውን አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው ከተለያዩ ኣገሮች ከመጡ ስደተኞች በተለይም በማኅበሩ ብተደራጀ የጣልያነኛ ቋንቋ ትምህርት የሚከታተሉትን ትንሽ ቡድን ሲያነጋገሩ፣ “ቋንቋ በአንድነት ለመኖርና አንድ ቤተ ሰብ ለመሆን የመዋሃሃድ ቍልፍ ነው፣ በቋንቋ ባህልና የባህል ታሪክ እንዲሁም የባህሉ ዕጣ ፈንታ ተደብቆ ይገኛል፣ ይህንን የቋንቋ ትምህርት ዕድል ላበረከተላችሁ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር አመሰግናለሁ”፣ ሲሉ የተሰጣቸውን ዕድል እንዲጠቀሙበት አደራ ብለው፣ ካበረታቱ በኋላ ማኅበሩ የሠራውን የቤተ ሰቡ የልደት የቤተ ልሔም ግርግም አይተው ምሳ በልተዋል። በምሳ ጊዜ ከቅዱስነታቸው የተለያየ ችግር ያላቸውና ከተለያዩ ወገኖች የመጡ 12 ሰዎች በአንድ ጠረጲዛ ተመግበዋል።

ቅዱስነታቸው እንደ ኢየሱስ ልዩ ጓደኞች የጠርዋቸው የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ አብረው በመመገባቸው የተሰማቸውን ደስታና እርካታ ገልጠዋል። ግብረ ሠናዩንም እንዲህ ሲሉ አመጕሰውታል፣ “ኢየሱስን በሚከተሉ የዘመናችን ሓዋርያት በሚደረግ ግብረ ሠናይ እግዚአብሔር በመጀመርያ እንደወደደንና ገናም እንደሚወደን የሚያሳይ እውነት ግልጽ ይሆናል፣ ለዚህም መልስ የምንሰጠው በፍቅር ነው፣ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ይህንን ምግባረ ሠናይ ለማን መሆኑን ለመግለጽ ደግሞ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። እነዚህን ቃላት ስንሰማ ኢየሱን ከሚያመለክቱ ከተቸግሩት ጋር አጋርነት እንድናሳይ አይቀሰቅስምን፣ ጓደኝነትና ኣጋርነት ብቻ ሳይሆን ቤተ ሰብ መሆናችንስ አይሰማንምን” ብለዋል።

ስደትና ችግርን አስመልክተውም፣ የኢየሱስ ቤተሰብም ችግር አጋጥሞታል፣ ገና ቤተሰብ ለመመሥረት ሲጀምሩ በቤተልሔም የሚቀበላቸው አጥተዋል፣ ወደ ግብጽ እንዲሰደዱ ተገደዋል፣ እናንተ የስደትን ችግር ጥሩ ኣርጋችሁ ታውቃላችሁ፣ በችግርና በመከራ ብትገኙም እዚህ እናንተን ለማንከባከብና ለማገልገል የተዘጋጁ የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት የቅዱስ ኤጅድዮ ማኅበር አለላችሁ፣ ዛሬ እዚህ በየቤታችሁ ልታገኙት የምትችሉትን ታገኛላችሁ። ይህ የእውነተኛ ቤተ ሰብ ቤት ነው፣ በቤተሰብ እኔ የሚለው በእኛ ይተካል፣ ማኅበር ይቆማል፣ የፍቅር ማኅበር ስለሆነም እግዚአብሔር ማሃከላችን ይገኛል።

ኢየሱስ የሚሰቃዩትንና ችግር ያላቸውን ሰዎች የሱ ጓደኞች እንደሚያደጋቸውና እንደሚወዳቸው በመረዳት እሱን በመከተል ለሁሉም በተለይም ለተጐዱትና ረዳት ለሌላቸው ለመርዳት ዝግጁነታችን ማረጋገጥ እንድለብን አሳስበዋል፣ “ማንም ሰው ብቻው እንዳይሆን፣ ማንም ሰው እንዳይነጠል፣ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር” ሲሉም አደራ በልዋል።

Xmas_Lunchቫቲካን ራድዮ - ቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የልደት በዓልን ምክንያት የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር በየዓመቱ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ለነዳያን በሚያዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ በመገኘት ቅዱስ አባታችን .ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትላንትና ከ2000 ነዳያን ጋር ምሳ በልተዋል። ተጋባዦቹ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ስደተኞችና ምንም የሌላቸው በሮማ የሚኖሩ ነዳያን ናቸው። ቅዱነታቸው በስፍራው በደረሱበት ጊዜ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር መሥራች ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ፣ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓግልያዞ፣ የሰኔጋል ስደተኛ ወጣትና የተርኒ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓግልያ እና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ሞረቲ ከተቀሩት ነዳያን ጋር በመሆን አብረው ተቀብለዋቸዋል፣

ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው፣ “ብፁዕ አባታችን ይህንን ቦታ እንደቤትዎ በመቁጠርና የዚህ ልዩ ኅብረተሰብ ጓደኛ በመሆን ከእኛ ጋር አብረው በመሳተፍዎና እርስዎን በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር ማእድ ከእኛ ጋር በማየታችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል”፣ ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠው በቦታው በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ ነዳያን እንደሚመገቡ፣ ሰዎቹም በተለያዩ ችግሮች የተጠቁ መሆንቸውን ገልጠው፣ እንደ ቤተሰብ ሆነው መመገብ ብቻ ሳይሆን በፍቅርና በጓደኝነት እንደሚኖሩም ኣብራርተዋል። የድኆች ጓደኛና አለኝታ መሆን ክርስትያንን ያሳድጋል በማለት ትልቁ ጎርጎርዮስ ነዳያንን በማገልግል ኃይልና ብርታት እንደሚገኝ ያስተማረውንም አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው ከተለያዩ ኣገሮች ከመጡ ስደተኞች በተለይም በማኅበሩ በተደራጀ...

ቅዱስነታቸው እንደ ኢየሱስ ልዩ ጓደኞች የጠርዋቸው የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ አብረው በመመገባቸው የተሰማቸውን ደስታና እርካታ ገልጠዋል። ግብረ ሠናዩንም እንዲህ ሲሉ አመጕሰውታል፣ “ኢየሱስን በሚከተሉ የዘመናችን ሓዋርያት በሚደረግ ግብረ ሠናይ እግዚአብሔር በመጀመርያ እንደወደደንና ገናም እንደሚወደን የሚያሳይ እውነት ግልጽ ይሆናል፣ ለዚህም መልስ የምንሰጠው በፍቅር ነው፣ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና ብሏል። ይህንን ምግባረ ሠናይ ለማን መሆኑን ለመግለጽም ደግሞ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። እነዚህን ቃላት ስንሰማ ኢየሱን ከሚያመለክቱ ከተቸግሩት ጋር አጋርነት እንድናሳይ አይቀሰቅስምን፣ ጓደኝነትና ኣጋርነት ብቻ ሳይሆን ቤተ ሰብ መሆናችንስ አይሰማንምን” ብለዋል።

ስደትና ችግርን አስመልክተውም፣ የኢየሱስ ቤተሰብም ችግር አጋጥሞታል፣ ገና ቤተሰብ ለመመሥረት ሲጀምሩ በቤተልሔም የሚቀበላቸው አጥተዋል፣ ወደ ግብጽ እንዲሰደዱ ተገድደዋል፣ እናንተ የስደትን ችግር ጥሩ ኣርጋችሁ ታውቃላችሁ፣ በችግርና በመከራ ውስጥ ብትገኙም እዚህ እናንተን ለመንከባከብና ለማገልገል የተዘጋጁ የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት የቅዱስ ኤጅድዮ ማኅበር አለላችሁ። ዛሬ  በየቤታችሁ ልታገኙት የምትችሉትን እዚህ ታገኛላችሁ። ይህ የእውነተኛ ቤተ ሰብ ቤት ነው፣ በቤተሰብ እኔ የሚለው በእኛ ይተካል፣ ማኅበር ይቆማል፣ የፍቅር ማኅበር ስለሆነም እግዚአብሔር በመካከላችን ይገኛል።

ኢየሱስ የሚሰቃዩትንና ችግር ያላቸውን ሰዎች የሱ ጓደኞች እንደሚያደጋቸውና እንደሚወዳቸው በመረዳት እሱን በመከተል ለሁሉም በተለይም ለተጐዱትና ረዳት የሌላቸውን ለመርዳት ዝግጁነታችን ማረጋገጥ እንድለብን አሳስበዋል፣ “ማንም ሰው ብቻውን እንዳይሆን፣ ማንም ሰው እንዳይነጠል፣ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር” ሲሉም አደራ በልዋል።

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።