እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

6 - ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን እንዴት ማመስገን እንዳለብን ታስተምረናለች

6 - ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን እንዴት ማመስገን እንዳለብን ታስተምረናለች

የእግዚአብሔር ቃል፤ - የማርያም የምስጋና ጸሎት፤ ሉቃስ 1፡ 46-55

እናታችን ማርያም፣ እርሷ የእግዚአብሔር የፍቅር ፍሬ እንደሆነች ተገንዝባለች፡፡ ‹‹ኀያሉ እግዚአብሔር እኔን ዝቅተኛ አገልጋይቱን ተመለከተና ታላላቅ ነገሮችን አደረገልኝ››፡፡ ማርያም ራሷን ከፍ ከፍ እያደረገች ሳይሆን እግዚአብሔርን እያመሰገነች ነው፡፡

እኛ የእግዚአብሔር ፍቅር ፍሬዎች ነን፡፡ እግዚአብሔርን ስለ ፍቅሩ እናመሰግነዋለን? በየቀኑ በቤታችን ጸሎት እናደርጋለን ወይ?

ቅዳሴ ትልቁ የምስጋና ጸሎት ነው፡፡ ከክርስቶስ መሥዋዕት አንድ በመሆን ሥራችንን፣ ሳምንታችንን፣ የሠራነውንና ክፋታችንን ለአባታችን ማቅረብና ለሕይወታችን ዋጋ መስጠት እንችላለን፡፡ በቅዳሴ ጊዜ በሳምንቱ ውስጥ የምንኖርበት የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን፡፡ በቁርባን የምናደርገው አንድነት በሳምንቱ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ይቀጥላል፡፡ እንደ ቤተሰብ እንሰበሰባለን፡፡ በሳምንቱ ውስጥ ይህንን አንድነት፣ ህብረትና መስዋዕት እንድንቀጥል ተጋብዘናል፡፡ ቅዳሴ የሳምንቱ ማዕዘን ድንጋያችን ነው፡፡ ይህ የማዕዘን ድንጋይ (ቅዳሴ) ከተነሳ በሳምንቱ የምናደርገው ነገር ፍፁም ሆኖ ወደ አብ አይደርስምና በአዲስ መንፈስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር የሚያስችለን ፀጋና የእግዚአብሔር ቃል አናገኝም፡፡

አንድ የአፍሪካውያን ክርስቲያኖች ቡድን በሁለት መቶ ክፍለ ዘመን የእሁድ ቅዳሴ ከመተው ሞትን እንደመረጡ ‹‹ያለ ቅዳሴ መኖር አንችልም›› አሉት፡፡ የሰሜን አፍሪካ ሰማዕታት ይህን ነገር ተገንዝበው ነበር፡፡ ቅዳሴ የሌለበት ሕይወት ዋጋ የለውም፡፡ የሮም ንጉሥ አውጆ ነበር ምክንያቱም ቅዳሴ ከሌለ ክርስቲያኖች ክርስቶስን እንደሚረሱ ያውቅ ስለነበር ነው፤ ሆኖም ግን ሰማዕታቱ ቅዳሴን ከማጣት ይልቅ ሕወታቸውን መሰዋቱን መርጠው ነበር፡፡

የእኛም እምነት እንደዚህ ነው ወይ? ቢያንስ በየሳምንቱ እሁድ ለሥርዓተ ቅዳሴ አንሄዳለን? ቅዱስ ቁርባንንስ እንቀበላለን ወይ? በጊዜና በአንድነት ከቤተሰባችን ለቅዳሴ እንሄዳን ወይ? እኛ ግን ስንት ጊዜ በቅዳሴ ፈንታ ዕድር፣ ለቅሶን፣ ገበያን ወይም እንግዳን መቀበልን እንመርጣለን!

እናታችን ማርያም በእግዚአብሔር እጅ ያለች መሳሪያ ብቻ መሆኑዋን ታውቃለች፣ መሳሪያነቷ የእሺታና በእግዚአብሔር እጅ ራሷን በግንዛቤ የማድረግ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለማዳኑ ስራ የእርሷነ ትብብረ ጠየቀ፣ እርሷም ዝግጁ ነበረች፡፡

እግዚአብሔር ይህን ዓለም ሲፈጥር ያለ እኛ ፈጠረ፣ አሁን ግን ዓለምን ሊያድን የእኛን ትብብር ይፈልጋ፡፡ የማርያም ትብብር (እሺታ) ልዩ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር የእኛንም እሺታ ይጠብቃልም ይፈልጋልም፡፡ በማርያመ እሺታ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ በእኛ እሺታ ኢየሱስ ወዴየቤተሰባችንና ወደየጎረቤቶቻችን ይገባል፡፡

እንጸልይ፡-

ሁሉን የምትችል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሆየ፣ አንተ ዝቅተኛይቱን ቅድስት ድንግል ማርየምን ከፍ በማድረግና የአዳኛችን እናት በማድረግህ የኃይልህን ውበት ገልጸሃል፡፡ ፀሐይን የለበሰችው ሴት ጸሎት፣ ክርስቶስን እየጠበቀች ላለች ዓለም እርሱን እንድታመጣና በባዶ የተሞላውን ዓለማችን በሕፃኑ ሕልውና እንዲሞላ፣ ለዘላለም በሚኖረውና በሚነግሰው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት