እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

5 - የእናት አገልግሎት

5 - የእናት አገልግሎት

የእግዚአብሔር ቃል፤ - እመቤታችን ማርያም ኤልሣቤጥን ጎበኘች፡፡ ሉቃስ 1፡ 39-45

ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጎብኘትና ለማገልገል በተራራማው በይሁዳ አገር ወዳለችው ከተማ በፍጥነት ተነሥታ ሄደች፡፡

ማርያም የእግዚአብሔርና የእኛ አገልጋይ ናት፡፡

እናት ከፍቅሯ የተነሣ ሁል ጊዜ ታገለግላለች፣ ከባሏና ከልጆቿ ምንም አትጠብቅም፡፡ የእርሷ ደስታ እነርሱ ሲያድጉ ማየት ነው፡፡ አገልግሎት እናመሰግናቸዋለን? ይህ አገልግሎት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ በእናቶቻችንና በሌሎች በሚያገለግሉት ሁሉ ላይ የመሆኑ ምልክት ነው፡፡

በሕብረተሰባችን ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ማገልገል የሚፈልጉ፡፡ በቤተሰባችን ውስጥም አንዱ አንዳንድ ጊዜ ማገልገልን ሳይሆን አለቃ መሆንን ይመርጣል፡፡ ኢየሱስ ግን ሁሉንም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡

‹‹ ›› (ማቴ 20፡ 25-28)፡፡

‹‹ ››(ዮሐ 13 12-15፣34)፡፡

ኢየሱስ የአገልግሎት ትእዛዝ ሁሉ በእናቱ በማርያም እንደተፈጸመ አይቷል፡፡ እርሱ፣ እንደ ሌሎች ልጆች፣ ፍፁም ሰው ስለሆነ፣ ከእናቱ ማገልገልን ተማረ፡፡ የእናት መስዋዕትነትና ጥሩ ምሳሌነት በቤት ውስጥ ፍሬ ያፈራል፡፡

እንጸልይ፡-

ዘላለማዊ አባት ሆይ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም የልጅህ እናት እንድትሆን ቅድስት ኤልሳቤጥንም በሚያስፈልጋት አገልግሎት እንድታገለግልና እንድትጎበኛት በመንፈስህ ሞላኃት፡፡ እኛንም ለመንፈስ ቅዱስ ስራ ልባችንን ክፍት አድርገህልን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ሁሌ አንተን እንድንወድስህ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት