እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ፀሐይን የለበሰችው ሴት (ራእ 12) - ክፍል አንድ

ፀሐይን የለበሰችው ሴት ( ራእ 12) - ክፍል አንድ

Filseta_LeMariamበምዕራብ ቤተክርስቲያን የላቲን ሥርዓተ አምልኮ ውስጥ ራእዩ ለዮሐንስ 12፡1 ከ1951 ዓ.ም. ጀምሮ ለፍልሰታ ማርያም መሥዋዕተ ቅዳሴ መክፈቻ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በ1969 አዲስ ግጻዌ በታተመበት ጊዜ የመሥዋዕተ ቅዳሴ የቃል ክፍል የመጀመርያ ንባባት ብሎ ራእ 11፡19ሀ ፤ 12 ፡1 ፤3-6 እና 10 ሀለ አስቀመጠልን፡፡ በ1950 ዓ.ም ር.ሊ.ጳጳሳት ፒዮስ የእመቤታችንን ፍልስት በተመለከተ ባወጡት ድንጋጌ ላይ እንዲህ የሚል ትርጉም እናገኛለን፡፡‹‹ በእመቤታችን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ላይ ጥናታቸውን ያደረጉት ሊቆች ፍልሰታዋን በብሉይ ኪዳን ውስጥ በተምሳሌታዊ አቀራረብ የሚገኝ ብቻ ሳይሆን በፓትሞስ ደሴት ላይ ሐዋርያዊ ቅዱስ ዮሐንስ በጥቅል በተመለከታት ፀሐይን የለበሰች ሴት ተመስሎ አግኝተውታል፡፡››[1] እዚህ ላይ ግን ር.ሊ.ጳ. በየትኛውም መልኩ ቢሆን የእመቤታችን ፍልሰት አስተምህሮ በራእይ 12፡1 ላይ ይገኛል እያሉ አለመሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን በመካከለኛው ዘመን ( ልክ እንደአንድ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት) ይህ ጥቅስ ስለ እመቤታችን ፍልሰት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡

ይህቺ ፀሐይን የለበሰች ሴት ማነች?

ካቶሊካዉያን ያልሆኑ ሰዎች ሴቲቱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምሳሌ ናት፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኘው የእስራኤል ሕዝብ ምልክት ወይም በአዲስ ኪዳን የምትገኘዋ ቤተክርስቲያን ምልክት አልያም ደግሞ ሁለቱም አጣምራ የያዘች ትሆናለች እንጂ በምንም መልኩ የአምላክ እናት ድንግል ማርያምን አትወክልም ይላሉ፡፡ ማክሲ ቱሪያን (Max Thurian) የተባለው ሰው ከእነዚህ በተለየ መንገድ ምስሉ በመጀመርያ እስራኤልን ለመወከል የቆመ ሲሆን ከዚህ በኃላ የድንግል ማርያም ገጽታ በመላበስ የክርስቲያን ቤተክርስቲያንን የሚወክል ምስል ነው ብሎ ያስባል፡፡

በሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሁለት ጸሐፍት ሴቲቱ ልትወክል የምትችለው እመቤታችን ድንግል ማርያምን ብቻ ነው በማለት ይገምታሉ፡፡ ቤተክርስቲያንን የሚወክል አንዳችም ነገር በምስሉ ውስጥ አናገኘኝም በማለት የቀደሙትን ሃሳቦች ውድቅ ያደርጋሉ፡፡ ክርክራቸው የሚነሳው ሴቲቱ መሲህ በመውለዷ ላይ ተመርኩዞ ነው (ራእ 12፡5) በዚህም ሴቲቱ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ልትሆን አትችልም ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የመጣችው ከክርስቶስ ነው፡፡ ደግሞ የሁሉም ክርስቲያን አማኞች እናት (12፡7) ስለሆነች በምንም መልኩ የአይሁድ ምኩራብ ምሳሌ ልትሆን አትችልም፡፡ በራእይ ለዩሐንስ መጽሐፍ ይህ ምኩራብ ዘወትር ለክርስቲያን ቤተክርስቲያን እንደ ጠላት ተደርጎ ይቀርብ ነበር፡፡ (2፡9፣3፡9) የክርስቶስ እናት እና የአማኞች ሁሉ እናት ተብላ ልትጠራ የምትችለው ማርያም ብቻ ነች!

ይህንን ጽሑፍግለጽ በሆነ መልኩ የሚቀበሉት ሰዎች በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡

1) ጸሐፊው ቤተክርስቲያንን እየገለጸ ነው፣ ይኸውም የእመቤታችንን ምሳሌ ለቤተክርስቲያን መግለጫ አድርጎ በመጠቀም ነው የሚሉ፡፡

2) ጸሐፊው በቅድሚያ የሚገልጸው ማርያምን ሲሆን እርሷንም በአማኝ ሕዝብ ቤተክርስቲያን መስሎ አቅርቧታል የሚሉ፡፡

3) ጸሐፊው በተመሳሳይ ወቅት/በአንድ ጊዜ ሰለማርያም እና ስለቤተክርስቲያን ይናገራል፡፡ ለአንዱ ከሌላው አስበልጦ ትኩረት አይሰጠውም፡፡ሁለቱንም እኩል ይገልፃቸዋል፡፡ ለዚህም የተጠቀመው ሁለት ነገር በአንድ ጊዜ የሚገልጽ ምስል ነው የሚሉ ናቸው፡፡

በእነዚህ ክፍፍሎች ውስጥ ደግሞ ጸሐፊው የሚናገረው ከክርስቶስ መምጣት በፊት ስለነበረው የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው ብለው የሚያስቡ ፣ ስለቤተክርስቲያን እና ስለእግዚአብሔር ሕዝብ ይናገራል ብለው የሚያስቡም አሉ፡፡ ዘመናዊው ሁኔታ በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበረውን የአመለካከት ልዩነት ብቻ ያንጸባርቃል፡፡ ይህንን ጽሑፍ ከተነተኑት አበው አብዛኞቹ ፀሐይን የለበሰች ሴት የክርስቲያኖችን ቤተክርስቲያን ይመለከታሉ ( ጄሮም፣ ቪክቶሪኑስ እና አጉስጢኖስ ) እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ‹‹ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን›› ሲሉ በአሮጌው እና በአዲሱ ኪዳን ውስጥ ያሉትን የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ማለት መሆኑን ነው፡፡ ጽሑፉ ለማርያም የተሰጠ መግለጫ ነው የሚሉ አስተያየቶች እዚህም እዚያም ቢሰሙም እነዚህ ጽሕፈት ማርያም የቤተክርስቲያን ምስል አድርገው አስበዋት አያውቁም፡፡ በእርግጥ እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በራእይ መጽሐፍ የተገለጠችውን ሴት ከቤተክርስቲያን ለይቶ የተመለከታት አልነበረም፡፡ ግና ሴቲቱ ለአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንብቻ ተምሰሌት ሆና ልትቆምአትችልም የሚለው ሃሳብ ይበልጥ እርግጠኛ ይመስላል፡፡ በራእይ 12፤5 የኢየሱስ እናት ነችና፡፡ በአዲስ ኪዳን ያለችው የክርስቲያን ቤተክርስቲያን የጌታዋ እናት ተብላ ልትጠራ ትችላለች? ከክርስቶስ ልደት በኋላ ቤተክርስቲያን ገና አልተወለደችምና፡፡ እዚህም ላይ ደግሞ ሴቲቱ እሰከምትወልድ ድረስ ያየችውን ስቃይ እንዲህ ነው ብሎ ለመተንተን አስቸጋሪ ነው፣ ሁለተኛ ማርያምን እና ቤተክርስቲያን ጋር ለይቶ ለማወቅ ከክርስቶስ ልደት በፊት ማርያም እና የእስራኤል ሕዝብ ማስወገድ በጽሑፉ ላይ አጥፍቶ መጥፋት መፈጸም ይሆንብናል፡፡ሆኖም አያሌ ሊቃውንት ሴቲቱ የብሉይ እን በሐዲስ ኪዳን የሚገኘው የእግዚአብሔር ሕዝብ ምሳሌ አድርገው ይወሰወዷታል፡፡

በሁለተኛነት ደግሞ ፣ እስራኤልን የመሲሑ እናት ነው ብሎ ማሰቡ ቀላል ሆኖ እናገኘው ይሆናል ነገር ግን እስራኤል እንደ ሕዝብ ፣ እሰራኤል እንደ አንድ ማኀበረሰብ መሲህ ተብሎ የሚጠራ ግለሰብ መውለዱን የሚነወገር አንዳች የብሉይ ኪዳን ቃል አናገኝም፡፡ በብሉይ ኪዳን ማኅበረሰብ ይወልዳል ነገር ግን መሲሕ የተባለውን የወለደች ግን አንዲት ሴት ብቻ ነች፡፡

አያሌ ካቶሊካውያን ጸሐፍት ሴቲቱ በቅድሚያ ከምንም በላይ የምትወክለው እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ነው ምክንያቱም በምልአት የመሲሕ እናት ተብሎ ልትጠራ የምትችለው እርሷ ብቻ ናት ብለው ያምናሉ፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ራእ12፣2 ላይ ሌላ እንቅፋት ይገጥመናል፤ ለበርካታ ዘመናት ብዙ ክርስቲያኖች የጌታ ልደት ስቃይ የሌለበት ነው ብለው ያሰቡ ነበር ፣ በርካታ ሰዎች ሴቲቱ ማርያም ናት ብለው የሚያስቡ ይህ አመለካከት ነበራቸው፡፡ ስለዚህም በራእይ 12፣2 ላይ ስላለው ስቃይ አሳማኝ ማስረጃ ላመቅረብ ከፍተኛ ጫና ነበረባቸው፡፡ ‹‹ እርሷም ነፍሰጡር ነበረች፣ ምጥ ይዧትም ተጨንቃ ትጮህ ነበር፡፡›› ከዚህ የበለጠ ቅሬታ የሚያስነሳው ደግሞ ልጁ እንደ ተወለደ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን የመወሰዱ እና ሴቲቱም ወደ በረሃ የመሸሿ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የመጽሐፉ ክፍል በቤተልሔም የነበረውን የጌታን ልደት ለማመልከት የገባ ነው ካልን ምን ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን? የትኛውንም ዓይነት ንድፈ ሐሳብ ብናዘጋጅ ለመመለስ አሰቸጋሪ የሆኑ እውነታዎች መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ 

(ይቀጥላል)

ምንጭ: The Mother of Jesus in the New Testament - በወጣት ሳምሶን ከቅ. ዮሴፍ ቁምስና ዘሲታውያን አዲስ አበባ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት