ጾም-ጸሎት ከር.ሊ.ጳ. ጋር
- Category: ዜናዎች
- Published: Friday, 27 October 2023 08:31
- Written by Super User
- Hits: 933
- 27 Oct

“ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ!” (ሉቃ 2፡14)
ር.ሊ.ጳ ፍራቺስኮስ ለኲሏዊቷ ቤተ ክርስትያን ባቀረቡት የጾም ጸሎት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በመላው ዓለም የጾም እና የጸሎት ቀን ሆኖ ይውላል። ክርስትያኖች ይህንን ቀን ቅዳሴ በማስቀደስ፣ የመቁጠርያ ጸሎት በማድረስ፣ በጾም፣ የመለኮታዊ ምሕረት ጸሎት በማድረስ፣ በምጽዋት፣ በጽሙና እና በአርምሞ ለዓለም ሰላም እና ለቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ተሃድሶ በጸሎት እንዲተጉ ተጋብዘዋል። መላው የሲታውያን አባቶች እና ወንድሞች ከኲላዊቷ ቤተ ክርስትያን ጋር በጋራ በመሆን ይህንን ቀን በጾም ጸሎት ያሳልፋሉ!
በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይከብር ዘንድ!