በአባ ፍስሐ ገብረ አምላክ አማልጅነት ከእግዚአብሔር ጸጋን ለመለመን የሚደረግ ጸሎት
- Category: እኛ ማነን
- Published: Wednesday, 29 December 2010 13:21
- Hits: 8886
አባ ፍስሐ ገብረ አምላክ የመጀመሪያው ሲታዊ ሓበሻ
አባ ፍሥሐ ገብረአምላክ ሰኔ 16 ቀን 1887 ዓ.ም. በኤርትራ በከረን አካባቢ “ዓዲ በሃይማኖት” በምትባል መንደር ተወለዱ። በከረን ቅ.ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተጠምቀው ኃይለማርያም ተባሉ። ከልጅነታቸው ጀምሮ ክፋትን የሚጠሉና ሰብአዊ ርኅርኄ ያላቸው ሰው ነበሩ። በጽኑ በሽታ በሥጋ ሞት እስካረፉባት እድሜያቸው በነበራቸው የሕይወት ቅድስና መልካም ምስክርነትን ሲሰጡ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ይህ ምስክርነታቸው ለብዙኀን ትሩፋት ይሆን ዘንድ ሕይወታቸው በቤተ ክርስቲያን ወጋዊ የቅድስና ሂደት ላይ ይገኛል...ተጨምሪ የሕይወት ታሪካቸውንና የቅድስና ገድላቸውን ለማንበብ ይህን ይጫኑት በአማልጅነታቸው ከእግዚአብሔር ጸጋን ለመለመን የሚደረገውን ጸሎት ለማድረስ ከታች ይመልከቱ። (ሐምሌ 2000 ዓ.ም. ለዕረፍታቸው 75ኛ ዓመት በካዛማሪ የተደረገው ቅዳሴ ፎቶዎች)
የእግዚአብሔር አገልጋይ አባ ፍስሐ ገብረአምላክ። |
አባ ፍስሐን ብፁዕ ለማለት በቤ/ያን የሚያስፈልገው ቅድመ ጥናት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በርሳቸው አማላጅነት ከእግዚአብሔር ተአምር ማግኘት ከተቻለ በይፋ ብፁዕ ይባላሉ ለዚህም ያግዝ ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ፈቃድ በአማላጅነታቸው ጸጋ ለማግኘት የሚደረገው ጸሎት አነሆ:-
|
{jathumbnail off}