ክቡር አባ ዳንኤል ጌታቸው በኦስትርያ ደብረ ቅዱስ መስቀል የሲታውያን ገዳም ጎበኙ!
- Category: ዜናዎች
- Published: Friday, 20 October 2023 20:38
- Written by Super User
- Hits: 749
- 20 Oct

ክቡር አባ ዳንኤል ጌታቸው በኢትዮጵያ የገዳመ ሲታውያን ጠቅላይ አለቃ በቅርቡ በኦስትርያ የሚገኘውን እና 900 ዓመታት ያስቆጠረውን ታላቁን የደብረ ቅዱስ መስቀል ገዳመ-ሲታውያን መነኮሳን ጎብኝተዋል። ክቡር አባ ዳንኤል ጌታቸው በዚሁ ጉብኝታቸው ከገዳሙ አበምኔት ክክቡር አባ ማክስሚሊያን ሃይም እና ከገዳሙ መነኮሳን ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ቆይታቸው ክቡር አባ ዳንኤል ስለ ኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ እና ስለ ምንኩስና ታሪክ እና መንፈሳዊነት ለገዳሙ መነኮሳን ያጋሩ ሲሆን የገዳሙ አበምኔት ክቡር አባ ማክስሚሊያን ሃይም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የኢትዮጵያ ገዳመ ሲታውያንን እና መነኮሳንን እንዲጎበኙ እና አባታዊ ቡራኬያቸውን እንዲሰጡ ልባዊ ጥሪ አርበውላቸዋል።