ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቼክ ሬፐብሊክን ይጐበኛሉ
- Category: ዜናዎች
- Published: Thursday, 04 June 2009 23:11
- Written by Super User
- Hits: 2735
- 04 Jun
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የቼክ ሬፐብሊክ መንግሥት መሪ ፕሬዝዳንት ቫክላቭ ክላዉስ እና የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት፣ እኤአ ፊታችን መስከረም ወር 26 ቀን በረፓብሊክ ቸክ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የቫቲካን ማኅተም ክፍል መገለጫ አስታውቀዋል።
በዚሁ መግለጫ መሠረት፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በረፓብሊክ ቸክ ቆይታቸው ርእሰ ከተማ ፕራግ ብርኖ ስታራ፡ በለስላቭ ይጐበኛሉ።
ይህ ቅዱስ አባታችን በነዲክቶስ በቸክ ረፓብሊክ የሚያካሄዱት ጉብኝት አሥራ ሶስተኛ አገሮች አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ነው።
ነፍሰኄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እኤአ በ1997 ዓ.ም ረፓብሊክ ቸክ መጐብኘታቸው የሚታወስ ነው።
ትናትና የቸክ ረፓብሊክ መንግሥት መሪ ፕረሲዳንት ቫክላቭ ክላውስ ቫቲካን የጐበኙ ሲሆን ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶ ከየቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና ከየውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ከሊቀ ጳጳሳት ከብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር መገናኘታቸው ይታወቃል።
የቫቲካን መግለጫ እንዳመለከተው ፡ የቸክ ረፓብሊክ ፕረሲዳንት ክላውስ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከየቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና ከሊቀ ጳጳሳት ከብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር በተገናኙበት ግዜ ፡ የቸክ ረፓብሊክ ወቅታዊ ሁኔታ፡ የሀገሪቱ መንግሥት ከካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጋር ያላትን ግኑኝነት እና የረፓብሊክ ቸክ ክርስትያናዊ መንፈሳዊ እና ባህላዊ እሴቶች ትኩረት በሰጡ ጉዳዮች ተነጋግረዋል።
የቸክ ረፓብሊክ መንግሥት መሪ ፕረሲዳንት ቫክላቭ ክላውስ ከግንኘቱ በኋላ እንደገለጡት፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሀገራች እንዲጐበኙ የተደረገላቸው ዕድሜ አክብረው ፊታችን መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሀገሪቱ ለመጐብኘት ዝግጁ እና ደስተኛ መሆናቸው እንደገለጡላቸው እና ከፈተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ለመገናኛ ብዙኀን መግለጣቸው ተመልክተዋል።